1 ULB ኢየሱስ ለሕዝቡ የሚናገረውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ፣ ወደ ቅፍርናሆም ገባ። BSB BSB: When Jesus had concluded His discourse in the hearing of the people, He went to Capernaum.
2 ULB እጅግ የሚወደውና ሞት አፋፍ ላይ የደረሰ አገልጋይ የነበረው አንድ የመቶ አለቃ ነበረ። BSB BSB: There a highly valued servant of a centurion was sick and about to die.
3 ULB ስለ ኢየሱስ በሰማ ጊዜ መጥቶ አገልጋዩን ከመሞት እንዲያድንለት እንዲለምኑት የአይሁድ ሽማግሌዎችን ወደ እርሱ ላካቸው። BSB BSB: When the centurion heard about Jesus, he sent some Jewish elders to ask Him to come and heal his servant.
4 ULB እነርሱ ወደ ኢየሱስ በቀረቡ ጊዜ፣ "ለእርሱ ይህን ልታደርግለት የተገባ ነው፣ BSB BSB: They came to Jesus and pleaded with Him earnestly, “This man is worthy to have You grant this,
6 ULB ስለዚህ ኢየሱስ ዐብሮአቸው መንገዱን ቀጠለ። ነገር ግን ወደ ቤቱ ለመድረስ ጥቂት በቀረው ጊዜ፣ የመቶ አለቃው፣ እንዲህ ብለው እንዲነግሩት ወዳጆቹን ወደ ኢየሱስ ላካቸው፤ “ጌታ ሆይ፣ አትድከም፣ ምክንያቱም አንተ ወደ ቤቴ ልትገባ የተገባሁ አይደለሁም፤ BSB BSB: So Jesus went with them. But when He was not far from the house, the centurion sent friends with the message: “Lord, do not trouble Yourself, for I am not worthy to have You come under my roof.
7 ULB ከዚህ የተነሣ እኔም ራሴ ወደ አንተ ለመምጣት የምገባ አድርጌ እንኳ ራሴን አልቈጥረውም። ነገር ግን ቃል ብቻ ተናገር አገልጋዬ ይፈወሳል፤ BSB BSB: That is why I did not consider myself worthy to come to You. But just say the word, and my servant will be healed.
8 ULB እኔም ደግሞ ባለ ሥልጣን ነኝና፤ በእኔ ሥር ወታደሮች አሉኝ፤ አንዱን 'ሂድ' ስለው ይሄዳል፤ ሌላውን 'ና' ስለው ይመጣል። BSB BSB: For I myself am a man under authority, with soldiers under me. I tell one to go, and he goes, and another to come, and he comes. I tell my servant to do something, and he does it.”
9 ULB ኢየሱስ ይህን በሰማ ጊዜ፣ በመቶ አለቃው ተደንቀ፣ ይከተሉት ወደነበሩት ሰዎችም ዞር ብሎ፣ “በእስራኤልም እንኳ እንዲህ ያለ እምነት ያለው ሰው አላገኘሁም” አላቸው። BSB BSB: When Jesus heard this, He marveled at the centurion. Turning to the crowd following Him, He said, “I tell you, not even in Israel have I found such great faith.”
10 ULB ከዚያም የተላኩት ሰዎች ወደ መቶ አለቃው ቤት ተመልሰው፣ አገልጋዩን ጤናማ ሆኖ አገኙት። BSB BSB: And when the messengers returned to the house, they found the servant in good health.
11 ULB ከጥቂት ጊዜ በኋላ ኢየሱስ ናይን ወደ ምትባል ከተማ እየተጓዘ ነበር። ከእርሱም ጋር ደቀ መዛሙርቱና ብዙ ሕዝብ ዐብረውት ይሄዱ ነበር። BSB BSB: Soon afterward, Jesus went to a town called Nain. His disciples went with Him, accompanied by a large crowd.
12 ULB ወደ ከተማይቱም በቀረበ ጊዜ፣ እነሆ፣ ለእናቱ ብቸኛ ልጅ የነበረ ሰው ሞቶ አስከሬኑን ሰዎች ተሸክመው እየሄዱ ነበር። የልጁ እናት መበለት ነበረች፤ በርከት ያሉ ለቀስተኞችም ተከትለዋት ነበር። BSB BSB: As He approached the town gate, He saw a dead man being carried out, the only son of his mother, and she was a widow. And a large crowd from the town was with her.
13 ULB ጌታም ተመልክቷት እጅግ ዐዘነላትና፣ “አታልቅሺ” አላት። BSB BSB: When the Lord saw her, He had compassion on her and said, “Do not weep.”
14 ULB ከዚያም ወደ ቃሬዛው ተጠግቶ ነካው ቃሬዛውን የተሸከሙትም ቆሙ። ኢየሱስ፣ “አንተ ወጣት ተነሥ እልሃለሁ” አለ። BSB BSB: Then He went up and touched the coffin, and those carrying it stood still. “Young man,” He said, “I tell you, get up!”
15 ULB ወጣቱም ተነሥቶ መናገር ጀመረ፤ ከዚያም ኢየሱስ ልጁን ለእናትዮዋ ሰጣት። BSB BSB: And the dead man sat up and began to speak! Then Jesus gave him back to his mother.
16 ULB ከዚያም ሁሉንም ፍርሀት ያዛቸው። “ታላቅ ነቢይ በመካከላችን ተነሥቶአል" "ደግሞ እግዚአብሔር ሕዝቡን ጎበኝቶአል” በማለት እግዚአብሔርን አመሰገኑ። BSB BSB: A sense of awe swept over all of them, and they glorified God. “A great prophet has appeared among us!” they said. “God has visited His people!”
17 ULB ይህ የኢየሱስ ዝና በመላው ይሁዳና በዙሪያው ባለው አገር ሁሉ ተሰማ። BSB BSB: And the news about Jesus spread throughout Judea and all the surrounding region.
18 ULB የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ አወሩለት። BSB BSB: Then John’s disciples informed him about all these things.
19 ULB ከዚያም ዮሐንስ፣ “የምትመጣው አንተ ነህን ወይስ ሌላ እንጠብቅ?” ብለው እንዲጠይቁት ከእነርሱ ሁለቱን ወደ ኢየሱስ ላካቸው። BSB BSB: So John called two of his disciples and sent them to ask the Lord, “Are You the One who was to come, or should we look for someone else?”
20 ULB ሰዎቹም ወደ ኢየሱስ ቀርበው፣ "'የምትመጣው አንተ ነህን ወይስ ሌ እንጠብቅ?' ብለን እንድንጠይቅህ መጥምቁ ዮሐንስ ልኮናል" አሉ። BSB BSB: When the men came to Jesus, they said, “John the Baptist sent us to ask, ‘Are You the One who was to come, or should we look for someone else?’”
21 ULB በዚያኑ ሰዓት ኢየሱስ ብዙ ሰዎችን ከተለያየ ደዌና በሽታ ፈወሰ። በአጋንንት የተያዙትን ነጻ አወጣ፣ ዐይነ ስውራንም ማየት እንዲችሉ አደረገ። BSB BSB: At that very hour Jesus healed many people of their diseases, afflictions, and evil spirits, and He gave sight to many who were blind.
22 ULB ኢየሱስ መልእክተኞቹን፣ “ወደ ዮሐንስ ተመልሳችሁ ሂዱና ያያችሁትንና የሰማችሁትን እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፣ ዐይነ ስውራን ያያሉ፣ ሽባዎች ይራመዳሉ፣ ለምጻሞች ይነጻሉ፣ መስማት የተሳናቸው ይሰማሉ፣ ሙታን ይነሣሉ፣ ለድኾችም ወንጌል እየተሰበከ ነው። BSB BSB: So He replied, “Go back and report to John what you have seen and heard: The blind receive sight, the lame walk, the lepers are cleansed, the deaf hear, the dead are raised, and the good news is preached to the poor.
23 ULB በማደርጋቸው ነገሮች በእኔ ሳይሰናከል በእምነቱ የሚጸና ሰው የተመሰገነ ነው” አላቸው። BSB BSB: Blessed is the one who does not fall away on account of Me.”
24 ULB የዮሐንስ መልእክተኞች ከሄዱ በኋላ ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ ለሕዝቡ እንዲህ ይላቸው ጀመር፣ “ምን ልታዩ ወደ በረሐ ወጣችሁ በነፋስ የሚወዛወዘውን ሸንበቆ ለማየት ነውን? BSB BSB: After John’s messengers had left, Jesus began to speak to the crowds about John: “What did you go out into the wilderness to see? A reed swaying in the wind?
25 ULB ወይስ የወጣችሁት የሚያማምሩ ልብሶች የለበሱትን ለማየት ነውን? እነሆ፣ የሚያማምሩ ልብሶችን ለብሰው በድሎት የሚኖሩ ሰዎች የሚገኙት በአብያተ መንግሥታት ነው። BSB BSB: Otherwise, what did you go out to see? A man dressed in fine clothes? Look, those who wear elegant clothing and live in luxury are found in palaces.
26 ULB ልታዩ የወጣችሁት ግን ነቢይን ከሆነ፣ እንግዲያውስ ያያችሁት ነቢይን ብቻ ሳይሆን ከነቢያትም የበለጠውን ነው። BSB BSB: What then did you go out to see? A prophet? Yes, I tell you, and more than a prophet.
27 ULB ስለ እርሱ፣ ‘እነሆ፣ በፊታችሁ መንገድን የሚጠርግ መልእክተኛዬን እልካለሁ’ ተብሎ ተጽፏል። BSB BSB: This is the one about whom it is written: ‘Behold, I will send My messenger ahead of You, who will prepare Your way before You.’
28 ULB እላችኋለሁ፣ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም፤ ቢሆንም በእግዚአብሔር መንግሥት ከሁሉም የሚያንሰው ይበልጠዋል። BSB BSB: I tell you, among those born of women there is no one greater than John, yet even the least in the kingdom of God is greater than he.”
29 ULB ይህን በሰሙ ጊዜ ቀራጮች እንኳ ሳይቀሩ ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔር ጻድቅ እንደ ሆነ ተናገሩ፤ ምክንያቱም እነርሱን ያጠመቃቸው ዮሐንስ ነበር። BSB BSB: All the people who heard this, even the tax collectors, acknowledged God’s justice. For they had received the baptism of John.
30 ULB በዮሐንስ ያልተጠመቁት ፈሪሳውያንና የአይሁድ የሕግ ዐዋቂዎች ግን በራሳቸው ፈቃድ የእግዚአብሔርን ጥበብ ተቃወሙ። BSB BSB: But the Pharisees and experts in the law rejected God’s purpose for themselves, because they had not been baptized by John.
31 ULB እንግዲያውስ የዚህን ትውልድ ሰዎች ከምን ጋር አመሳስላቸዋለሁ? ምንስ ይመስላሉ? BSB BSB: “To what, then, can I compare the men of this generation? What are they like?
32 ULB እርስ በርሳቸው በገበያ እየተጠራሩ፥ ‘እንቢልታ ነፋንላችሁ እናንተም አልዘፈናችሁም፣ ሙሾ አወጣንላችሁ እናንተም አላለቀሳችሁም’ እንደሚባባሉ ልጆች ናቸው። BSB BSB: They are like children sitting in the marketplace and calling out to one another: ‘We played the flute for you, and you did not dance; we sang a dirge, and you did not weep.’
33 ULB መጥምቁ ዮሐንስ እንጀራ ሳይበላና ወይን ጠጅ ሳይጠጣ ቢመጣ፣ ‘ጋኔን አለበት’ አላችሁት፣ BSB BSB: For John the Baptist came neither eating bread nor drinking wine, and you say, ‘He has a demon!’
34 ULB የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ ቢመጣ፦ ‘በላተኛና ጠጪ፣ የቀራጮችና የኃጢአተኞች ወዳጅ!’ አላችሁት። BSB BSB: The Son of Man came eating and drinking, and you say, ‘Look at this glutton and drunkard, a friend of tax collectors and sinners!’
35 ULB ጥበብ ግን በልጆቿ ሁሉ ትክክል እንደ ሆነች ታወቀች። BSB BSB: But wisdom is vindicated by all her children.”
36 ULB አንድ ፈሪሳዊም በቤቱ ዐብሮት እንዲመገብ ኢየሱስን ጋበዘው ኢየሱስ ግብዣውን ተቀብሎ ወደ ማዕዱ ቀረበ። BSB BSB: Then one of the Pharisees invited Jesus to eat with him, and He entered the Pharisee’s house and reclined at the table.
37 ULB እነሆ፣ በዚያ ከተማ በመጥፎ ምግባሯ የታወቀች እንዲት ሴት ኢየሱስ በፈሪሳዊው ቤት ተጋብዞ በማዕድ እንደ ተቀመጠ ተረድታ የአልባስጥሮስ ሽቱ ብልቃጥ ይዛ ወደ ቤቱ ገባችና BSB BSB: When a sinful woman from that town learned that Jesus was dining there, she brought an alabaster jar of perfume.
38 ULB ከኢየሱስ በስተኋላ ከእግሩ አጠገብ ቆማ ማልቀስ ጀመረች። ከዚያም በእንባዋ እግሩን ማራስና በፀጉሯም ማበስ ቀጠለች፣ እግሩንም ትስመው በሽቱም ትቀባው ነበር። BSB BSB: As she stood behind Him at His feet weeping, she began to wet His feet with her tears and wipe them with her hair. Then she kissed His feet and anointed them with the perfume.
39 ULB ኢየሱስን የጋበዘው ፈሪሳዊ ይህንን ባየ ጊዜ፣ "ይህ ሰው በእርግጥ ነቢይ ቢሆን ኖሮ እየነካችው ያለችው ሴት ምን ዓይነት ሴት እንደ ሆነች ባወቀም ነበር" ብሎ በልቡ ዐሰበ። BSB BSB: When the Pharisee who had invited Jesus saw this, he said to himself, “If this man were a prophet, He would know who this is and what kind of woman is touching Him—for she is a sinner!”
40 ULB ኢየሱስም መልሶ ፈሪሳዊውን፣ “አንድ የምነግርህ ነገር አለኝ” አለው። ፈሪሳዊውም፣ “መምህር ሆይ፣ ተናገር” አለው። BSB BSB: But Jesus answered him, “Simon, I have something to tell you.” “Tell me, Teacher,” he said.
41 ULB ኢየሱስ፣ “ከአንድ አበዳሪ ገንዘብ የተበደሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፣ አንደኛው የአምስት መቶ ዲናር ሌላኛው ደግሞ የሃምሳ ዲናር ዕዳ ነበረባቸው፤ BSB BSB: “Two men were debtors to a certain moneylender. One owed him five hundred denarii, and the other fifty.
42 ULB የሚከፍሉት ስላልነበራቸው ሁለቱንም ዕዳቸውን ማራቸው። ስለዚህ ዕዳቸው ከተማረላቸው ከእነዚህ ከሁለቱ ማንኛቸው አብዳሪውን የበለጠ የሚወደው ይመስልሃል? አለው። BSB BSB: When they were unable to repay him, he forgave both of them. Which one, then, will love him more?”
43 ULB ስምዖንም መልሶ፣ “ብዙ የተተወለቱ ይመስለኛል” አለው። ኢየሱስ፣ “በትክክል መልሰሃል” አለው። BSB BSB: “I suppose the one who was forgiven more,” Simon replied. “You have judged correctly,” Jesus said.
44 ULB ኢየሱስም ወደ ሴትዮይቱ ዞር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፣ “ይህችን ሴት ትመለከታታለህ? እኔ ወደ ቤትህ ገብቼ ለእግሬ ውሃ እንኳን አላቀረብህልኝም፣ እርሷ ግን በእንባዋ እግሬን አራሰች፣ በፀጉሯም አበሰችው፤ BSB BSB: And turning toward the woman, He said to Simon, “Do you see this woman? When I entered your house, you did not give Me water for My feet, but she wet My feet with her tears and wiped them with her hair.
45 ULB አንተ አልሳምኸኝም፣ እርሷ ግን ከመጣሁበት ጊዜ ጀምሮ እግሬን ከመሳም አላቋረጠችም። BSB BSB: You did not greet Me with a kiss, but she has not stopped kissing My feet since I arrived.
46 ULB አንተ ራሴን ዘይት አልቀባኸኝም፣ እርሷ ግን እግሬን ሽቱ ቀባች፣ BSB BSB: You did not anoint My head with oil, but she has anointed My feet with perfume.
47 ULB ስለዚህ ለበዛው ኃጢአቷ ብዙ ምሕረትን አግኝታለችና አብዝታ ወዳለች። ጥቂት ኃጢአቱ ይቅር የተባለለት ግን ጥቂት ይወዳል” አለው። BSB BSB: Therefore I tell you, her many sins have been forgiven, for she has loved much. But he who has been forgiven little loves little.”
48 ULB ከዚያም ወደ ሴቱቱ ዞር ብሎ፣ “ኃጢአትሽ ተሰርዮልሻል” አላት። BSB BSB: Then Jesus said to her, “Your sins are forgiven.”
49 ULB በዚያም ተቀምጠው የነበሩት እርስ በርሳቸው፣ “ኃጢአትን ይቅር የሚል ይህ ማን ነው?” አሉ። BSB BSB: But those at the table began to say to themselves, “Who is this who even forgives sins?”
50 ULB ከዚያም ኢየሱስ ሴቲቱን፣ “እምነትሽ አድኖሻል። በስላም ሂጂ” አላት። BSB BSB: And Jesus told the woman, “Your faith has saved you; go in peace.”