1 ULB ኢየሱስም በምሳሌ ይነግራቸው ጀመር፡፡ አንድ ሰው የወይን ተክል ተከለ፤በዙሪያው ዐጥር ሠራ፤ለወይን መጭመቂያ የሚሆን ጕድጓድ ቈፈረ፤ማማም ሠራ፡፡ ለገበሬዎችም አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ፡፡ BSB BSB: Then Jesus began to speak to them in parables: “A man planted a vineyard. He put a wall around it, dug a wine vat, and built a watchtower. Then he rented it out to some tenants and went away on a journey.
2 ULB በወቅቱ የወይኑን ፍሬ እንዲቀበል አንድ አገልጋይ ወደ ገበሬዎቹ ላከ፡፡ BSB BSB: At harvest time, he sent a servant to the tenants to collect his share of the fruit of the vineyard.
3 ULB እነርሱም አገልጋዩን ያዙት፤ ደብድበውም ባዶ እጁን ሰደዱት፡፡ BSB BSB: But they seized the servant, beat him, and sent him away empty-handed.
4 ULB በድጋሚም ሌላ አገልጋይ ላከ፤እነርሱም ፈነከቱት፤ አሳፈሩትም፡፡ BSB BSB: Then he sent them another servant, and they struck him over the head and treated him shamefully.
5 ULB ሌላም አገልጋይ ወደ እነርሱ ላከ፤ እርሱንም ገደሉት፡፡ ብዙዎች ሌሎችንም ላከ፤ አንዳንዶቹን ደበደቡ፤ ሌሎቹንም ገደሉ፡፡ BSB BSB: He sent still another, and this one they killed. He sent many others; some they beat and others they killed.
6 ULB የወይኑ ተክል ባለቤት አንድ ተወዳጅ ልጅ ነበረው፤ልጄን ያከብሩታል በማለት በመጨረሻ እርሱን ላከው፡፡ BSB BSB: Finally, having one beloved son, he sent him to them. ‘They will respect my son,’ he said.
7 ULB ገበሬዎቹ ግን እርስበርሳቸው እንዲህ አሉ፡፡ ይህ ወራሹ ነው ኑ እንግደለው ሀብቱ ሁሉ የእኛ ይሆናል ተባባሉ፡፡ BSB BSB: But the tenants said to one another, ‘This is the heir. Come, let us kill him, and the inheritance will be ours.’
8 ULB ልጁንም ያዙት፤ ገደሉት፤ከወይኑ ቦታ ውጭም ጣሉት፡፡ BSB BSB: So they seized the son, killed him, and threw him out of the vineyard.
9 ULB የወይኑ ተክል ባለቤት በዚህ ጊዜ ምን ያደርጋል? ይመጣና ገበሬዎቹን ያጠፋቸዋል፤የወይን ቦታውንም ለሌሎች ይሰጣቸዋል፡፡ BSB BSB: What then will the owner of the vineyard do? He will come and kill those tenants and give the vineyard to others.
10 ULB ይህን የመጽሓፍ ቃል አላነበባችሁምን? እነሆ ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማእዘን ድንጋይ ሆነ፤ BSB BSB: Have you never read this Scripture: ‘The stone the builders rejected has become the cornerstone.
11 ULB ይህ ከጌታ ነው፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው፡፡ BSB BSB: This is from the Lord, and it is marvelous in our eyes’?”
12 ULB ኢየሱስ ምሳሌውን የተናገረው ስለ እነርሱ እንደ ሆነ ስለ ተገነዘቡ እጃቸውን ሊጭኑበት ፈለጉ፤ነገር ግን ሕዝቡን ስለ ፈሩ፤ትተውት ሄዱ፡፡ BSB BSB: At this, the leaders sought to arrest Jesus, for they knew that He had spoken this parable against them. But fearing the crowd, they left Him and went away.
13 ULB እነርሱም በንግግር እንዲያጠምዱት አንዳንድ ፈሪሳውያንና ከሄሮድስ ወገን የሆኑ ሰዎችን ላኩ፡፡ BSB BSB: Later, they sent some of the Pharisees and Herodians to catch Jesus in His words.
14 ULB ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ እንዲህ አሉት፤መምህር ሆይ፣ አንተ እውነተኛ እንደ ሆንህ ለማንም በይሉኝታ እንደማታደርግ፣ለሰው ፊትም እንደማታዳላ ነገር ግን የእግዚአብሔርን መንገድ በእውነት እንደምታስተምር እናውቃለን፡፡ ለቄሳር ግብር መክፈል ተገቢ ነው? ወይስ አይደለም? BSB BSB: “Teacher,” they said, “we know that You are honest and seek favor from no one. Indeed, You are impartial and teach the way of God in accordance with the truth. Is it lawful to pay taxes to Caesar or not? Should we pay them or not?”
15 ULB እንክፈል ወይስ አንክፈል? አሉት፡፡ ኢየሱስ ግን ግብዝነታቸውን ዐውቆ ለምን ትፈትኑኛላችሁ? አላቸው፡፡ እንዳየው አንደ ዲናር አምጡልኝ አላቸው፡፡ BSB BSB: But Jesus saw through their hypocrisy and said, “Why are you testing Me? Bring Me a denarius to inspect.”
16 ULB እነርሱም አመጡለት፡፡ ኢየሱስም ይህ ምስል ቅርጹም የማን ነው? አላቸው፡፡ እነርሱም የቄሳር ነው አሉት፡፡ BSB BSB: So they brought it, and He asked them, “Whose image is this? And whose inscription?” “Caesar’s,” they answered.
17 ULB ኢየሱስም እንግዲህ የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር ስጡ አላቸው፡፡ እጅግም ተገረሙበት፡ BSB BSB: Then Jesus told them, “Give to Caesar what is Caesar’s, and to God what is God’s.” And they marveled at Him.
18 ULB ትንሣኤ ሙታን የለም የሚሉ ሰዱቃውያን ወደ እርሱ መጥተው እንዲህ ብለው ጠየቁት፡፡ BSB BSB: Then the Sadducees, who say there is no resurrection, came to Jesus and questioned Him:
19 ULB መምህር ሆይ፣ ሙሴ፣ አንድ ሰው ልጅ ሳይወልድ ሚስቱን ትቶ ቢሞት፣ ወንድሙ እርስዋን አግብቶ ለወንድሙ ዘር ይተካለት ብሎ ጽፎልናል፡፡ BSB BSB: “Teacher, Moses wrote for us that if a man’s brother dies and leaves a wife but no children, the man is to marry his brother’s widow and raise up offspring for him.
20 ULB ሰባት ወንድማማቾች ነበሩ፡፡ የመጀመሪያው ሚስት አገባ፤ ዘር ሳይተካም ሞተ፡፡ BSB BSB: Now there were seven brothers. The first one married and died, leaving no children.
21 ULB ሁለተኛውም አገባት፤ እርሱም ዘር ሳይተካለት ሞተ፡፡ ሦስተኛውም እንዲሁ፡፡ BSB BSB: Then the second one married the widow, but he also died and left no children. And the third did likewise.
22 ULB ሰባቱም ለወንድማቸው ዘር አልተኩም፡፡ ከሁሉም በኋላ ሴቲቱም ደግሞ ሞተች፡፡ BSB BSB: In this way, none of the seven left any children. And last of all, the woman died.
23 ULB ታዲያ ይህች ሴት በትንሣኤ የየትኛው ሚስት ትሆናለች? አሉት፡፡ ሰባቱም አግብተዋት ነበርና፡፡ BSB BSB: In the resurrection, then, whose wife will she be? For all seven were married to her.”
24 ULB ኢየሱስም የምትስቱት መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኀይል ስለማታውቁ አይደለምን? BSB BSB: Jesus said to them, “Aren’t you mistaken, because you do not know the Scriptures or the power of God?
25 ULB በትንሳኤ ጊዜ ሰዎች አያገቡም፤ አይጋቡም፤ ነገር ግን በሰማይ እንደ መላእክት ይሆናሉ እንጂ፡፡ BSB BSB: When the dead rise, they will neither marry nor be given in marriage. Instead, they will be like the angels in heaven.
27 ULB እርሱ የሕያዋን አምላክ እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም፡፡ BSB BSB: He is not the God of the dead, but of the living. You are badly mistaken!”
30 ULB አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህ፣በፍጹም አሳብህ፣ በፍጹምም ኀይልህ ውደድ የምትለዋ ናት፡፡ BSB BSB: Love the Lord your God with all your heart and with all your soul and with all your mind and with all your strength.’
31 ULB ሁለተኛዋም ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትለዋ ናት፡፡ ከእነዚህ የሚበልጥ ምንም ሌላ ትእዛዝ የለም አለው፡፡ BSB BSB: The second is this: ‘Love your neighbor as yourself.’ No other commandment is greater than these.”
32 ULB ሰውዬውም መምህር ሆይ፣በእውነት መልካም ብለሃል፤ እርሱ አንድ ነው፤ከእርሱም በቀር ሌላ የለም፤ እርሱን በፍጹም ልብ፣ በፍጹም ማስተዋል፣ BSB BSB: “Right, Teacher,” the scribe replied. “You have stated correctly that God is One and there is no other but Him,
33 ULB በፍጹም ኀይል መውደድና ባልንጀራን እንደ ራስ መውደድ ሁሉንም ዓይነት መስዋእትና የሚቃጠል መሥዋእት ከማቅረብ ይበልጣል አለ፡፡ BSB BSB: and to love Him with all your heart and with all your understanding and with all your strength, and to love your neighbor as yourself. This is more important than all burnt offerings and sacrifices.”
34 ULB ኢየሱስም ሰውዬው በማስተዋል እንደ መለሰለት ባየ ጊዜ አንተ ከእግዚአብሔር መንግስት የራቅህ አይደለህም አለው፡፡ ከዚያ በኋላ ማንም ሰው ምንም ጥያቄ ሊጠይቀው አልደፈረም፡፡ BSB BSB: When Jesus saw that the man had answered wisely, He said, “You are not far from the kingdom of God.” And no one dared to question Him any further.
35 ULB ኢየሱስም መለሰላቸው፤ በቤተ መቅደስ ውስጥ ሲያስተምር፣ ጸሓፍት ክርስቶስ የዳዊት ልጅ ነው የሚሉት እንዴት ነው? አለ፡፡ BSB BSB: While Jesus was teaching in the temple courts, He asked, “How can the scribes say that the Christ is the Son of David?
36 ULB ዳዊት ራሱ በመንፈስ ቅዱስ ጌታ ጌታዬን ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው፡፡ BSB BSB: Speaking by the Holy Spirit, David himself declared: ‘The Lord said to my Lord, “Sit at My right hand until I put Your enemies under Your feet.”’
37 ULB ዳዊት ራሱ ጌታዬ ብሎ ይጠራዋል፤ ታዲያ እንዴት ልጁ ይሆናል? ሕዝቡም በደስታ ይሰማው ነበር፡፡ BSB BSB: David himself calls Him ‘Lord.’ So how can He be David’s son?” And the large crowd listened to Him with delight.
38 ULB ኢየሱስም እንዲህ አለ፡፡ ከጸሓፍት ተጠንቀቁ፤ የተንዘረፈፈ ልብስ ለብሰው መሄድን ይወድዳሉ፤ እነርሱ በገበያ ቦታ ሰላምታን፣ BSB BSB: In His teaching Jesus also said, “Watch out for the scribes. They like to walk around in long robes, to receive greetings in the marketplaces,
39 ULB በምኩራብም የክብር ወንበር፣ በግብዣም የክብር ቦታ ላይ መቀመጥ ይወድዳሉ፡፡ BSB BSB: and to have the chief seats in the synagogues and the places of honor at banquets.
40 ULB ለይምሰል ጸሎት በማስረዘም የመበለቶችን ቤት ይበዘብዛሉ፡፡ እነዚህ የባሰ ፍርድ ይቀበላሉ፡፡ BSB BSB: They defraud widows of their houses, and for a show make lengthy prayers. These men will receive greater condemnation.”
41 ULB ኢየሱስም በመባ መቀበያው ፊት ለፊት ተቀመጠ፡፡ ብዙ ሰዎች በመባ መቀበያው ውስጥ ገንዘብ ሲጨምሩ ተመለከተ፡፡ ብዙ ሃብታሞች ብዙ ገንዘብ ይጨምሩ ነበር፡፡ BSB BSB: As Jesus was sitting opposite the treasury, He watched the crowd putting money into it. And many rich people put in large amounts.
42 ULB ከዚያም አንዲት ድኻ መበለት መጥታ ሁለት ናስ ጨመረች፤ይህም የብር ሩብ ነው፡፡ BSB BSB: Then one poor widow came and put in two small copper coins, which amounted to a small fraction of a denarius.
43 ULB እርሱም ደቀመዛሙርቱን ወደ ራሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፡፡ እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ይህች መበለት በመባ መቀበያው ውስጥ ገንዘባቸውን ከጨመሩት ሁሉ አብልጣ ሰጠች፡፡ BSB BSB: Jesus called His disciples to Him and said, “Truly I tell you, this poor widow has put more than all the others into the treasury.
44 ULB እነርሱ ከትርፋቸው ሰጥተዋልና፡፡ እርስዋ ግን ከጉድለቷ ሰጠች፤ ያላትን ሁሉ ሰጠች፤ ኑሮዋን እንኳ ሳይቀር ሁሉንም ሰጠች፡፡ BSB BSB: For they all contributed out of their surplus, but she out of her poverty has put in all she had to live on.”