1 ULB እንዲህም ሆነ፤ ኢየሱስ ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ገሊላን ትቶ፣ በዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ወዳለው ወደ ይሁዳ ጠረፍ መጣ፡፡ BSB BSB: When Jesus had finished saying these things, He left Galilee and went into the region of Judea beyond the Jordan.
2 ULB ብዙ ሕዝብ ተከተሉት፤ እዚያም ፈወሳቸው፡፡ BSB BSB: Large crowds followed Him, and He healed them there.
3 ULB ፈሪሳውያን እንዲህ በማለት ሊፈትኑት ወደ እርሱ መጡ፤ "በማንኛውም ምክንያት ሰው ሚስቱን ቢፈታ ሕጋዊ ነውን?" BSB BSB: Then some Pharisees came and tested Him by asking, “Is it lawful for a man to divorce his wife for any reason?”
5 ULB ደግሞም፣ 'በዚህ ምክንያት ሰው አባቱንና እናቱን ትቶ ከሚስቱ ጋር ይጣመራል፤ አንድ ሥጋም ይሆናሉ' የተባለውን አላነበባችሁምን? BSB BSB: and said, ‘For this reason a man will leave his father and mother and be united to his wife, and the two will become one flesh’?
6 ULB ስለዚህ እነርሱ ከእንግዲህ አንድ ሥጋ እንጂ ሁለት አይደሉም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር አንድ ላይ ያጣመረውን፣ ማንም አይለየው፡፡›› BSB BSB: So they are no longer two, but one flesh. Therefore what God has joined together, let man not separate.”
7 ULB እነርሱ፣ "ታዲያ የፍቺ የምስክር ወረቀት ሰጥተን ከዚያ በኋላ እንድናባርራት ሙሴ ለምን አዘዘን?" አሉት፡፡ BSB BSB: “Why then,” they asked, “did Moses order a man to give his wife a certificate of divorce and send her away?”
9 ULB እኔ እላችኋለሁ፣ ከዝሙት በቀር ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ፣ ሌላይቱንም የሚያገባ ያመነዝራል፤ የተፈታችውንም የሚያገባ ያመነዝራል፡፡" BSB BSB: Now I tell you that whoever divorces his wife, except for sexual immorality, and marries another woman commits adultery.”
11 ULB ኢየሱስ ግን እንዲህ አላቸው፤ "እንዲቀበሉት የተፈቀደላቸው እንጂ፣ ሁሉም ሰው ይህን ትምህርት አይቀበለውም፡፡ BSB BSB: “Not everyone can accept this word,” He replied, “but only those to whom it has been given.
13 ULB በዚያን ጊዜ እጁን ጭኖ እንዲጸልይላቸው ሰዎች ልጆችን ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ገሠጿቸው፡፡ BSB BSB: Then little children were brought to Jesus for Him to place His hands on them and pray for them. And the disciples rebuked those who brought them.
14 ULB ኢየሱስ ግን፣ "ልጆቹን ተዉአቸው፤ ወደ እኔም እንዲመጡ አትከልክሏቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉት ናትና" አለ፡፡ BSB BSB: But Jesus said, “Let the little children come to Me, and do not hinder them! For the kingdom of heaven belongs to such as these.”
15 ULB 15 እጁንም በልጆቹ ላይ ጫነባቸው፤ ከዚያም ያን ቦታ ትቶ ሄደ፡፡ BSB BSB: And after He had placed His hands on them, He went on from there.
16 ULB እነሆ፣ አንድ ሰው ወደ ኢየሱስ መጥቶ፣ ‹‹መምህር ሆይ፣ የዘላለም ሕይወት እንዳገኝ ምን መልካም ነገር ማድረግ አለብኝ?›› አለ፡፡ BSB BSB: Just then a man came up to Jesus and inquired, “Teacher, what good thing must I do to obtain eternal life?”
17 ULB ኢየሱስ፣ ‹‹ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም አንድ ብቻ ነው፤ ነገር ግን ወደ ሕይወት ለመግባት ብትፈልግ ትእዛዛትን ጠብቅ›› አለው፡፡ BSB BSB: “Why do you ask Me about what is good?” Jesus replied. “There is only One who is good. If you want to enter life, keep the commandments.”
18 ULB ሰውዬው፣ ‹‹የትኞቹን ትእዛዛት? አለ፡፡ ኢየሱስ እንዲህ አለው፤ "አትግደል፤" "አታመንዝር" "አትስረቅ፤" "በሐሰት አትመስክር፤" BSB BSB: “Which ones?” the man asked. Jesus answered, “‘Do not murder, do not commit adultery, do not steal, do not bear false witness,
19 ULB "አባትህንና እናትህን አክብር፤" እንዲሁም፣ "ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፡፡" BSB BSB: honor your father and mother, and love your neighbor as yourself.’”
20 ULB ወጣቱ፣ "እነዚህን ነገሮች ሁሉ ፈጽሜአለሁ፣ ሌላስ ምን ያስፈልገኛል?" አለው፡፡ BSB BSB: “All these I have kept,” said the young man. “What do I still lack?”
21 ULB ኢየሱስ እንዲህ አለው፤ "ፍጹም ለመሆን ብትፈልግ፣ ሂድና ያለህን ሽጠህ ለድኾችም ስጠው፤ በሰማይም ሀብት ይኖርሃል፡፡ ከዚያም መጥተህ ተከተለኝ፡፡›› BSB BSB: Jesus told him, “If you want to be perfect, go, sell your possessions and give to the poor, and you will have treasure in heaven. Then come, follow Me.”
22 ULB ነገር ግን ወጣቱ ኢየሱስ የተናገረውን በሰማ ጊዜ፣ ብዙ ንብረት ነበረውና ዐዝኖ ሄደ፡፡ BSB BSB: When the young man heard this, he went away in sorrow, because he had great wealth.
23 ULB ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ "እውነት እላችኋለሁ፤ ለባለ ጠጋ ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት ከባድ ነው፡፡ BSB BSB: Then Jesus said to His disciples, “Truly I tell you, it is hard for a rich man to enter the kingdom of heaven.
24 ULB ደግሜ እላችኋለሁ፤ ለባለ ጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከመግባት፣ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል፡፡" BSB BSB: Again I tell you, it is easier for a camel to pass through the eye of a needle than for a rich man to enter the kingdom of God.”
25 ULB ደቀ መዛሙርቱ ይህን በሰሙ ጊዜ በጣም ተደነቁና፣ "ታዲያ ማን ሊድን ይችላል?" አሉ፡፡ BSB BSB: When the disciples heard this, they were greatly astonished and asked, “Who then can be saved?”
26 ULB ኢየሱስ ወደ እነርሱ ተመልክቶ፣ "ይህ ለሰዎች የማይቻል ነው፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል" አለ፡፡ BSB BSB: Jesus looked at them and said, “With man this is impossible, but with God all things are possible.”
27 ULB ከዚያም ጴጥሮስ መልሶ፣ "ተመልከት፣ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ፤ ታዲያ ምን እናገኛለን?" አለ፡፡ BSB BSB: “Look,” Peter replied, “we have left everything to follow You. What then will there be for us?”
28 ULB ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ "እውነት እላችኋለሁ፣ እናንተ እኔን የተከተላችሁኝ፣ በዐዲሱ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን ላይ በሚቀመጥበት ጊዜ፣ እናንተም በዐሥራ ሁለት ዙፋኖች ላይ ትቀመጣላችሁ፤ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶችም ላይ ትፈርዳላችሁ፡፡ BSB BSB: Jesus said to them, “Truly I tell you, in the renewal of all things, when the Son of Man sits on His glorious throne, you who have followed Me will also sit on twelve thrones, judging the twelve tribes of Israel.
29 ULB ስለ ስሜ ቤቶችን፣ ወንድሞችን፣ እኅቶችን፣ አባትን፣ እናትን፣ ልጆችን፣ ወይም ርስትን የተወ ሁሉ፣ መቶ እጥፍ ይቀበላል፣ የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል፡፡ BSB BSB: And everyone who has left houses or brothers or sisters or father or mother or wife or children or fields for the sake of My name will receive a hundredfold and will inherit eternal life.
30 ULB ነገር ግን አሁን ፊተኞች የሆኑ ብዙዎች ኋለኞች ይሆናሉ፤ ኋለኞች የሆኑ ብዙዎችም ፊተኞች ይሆናሉ፡፡ BSB BSB: But many who are first will be last, and the last will be first.