1 ULB ከዚያም ኢየሱስ ለሕዝቡና ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ሲል ተናገረ፤ BSB BSB: Then Jesus spoke to the crowds and to His disciples:
2 ULB "የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል፡፡ BSB BSB: “The scribes and Pharisees sit in Moses’ seat.
3 ULB ስለዚህ የሚያዝዙአችሁን ሁሉ አድርጉ፤ አክብሩትም፡፡ እነርሱ የሚያደርጉትን ግን አታደርጉ፤ ምክንያቱም እነርሱ ራሳቸው የሚናገሩትን አያደርጉትም፡፡ BSB BSB: So practice and observe everything they tell you. But do not do what they do, for they do not practice what they preach.
4 ULB ለመሸከም የሚያስቸግር ከባድ ሸክም አንሥተው በሰዎች ትከሻ ላይ ይጭናሉ፡፡ እነርሱ ራሳቸው ግን መሸከም ቀርቶ በጣታቸው ሊያነሡት እንኳ አይፈልጉም፡፡ BSB BSB: They tie up heavy, burdensome loads and lay them on men’s shoulders, but they themselves are not willing to lift a finger to move them.
5 ULB ሥራቸውን ሁሉ የሚያደርጉት በሰዎች ለመታየት ነው፤ አሸንክታባቸውን ያሰፋሉ፤ የልብሳቸውንም ዘርፍ ያስረዝማሉ፡፡ BSB BSB: All their deeds are done for men to see. They broaden their phylacteries and lengthen their tassels.
6 ULB ግብዣ ላይ የከበሬታ ቦታዎችንና በምኵራብ ውስጥ የተለየ መቀመጫ እንዲሰጣቸው ይፈልጋሉ፤ BSB BSB: They love the places of honor at banquets, the chief seats in the synagogues,
7 ULB በገበያ ቦታ ሰዎች የተለየ ክብር እንዲሰጧቸውና፣ 'መምህር ሆይ› በማለት እንዲጠሩአቸው ይፈልጋሉ፡፡ BSB BSB: the greetings in the marketplaces, and the title of ‘Rabbi’ by which they are addressed.
8 ULB እናንተ ግን ያላችሁ አንድ መምህር ብቻ ስለሆነና ሁላችሁም ወንድማማች ስለሆናችሁ ‹መምህር› ተብላችሁ አትጠሩ፡፡ BSB BSB: But you are not to be called ‘Rabbi,’ for you have one Teacher, and you are all brothers.
9 ULB በምድር ላይ ማንንም አባት ብላችሁ አትጥሩ፤ ምክንያቱም በሰማይ የሚኖር አንድ አባት ብቻ አላችሁ፡፡ BSB BSB: And do not call anyone on earth your father, for you have one Father, who is in heaven.
10 ULB ‹ሊቅም› ተብላችሁ አትጠሩ፤ ምክንያቱም ያላችሁ አንድ ሊቅ ብቻ ነው፤ እርሱም ክርስቶስ ነው፡፡ BSB BSB: Nor are you to be called instructors, for you have one Instructor, the Christ.
11 ULB ከእናንተ መካከል ታላቅ የሆነው አገልጋያችሁ ይሁን፡፡ BSB BSB: The greatest among you shall be your servant.
12 ULB ራሱን ከፍ የሚያደርግ ዝቅ ይላል፤ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ከፍ ይላል፡፡ BSB BSB: For whoever exalts himself will be humbled, and whoever humbles himself will be exalted.
13 ULB እናንተ፣ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ግን ወዮላችሁ! በሰዎች ፊት መንግሥተ ሰማይን ትዘጋላችሁ፡፡ እናንተ ራሳችሁ አትገቡበትም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ፡፡ BSB BSB: Woe to you, scribes and Pharisees, you hypocrites! You shut the kingdom of heaven in men’s faces. You yourselves do not enter, nor will you let in those who wish to enter.
14 ULB እናንተ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ለታይታ ረጅም ጸሎታችሁን በማድረግ የመበለቶችን ቤት ስለምትበሉ ወዮላችሁ! ስለዚህ የበለጠውን ፍርድ ትቀበላላችሁ፡፡ እናንተ ግብዞች የአይሁድ ሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! BSB BSB: Not in the BSB
15 ULB አንድን ሰው ተከታያችሁ ለማድረግ በባሕርና በምድር ትሄዳላችሁ፤ ተከታያችሁ ካደረጋችሁት በኋላ፣ ከእናንተ እጥፍ የሚከፋ የገሃነም ልጅ ታደርጉታላችሁ፡፡ BSB BSB: Woe to you, scribes and Pharisees, you hypocrites! You traverse land and sea to win a single convert, and when he becomes one, you make him twice as much a son of hell as you are.
16 ULB እናንተ ዐይነ ስውራን መሪዎች ወዮላችሁ፤ አንድ ሰው 'በቤተ መቅደሱ ቢምል ምንም ማለት አይደለም፤ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ባለው ወርቅ ቢምል ግን፣ በመሐላው ይጠመዳል' ትላላችሁ፡፡ BSB BSB: Woe to you, blind guides! You say, ‘If anyone swears by the temple, it means nothing; but if anyone swears by the gold of the temple, he is bound by his oath.’
17 ULB እናንተ የታወራችሁ ሞኞች፣ ለመሆኑ የትኛው ይበልጣል ወርቁ ወይስ ወርቁን የሚቀድሰው ቤተ መቅደሱ? BSB BSB: You blind fools! Which is greater: the gold, or the temple that makes it sacred?
18 ULB አንድ ሰው በመሠዊያው ቢምል ምንም ማለት አይደለም፤ መሠዊያው ላይ ባለው ስጦታ ቢምል ግን በመሐላው ይጠመዳል ትላላችሁ፡፡ BSB BSB: And you say, ‘If anyone swears by the altar, it means nothing; but if anyone swears by the gift on it, he is bound by his oath.’
19 ULB እናንተ ዕውሮች፤ ለመሆኑ የትኛው ይበልጣል ስጦታው ወይስ ስጦታውን የሚቀድሰው መሠዊያ? BSB BSB: You blind men! Which is greater: the gift, or the altar that makes it sacred?
20 ULB ስለዚህ በመሠዊያው የሚምል በመሠዊያውና እርሱ ላይ ባሉ ነገሮች ሁሉ ይምላል፡፡ BSB BSB: So then, he who swears by the altar swears by it and by everything on it.
21 ULB በቤተ መቅደሱ የሚምል በቤተ መቅደስና እርሱ ውስጥ በሚኖረው ይምላል፡፡ BSB BSB: And he who swears by the temple swears by it and by the One who dwells in it.
22 ULB በሰማይ የሚምል በእግዚአብሔር ዙፋንና በእርሱ ላይ በተቀመጠው ይምላል፡፡ BSB BSB: And he who swears by heaven swears by God’s throne and by the One who sits on it.
24 ULB እናንተ ዐይነ ስውራን መሪዎች፣ ትንኝን አውጥታችሁ ትጥላላችሁ፤ ግመልን ግን ትውጣላችሁ! BSB BSB: You blind guides! You strain out a gnat but swallow a camel.
25 ULB እናንተ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! የጽዋውንና የሳሕኑን ውጫዊ ክፍል ታጠራላችህ፤ ውስጡ ግን ቅሚያና ስስት ሞልቶበታል፡፡ BSB BSB: Woe to you, scribes and Pharisees, you hypocrites! You clean the outside of the cup and dish, but inside they are full of greed and self-indulgence.
26 ULB አንተ ዕውር ፈሪሳዊ፣ ውጫዊ አካሉም ንጹሕ እንዲሆን በመጀመሪያ የጽዋውንና የሳሕኑን ውስጥ አጽዳ፡፡ BSB BSB: Blind Pharisee! First clean the inside of the cup and dish, so that the outside may become clean as well.
28 ULB በተመሳሳይ መንገድ እናንተም ከውጭ ለሰዎች ጻድቃን ትመስላላችሁ፤ ውስጣችሁ ግን ግብዝነትና ርኲሰት ሞልቶበታል፡፡ BSB BSB: In the same way, on the outside you appear to be righteous, but on the inside you are full of hypocrisy and wickedness.
29 ULB እናንተ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! የነቢያትን መቃብር ስለምትሠሩ፣ የጻድቃንን መቃብር ስለምታስጌጡ፣ BSB BSB: Woe to you, scribes and Pharisees, you hypocrites! You build tombs for the prophets and decorate the monuments of the righteous.
30 ULB በአባቶቻችን ዘመን ኖረን ቢሆን ኖሮ፣ የነቢያትን ደም በማፍሰስ አንተባበራቸውም ነበር ትላላችሁ፡፡ BSB BSB: And you say, ‘If we had lived in the days of our fathers, we would not have been partners with them in shedding the blood of the prophets.’
31 ULB ስለሆነም የነቢያት ገዳይ ልጆች መሆናችሁን እናንተ ራሳችሁ ትመሰክራላችሁ፡፡ BSB BSB: So you testify against yourselves that you are the sons of those who murdered the prophets.
32 ULB እናንተ ራሳችሁም አባቶቻችሁ የጀመሩትን ኃጢአት ትፈጽማላችሁ፡፡ BSB BSB: Fill up, then, the measure of the sin of your fathers.
33 ULB እናንተ እባቦች፣ እናንተ የእፉኝት ልጆች፣ ከገሃነም ፍርድ እንዴት ታመልጣላችሁ? BSB BSB: You snakes! You brood of vipers! How will you escape the sentence of hell?
34 ULB ስለዚህ ነቢያትን፣ አስተዋይ ሰዎችንና የአይሁድ ሕግ መምህራንን ወደ እናንተ እልካለሁ፡፡ አንዳንዶቹን ትገድላላችሁ፣ ትሰቅላላችሁ፤ ሌሎቹን በምኵራቦቻችሁ ትገርፋላችሁ፣ ከከተማ ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፡፡ BSB BSB: Because of this, I am sending you prophets and wise men and teachers. Some of them you will kill and crucify, and others you will flog in your synagogues and persecute from town to town.
35 ULB ከጻድቁ ከአቤል አንሥቶ በቤተ መቅደሱና በመሠዊያው መካካል እስከ ገደላችሁት የበራክዩ ልጅ ዘካርያስ ደም ድረስ፣ በምድር ላይ በፈሰሰው ጻድቃን ደም ሁሉ ትጠየቃላችሁ፡፡ BSB BSB: And so upon you will come all the righteous blood shed on earth, from the blood of righteous Abel to the blood of Zechariah son of Berechiah, whom you murdered between the temple and the altar.
36 ULB እውነት እላችኋለሁ፤ እነዚህ ነገሮች ሁሉ በዚህ ትውልድ ላይ ይሆናሉ፡፡ BSB BSB: Truly I tell you, all these things will come upon this generation.
37 ULB ኢየሩሳሌም፣ ኢየሩሳሌም ሆይ፣ አንቺ ነቢያትን የምትገድዪ ወደ አንቺ የተላኩትን በድንጋይ የምትወግሪ! ዶሮ ጫጩቶችዋን በክንፎቿ ሥር እንደምትሰበስብ እኔም ልጆችሽን መሰብሰበ ብዙ ጊዜ ፈልጌ ነበር፤ እናንተ ግን አልፈለጋችሁም! BSB BSB: O Jerusalem, Jerusalem, who kills the prophets and stones those sent to her, how often I have longed to gather your children together, as a hen gathers her chicks under her wings, but you were unwilling!
38 ULB ስለሆነም ቤታችሁ ወና ሆኖ ይቀራል፡፡ BSB BSB: Look, your house is left to you desolate.
39 ULB 'በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው' እስክትሉ ድረስ ከአሁን ጀምሮ አታዩኝም እላችኋለሁ፡፡ BSB BSB: For I tell you that you will not see Me again until you say, ‘Blessed is He who comes in the name of the Lord.’”