3 ULB በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ እያለ፣ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ መጥተው፣ "እስቲ ንገረን፤ ይህ ሁሉ የሚሆነው መቼ ነው? የአንተ መምጣትና የዓለም መጨረሻስ ምልክቱ ምንድን ነው?" አሉት፡፡ BSB BSB: While Jesus was sitting on the Mount of Olives, the disciples came to Him privately. “Tell us,” they said, “when will these things happen, and what will be the sign of Your coming and of the end of the age?”
4 ULB ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፣ "ማንም እንዳያሳስታችሁ ተጠንቀቁ፡፡ BSB BSB: Jesus answered, “See to it that no one deceives you.
5 ULB ምክንያቱም ብዙዎች በስሜ ይመጣሉ፤ 'እኔ ክርስቶስ ነኝ' እያሉ ብዙዎችን ያሳስታሉ BSB BSB: For many will come in My name, claiming, ‘I am the Christ,’ and will deceive many.
7 ULB ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሣል፡፡ በተለያየ ቦታ ራብና የምድር መናወጥ ይሆናል፡፡ BSB BSB: Nation will rise against nation, and kingdom against kingdom. There will be famines and earthquakes in various places.
8 ULB እነዚሀ ሁሉ ግን የምጥ ጣር መጀመሪያ ብቻ ናቸው፡፡ BSB BSB: All these are the beginning of birth pains.
9 ULB ከዚያም ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል ይገድሏችኋልም፡፡ ስለ ስሜ ሕዝቦች ሁሉ ይጠሏችኋል፡፡ BSB BSB: Then they will deliver you over to be persecuted and killed, and you will be hated by all nations because of My name.
10 ULB ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ እርስ በርስ ይካካዳሉ፤ እርስ በርስ ይጠላላሉ፡፡ BSB BSB: At that time many will fall away and will betray and hate one another,
11 ULB ብዙ ሐሰተኛ ነቢያት ተነሥተው፣ ብዙዎችን ያሳስታሉ፡፡ BSB BSB: and many false prophets will arise and deceive many.
12 ULB ዐመፅ ስለሚበዛ የብዙዎች ፍቅር ይቀዘቅዛል፡፡ BSB BSB: Because of the multiplication of wickedness, the love of most will grow cold.
13 ULB እስከ መጨረሻ የሚታገሥ ግን ይድናል፡፡ BSB BSB: But the one who perseveres to the end will be saved.
14 ULB ለሕዝቦች ሁሉ ምስክር እንዲሆን የመንግሥቱ ወንጌል ለመላው ዓለም ይሰበካል፤ ከዚያም መጨረሻው ይመጣል፡፡ BSB BSB: And this gospel of the kingdom will be preached in all the world as a testimony to all nations, and then the end will come.
16 ULB በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፣ BSB BSB: then let those who are in Judea flee to the mountains.
17 ULB ጣራ ላይ ያለ ሰው በቤቱ ያለውን ምንም ነገር ከቤቱ ለመውሰድ አይመለስ፣ BSB BSB: Let no one on the housetop come down to retrieve anything from his house.
18 ULB በእርሻ ያለ ልብሱን ለመውሰድ አይመለስ፡፡ BSB BSB: And let no one in the field return for his cloak.
19 ULB ልጆች ላሉአቸውና ለሚያጠቡ እናቶች ግን ወዮላቸው! BSB BSB: How miserable those days will be for pregnant and nursing mothers!
20 ULB ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ፡፡ BSB BSB: Pray that your flight will not occur in the winter or on the Sabbath.
21 ULB ምክንያቱም ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስና ከዚያም በኋላ ፈጽሞ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናል፡፡ BSB BSB: For at that time there will be great tribulation, unseen from the beginning of the world until now, and never to be seen again.
22 ULB እነዚያ ቀኖች ባያጥሩ ኖሮ፣ ማንም ሥጋ ለባሽ አይድንም ነበር፤ ለተመረጡት ሲባል ግን እነዚያ ቀኖች ያጥራሉ፡፡ BSB BSB: If those days had not been cut short, nobody would be saved. But for the sake of the elect, those days will be cut short.
23 ULB ስለዚህ ማንም "እነሆ ክርስቶስ፣ እዚህ ነው" ወይም፣ 'ክርስቶስ እዚያ ነው' ቢላችሁ አትመኑ፡፡ BSB BSB: At that time, if anyone says to you, ‘Look, here is the Christ!’ or ‘There He is!’ do not believe it.
24 ULB ምክንያቱም ብዙዎችን ለማሳሳት ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት መጥተው ታላላቅ ምልክቶችንና ድንቆችን ያደርጋሉ፤ ከተቻለም የተመረጡትን እንኳ ያሳስታሉ፡፡ BSB BSB: For false Christs and false prophets will appear and perform great signs and wonders to deceive even the elect, if that were possible.
25 ULB ይህ ከመሆኑ በፊት አስቀድሜ ነግሬአችኋለሁ፡፡ BSB BSB: See, I have told you in advance.
26 ULB ስለዚህ፣ ‹ክርስቶስ በምድረ በዳ ነው› ቢሏችሁ ወደ ምድረ በዳ አትሂዱ ወይም ቤት ውስጥ ነው ቢሏችሁ አትመኑ፡፡ BSB BSB: So if they tell you, ‘There He is, in the wilderness,’ do not go out, or, ‘Here He is, in the inner rooms,’ do not believe it.
27 ULB መብረቅ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ በአንዴ እንደሚታይ የሰው ልጅ ሲመጣ እንደዚያው ይሆናል፡፡ BSB BSB: For just as the lightning comes from the east and flashes as far as the west, so will be the coming of the Son of Man.
28 ULB የሞተ እንስሳ ባለበት ሁሉ፣ በዚያ አሞሮች ይሰበሰባሉ፡፡ BSB BSB: Wherever there is a carcass, there the vultures will gather.
29 ULB ከእነዚህ የመከራ ቀኖች በኋላ ወዲያውኑ ፀሐይ ትጨልማለች፣ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም፤ ከዋክብት ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኅይላት ይናወጣሉ፡፡ BSB BSB: Immediately after the tribulation of those days: ‘The sun will be darkened, and the moon will not give its light; the stars will fall from the sky, and the powers of the heavens will be shaken.’
30 ULB ከዚያም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፤ የምድር ነገዶች ሁሉ አምርረው ያለቅሳሉ፡፡ የሰው ልጅንም በኀይልና በታላቅ ክብር ሲመጣ ያዩታል፡፡ BSB BSB: At that time the sign of the Son of Man will appear in heaven, and all the tribes of the earth will mourn. They will see the Son of Man coming on the clouds of heaven with power and great glory.
31 ULB መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፤ እነርሱም፣ ከአንድ የሰማይ ጫፍ እስከ ሌላው ጫፍ ድረስ ከአራቱም ነፋሳት ምርጦቹን ይሰበስቧቸዋል፡፡ BSB BSB: And He will send out His angels with a loud trumpet call, and they will gather His elect from the four winds, from one end of the heavens to the other.
33 ULB እናንተም እነዚህን ሁሉ ስታዩ እርሱ መቅረቡን፣ እንዲያውም በደጅ መሆኑን ዕወቁ፡፡ BSB BSB: So also, when you see all these things, you will know that He is near, right at the door.
38 ULB ከጥፋት ውሃ በፊት እንደ ነበረው ዘመን፣ ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባ ድረስ ይበሉና ይጠጡ፣ ያገቡና ይጋቡ ነበር። BSB BSB: For in the days before the flood, people were eating and drinking, marrying and giving in marriage, up to the day Noah entered the ark.
39 ULB ጐርፉ መጥቶ እስኪያጠፋቸው ድረስ ምንም አላወቁም፣ የሰው ልጅ ሲመጣም እንዲሁ ይሆናል፡፡ BSB BSB: And they were oblivious until the flood came and swept them all away. So will it be at the coming of the Son of Man.
40 ULB በዚያን ጊዜ ሁለት ሰዎች በዕርሻ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል ሌላው ይቀራል፡፡ BSB BSB: Two men will be in the field: one will be taken and the other left.
41 ULB ሁለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዷ ትወሰዳለች ሌላዋ ትቀራለች፡፡ BSB BSB: Two women will be grinding at the mill: one will be taken and the other left.
43 ULB ይህን ግን ዕወቁ፤ ሌባው በየትኛው ሰዓት እንደሚመጣ የቤቱ ባለቤት ቢያውቅ ኖሮ ይጠነቀቅ ነበር፤ ቤቱ አይዘረፍም ነበር፡፡ BSB BSB: But understand this: If the homeowner had known in which watch of the night the thief was coming, he would have kept watch and would not have let his house be broken into.
44 ULB የሰው ልጅ ባልጠበቃችሁት ሰዓት ስለሚመጣ እናንተም ብትሆኑ ተዘጋጅታችሁ መጠበቅ አለባችሁ፡፡ BSB BSB: For this reason, you also must be ready, because the Son of Man will come at an hour you do not expect.
45 ULB በተገቢው ጊዜ ለቤተ ሰቦቹ ምግባቸውን ለመስጠት ጌታው በቤቱ ላይ ኀላፊነት የሰጠው ታማኝና አስተዋይ አገልጋይ ማን ነው? BSB BSB: Who then is the faithful and wise servant, whom the master has put in charge of his household, to give the others their food at the proper time?
46 ULB ጌታው ሲመጣ ያንን እያደረገ የሚያገኘው አገልጋይ የተባረከ ነው፡፡ BSB BSB: Blessed is that servant whose master finds him doing so when he returns.
47 ULB እውነት እላችኋለሁ የምላችሁ፣ ጌታው ባለው ነገር ሁሉ ላይ ኀላፊ አድርጎ ይሾመዋል፡፡ BSB BSB: Truly I tell you, he will put him in charge of all his possessions.
48 ULB ይሁን እንጂ፣ አንድ ክፉ አገልጋይ በልቡ፣ ‹‹ጌታዬ ከመምጣት ዘግይቶአል ብሎ ቢያስብ፣ BSB BSB: But suppose that servant is wicked and says in his heart, ‘My master will be away a long time.’
49 ULB አገልጋይ ጓደኞቹን መደብደብና ከሰካራሞች ጋር መብላት መጠጣት ቢጀምር BSB BSB: And he begins to beat his fellow servants and to eat and drink with drunkards.
50 ULB የዚያ አገልጋይ ጌታ አገልጋዩ ባልጠበቀው ቀንና በማያውቀው ሰዓት ይመጣበታል፡፡ BSB BSB: The master of that servant will come on a day he does not expect and at an hour he does not anticipate.
51 ULB ጌታው ለሁለት ይሰነጥቀዋል፤ ዕጣ ፈንታውን ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፣ በዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል፡፡ BSB BSB: Then he will cut him to pieces and assign him a place with the hypocrites, where there will be weeping and gnashing of teeth.