1 ULB አንቺ የወታደር ከተማ ሰራዊትሽን አሰልፊ ከበባ ተደርጐብናልና የእስራኤልን ገዥ ጉንጩን በበትር ይመቱታል፡፡ BSB BSB: Now, O daughter of troops, mobilize your troops; for a siege is laid against us! With a rod they will strike the cheek of the judge of Israel.
3 ULB ስለዚህ ያማጠችው ልጅ እስክትወልድ ድረስ እግዚአብሔር ሕዝቡን ይተዋቸዋል የተቀሩት ወንድሞቹም ወደ እስራኤል ሕዝብ ይመለሳሉ፡፡ BSB BSB: Therefore Israel will be abandoned until she who is in labor has given birth; then the rest of His brothers will return to the children of Israel.
4 ULB በያህዌ ብርታት፣ በአምላኩ በያህዌ ስም ክብር ጸንቶ ይቆማል፤ መንጋውንም ይጠብቃል፡፡ በዚያ ጊዜ ታላቅነቱ እስከ ምድር ዳርቻ ስለሚደርስ ተደላድለው ይኖራሉ፡፡ BSB BSB: He will stand and shepherd His flock in the strength of the LORD, in the majestic name of the LORD His God. And they will dwell securely, for then His greatness will extend to the ends of the earth.
5 ULB እርሱ ሰላማችን ይሆናል፡፡ አሦራውያን ወደ ምድራችን ሲመጡ ወደ ምሽጐቻችንም ሲገሠግሡ ሰባት እረኞችን፣ እንዲሁም ስምንት መሪዎችን እናስነሣባቸዋልን፡፡ BSB BSB: And He will be our peace when Assyria invades our land and tramples our citadels. We will raise against it seven shepherds, even eight leaders of men.
6 ULB እነዚህ ሰዎች የአሦርን ምድር በሰይፍ፣ የናምሩዱንም ምድር እጃቸው ላይ ባለው ሰይፍ ይገዛሉ፡፡ ወደ ምድራችን ሲመጡ ወደ ድንበራችንም ሲገሠግሡ እርሱ ከአሦራውያን ይድነናል፡፡ BSB BSB: And they will rule the land of Assyria with the sword, and the land of Nimrod with the blade drawn. So He will deliver us when Assyria invades our land and marches into our borders.
7 ULB የያዕቆብ ትሩፍ በብዙ ሕዝብ መካከል ከያህዌ ዘንድ እንደሚወርድ ጠል፣ ሣር ላይ እንደሚጥል ካፊያ ሰውን እንደማይጠብቅ፣ በሰው ልጆችም እንደማይተማመን ሰው ይሆናል፡፡ BSB BSB: Then the remnant of Jacob will be in the midst of many peoples like dew from the LORD, like showers on the grass, which do not wait for man or linger for mankind.
8 ULB የያዕቆብ ትሩፍ በሕዝቦች መካከል፣ በብዙ ሕዝቦች መካከል ይሆናል፤ በዱር አራዊት መካከል እንዳለ አንበሳ፣ በበጐች መካከል እንዳለ አንበሳ ደቦል ይሆናል፡፡ በእግሩ እየረጋገጠ ይቦጫጭቃቸዋል፤ የሚያድናቸውም አይኖርም፡፡ BSB BSB: Then the remnant of Jacob will be among the nations, in the midst of many peoples, like a lion among the beasts of the forest, like a young lion among flocks of sheep, which tramples and tears as it passes through, with no one to rescue them.
9 ULB እጅህ በጠላቶችህ ላይ ከፍ ከፍ በማለት ያጠፋቸዋል፡፡ BSB BSB: Your hand will be lifted over your foes, and all your enemies will be cut off.
10 ULB በዚያ ቀን ይላል ያህዌ «ፈረሶቻችሁን ከመካከላችሁ አጠፋለሁ ሠረገሎቻችሁንም እደመስሳለሁ፡፡ BSB BSB: “In that day,” declares the LORD, “I will remove your horses from among you and wreck your chariots.
11 ULB የምድራችሁን ከተሞች አጠፋለሁ ምሽጐቻችሁንም ሁሉ አፈርሳለሁ፡፡ BSB BSB: I will remove the cities of your land and tear down all your strongholds.
12 ULB በምድራችሁ ያለውን ጥንቆላ አጠፋለሁ ከእንግዲህ አታሟርቱም፡፡ BSB BSB: I will cut the sorceries from your hand, and you will have no fortune-tellers.
13 ULB የተቀረጹ ምስሎቻችሁንና የድንጋይ ዐምዶቻችሁን ከመካከላችሁ አጠፋለሁ፡፡ ከእንግዲህ የእጆቻችሁን ሥራ አታመልኩም፡፡ BSB BSB: I will also cut off the carved images and sacred pillars from among you, so that you will no longer bow down to the work of your own hands.
14 ULB የአሼራ ምሰሶዋችሁን ከምድራችሁ እነቅላለሁ ከተሞቻችሁንም አጠፋለሁ፡፡ BSB BSB: I will root out the Asherah poles from your midst and demolish your cities.
15 ULB ያልታዘዙኝን ሕዝቦች በቀጣዬና በመዓቴ እበቀላሁ፡፡» BSB BSB: I will take vengeance in anger and wrath upon the nations that have not obeyed Me.”