1 ULB ራሱን ከሰው የሚለይ የራሱን ምኞት ይፈልጋል፣ ትክክለኛውንም ፍርድ ሁሉ ይቃወማል፡፡ BSB BSB: He who isolates himself pursues selfish desires; he rebels against all sound judgment.
2 ULB ሞኝ ሰው በማስተዋል ደስታን አያገኝም፣ በራሱ ልብ ውስጥ ያለውን ነገር በመግለጥ እንጂ፡፡ BSB BSB: A fool does not delight in understanding, but only in airing his opinions.
3 ULB ክፉ ሰው ሲመጣ፣ ንቀት ከእፍረትና ከስድብ ጋር አብረውት ይመጣሉ፡፡ BSB BSB: With a wicked man comes contempt as well, and shame is accompanied by disgrace.
4 ULB ከሰው አፍ የሚወጡ ቃላት ጥልቅ ውሃ ናቸው፤ የጥበብ ምንጭም የሚፈስ ወንዝ ነው፡፡ BSB BSB: The words of a man’s mouth are deep waters; the fountain of wisdom is a bubbling brook.
5 ULB ለክፉው ማድላት፣ ጽድቅን ለሚያደርጉም ፍትህን ማጉደል መልካም አይደለም፡፡ BSB BSB: Showing partiality to the wicked is not good, nor is depriving the innocent of justice.
6 ULB የሞኝ ከንፈሮች ጥልን ያመጡበታል፣ አፉም በትርን ትጠራለች፡፡ BSB BSB: A fool’s lips bring him strife, and his mouth invites a beating.
7 ULB የሞኝ አፍ መጥፊያው ነው፣ በከንፈሮቹም ራሱን ወጥመድ ውስጥ ይጥላል፡፡ BSB BSB: A fool’s mouth is his ruin, and his lips are a snare to his soul.
8 ULB የሐሜት ቃላት እንደ ጣፋጭ ጉርሻ ናቸው፣ ወደ ሰውነት ውስጣዊ ክፍሎች ጠልቀው ይገባሉ፡፡ BSB BSB: The words of a gossip are like choice morsels that go down into the inmost being.
9 ULB በስራው ችላ የሚልም ብዙውን የአጥፊ ሰው ወንድም ነው፡፡ BSB BSB: Whoever is slothful in his work is brother to him who destroys.
10 ULB የእግዚአብሔር ስም ጽኑ ግንብ ነው፤ ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ወደ እርሱ ሮጦ ይድናል፡፡ BSB BSB: The name of the LORD is a strong tower; the righteous run to it and are safe.
11 ULB የባለጸጋ ሐብት የእርሱ የተመሸገ ከተማ ነው፣ ሃሳቡም እንደ ረዥም ግንብ ነው፡፡ BSB BSB: A rich man’s wealth is his fortified city; it is like a high wall in his imagination.
12 ULB ከውድቀቱ በፊት የሰው ልብ ትዕቢተኛ ይሆናል፣ ትህትና ግን ክብርን ቀድሞ ይመጣል፡፡ BSB BSB: Before his downfall a man’s heart is proud, but humility comes before honor.
13 ULB ከማድመጡ በፊት የሚመልስ ሰው ሞኝነትና ዕፍረት ይሆንበታል፡፡ BSB BSB: He who answers a matter before he hears it—this is folly and disgrace to him.
14 ULB የሰው መንፈስ ሕመምን ትታገሳለች፣ የተሰበረን መንፈስ ግን ማን ሊሸከም ይችላል? BSB BSB: The spirit of a man can endure his sickness, but who can survive a broken spirit?
15 ULB የአስተዋይ ሰው ልብ እውቀትን ያገኛል፣ የጠቢብም ጆሮ ይፈልገዋል፡፡ BSB BSB: The heart of the discerning acquires knowledge, and the ear of the wise seeks it out.
16 ULB የሰው ስጦታ መንገዱን ትከፍትለታለች በተከበሩም ሰዎች ፊት ታቆመዋለች፡፡ BSB BSB: A man’s gift opens doors for him, and brings him before great men.
17 ULB ወደ ፍርድ ቀድሞ በመምጣት ጉዳዩን የሚያሰማ ጻድቅ ይመስላል፣ ይህ ግን የሚሆነው ተቀናቃኙ መጥቶ እስከሚጠይቀው ድረስ ነው፡፡ BSB BSB: The first to state his case seems right until another comes and cross-examines him.
18 ULB እጣ ማውጣት ክርክርን ያቆማል፣ ሃይለኛ ጠላቶችንም ትለያለች፡፡ BSB BSB: Casting the lot ends quarrels and separates strong opponents.
19 ULB የተበደለ ወንድምን መርታት ጠንካራ ከተማን ከማሸነፍ ይልቅ በጣም የከበደ ነው፣ ጠብም እንደ ግንብ ብረት ነው፡፡ BSB BSB: An offended brother is harder to win than a fortified city, and disputes are like the bars of a castle.
20 ULB የሰው ሆድ ከአፉ ፍሬ ይሞላል፤ በንፈሮቹም ምርት ይረካል፡፡ BSB BSB: From the fruit of his mouth a man’s belly is filled; with the harvest from his lips he is satisfied.
21 ULB ሞትና ሕይወት በምላስ ላይ ናቸው፣ የሚወዱትም ፍሬዋን ይበላሉ፡፡ BSB BSB: Life and death are in the power of the tongue, and those who love it will eat its fruit.
22 ULB ሚስትን ያገኘ መልካምን ነገር አግኝቷል፣ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ሞገስን አግኝቷል፡፡ BSB BSB: He who finds a wife finds a good thing and obtains favor from the LORD.
23 ULB ድሃ ሰው ምህረትን ይለምናል፣ ሃብታም ግን በማመናጨቅ ይመልሳል፡፡ BSB BSB: The poor man pleads for mercy, but the rich man answers harshly.
24 ULB ብዙ ጓደኞች ያለው ሰው በእነርሱ አማካኝነት ወደ ጥፋት ይመጣል፣ ከወንድም የቀረበ ጓደኛ ግን አለ፡፡ BSB BSB: A man of many companions may come to ruin, but there is a friend who stays closer than a brother.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.