1 ULB እነዚህ የይሁዳ ንጉስ፣ የሕዝቅያስ ሰዎች የቀዷቸው ተጨማሪ የሰለሞን ምሳሌዎች ናቸው፡፡ BSB BSB: These are additional proverbs of Solomon, which were copied by the men of Hezekiah king of Judah:
3 ULB ሰማያት ከፍ ያሉ እንደሆኑ፣ ምድርም ጥልቅ እንደሆነች ሁሉ፣ የነገስታት ልብም አይመረመርም፡፡ BSB BSB: As the heavens are high and the earth is deep, so the hearts of kings cannot be searched.
4 ULB ቆሻሻውን ከብር አስወግድ፣ የብረት ሰራተኛውም ብሩን ለእጅ ሙያው ሊጠቀምበት ይችላል፡፡ BSB BSB: Remove the dross from the silver, and a vessel for a silversmith will come forth.
5 ULB እንደዚሁ ክፉ ሰዎችን ከንጉስ ፊት አርቃቸው፣ ዙፋኑ ጽድቅን በማድረግ ይጸናል፡፡ BSB BSB: Remove the wicked from the king’s presence, and his throne will be established in righteousness.
6 ULB በንጉስ ፊት ራስህን ከፍ ከፍ አታድርግ፣ ለታላቅ ሰዎች መቆሚያ በተዘጋጀም ስፍራ ላይ አትቁም፡፡ BSB BSB: Do not exalt yourself in the presence of the king, and do not stand in the place of great men;
7 ULB በተከበሩ ሰዎች ፊት ከምትዋረድ ይልቅ፣ እርሱ “ወደዚህ ና” ቢልህ ይሻላል፡፡ ያየኸውን ነገርም፣ BSB BSB: for it is better to be told, “Come up here!” than to be demoted in the presence of the prince. Even what you have seen with your own eyes,
8 ULB ወደ ፍርድ ፈጥነህ አታምጣው፡፡ ጎረቤትህ ባሳፈረህ ጊዜ በመጨረሻ ምን ታርጋለህ? BSB BSB: do not bring hastily to court. Otherwise, what will you do in the end when your neighbor puts you to shame?
9 ULB ጉዳይህን በአንተና በጎረቤትህ መካከል ተከራከር፣ የሌላ ሰው ምስጢር ግን አታውጣ፣ BSB BSB: Argue your case with your neighbor without betraying another’s confidence,
10 ULB አለበለዚያ ግን አንተን የሰማ ሰው በአንተ ላይ ሃፍረትን ያመጣብሃል፣ ስለ አንተም ልትመልሰው የማትችለው መጥፎ ወሬ ይወራብሃል፡፡ BSB BSB: lest he who hears you bring shame upon you, and your infamy never go away.
11 ULB በጥንቃቄ የተመረጠ ቃል መናገር፣ በብር ላይ እንደተቀረጻ የወርቅ ንድፍ ነው፡፡ BSB BSB: A word fitly spoken is like apples of gold in settings of silver.
12 ULB ለሚሰማ ጆሮ የጥበበኛ ተግሳጽ እንደ ወርቅ ቀለበት፣ ከንጹህ ወርቅም እንደተሰራ ጌጥ ነው፡፡ BSB BSB: Like an earring of gold or an ornament of fine gold is a wise man’s rebuke to a listening ear.
13 ULB በምርት መሰብሰቢያ ወቅት እንዳለ የበረዶ ቅዝቃዜ ታማኝ መልዕክተኛ ለላኩት ሰዎች እንዲሁ ነው፤ የጌቶቹን ሕይወት ይመልሳል፡፡ BSB BSB: Like the cold of snow in the time of harvest is a trustworthy messenger to those who send him; he refreshes the soul of his masters.
14 ULB የማይሰጠውን ስጦታ እሰጣለሁ ብሎ የሚመካ ሰው ዝናብ እንደሌለው ደመናና ንፋስ ነው፡፡ BSB BSB: Like clouds and wind without rain is the man who boasts of gifts never given.
15 ULB በትዕግስት ገዢን እንዲለዝብ ማድረግ ይቻላል፣ መልካም ምላስም አጥንትን ትሰብራለች፡፡ BSB BSB: Through patience a ruler can be persuaded, and a gentle tongue can break a bone.
16 ULB ማር ካገኘህ፣ ለአንተ በቂ የሆነውን ብላ፣ አለበለዚያ ግን ከመጠን በላይ ከበላህ ትተፋዋለህ፡፡ BSB BSB: If you find honey, eat just what you need, lest you have too much and vomit it up.
17 ULB ወደ ጎረቤትህ ቤት እግር አታብዛ፣ ሊሰለችህና ሊጠላህ ይችላልና፡፡ BSB BSB: Seldom set foot in your neighbor’s house, lest he grow weary and hate you.
18 ULB በጎረቤቱ ላይ በሐሰት የሚመሰክር ሰው በጦርነት ላይ ጥቅም ላይ እንደሚውል ዱላ፣ ሰይፍ ወይም የተሳለ ቀስት ነው፡፡ BSB BSB: Like a club or sword or sharp arrow is a man who bears false witness against his neighbor.
19 ULB በችግር ጊዜ የታመንከው ወስላታ ሰው እንደ ተበላሸ ጥርስ ወይም እንደሚያነክስ እግር ነው፡፡ BSB BSB: Like a broken tooth or a foot out of joint is confidence in a faithless man in time of trouble.
20 ULB ላዘነ ልብ መዝሙር የሚዘምር፣ በብርድ ጊዜ ልብሱን እንደሚያወልቅ ወይም በሶዳ ላይ ኮምጣጤ እንደሚጨምር ነው፡፡ BSB BSB: Like one who removes a garment on a cold day or vinegar poured on a wound is one who sings songs to a heavy heart.
21 ULB ጠላትህ ቢራብ እንዲበላ ምግብ ስጠው፣ ቢጠማም እንዲጠጣ ውኃ ስጠው፣ BSB BSB: If your enemy is hungry, give him food to eat, and if he is thirsty, give him water to drink.
22 ULB በራሱ ላይ ፍም ትከምራለህና፣ እግዚአብሔርም ዋጋህን ይከፍልሃልና፡፡ BSB BSB: For in so doing, you will heap burning coals on his head, and the LORD will reward you.
23 ULB የሰሜን ንፋስ በእርግጠኝነት ዝናብን ይዞ እንደሚመጣ፣ ሚስጥርን የሚያባክን ሰው ሰዎችን ያስቆጣል፡፡ BSB BSB: As the north wind brings forth rain, so a backbiting tongue brings angry looks.
24 ULB ከጠበኛ ሴት ጋር በአንድ ቤት ከመኖር በጣራ ማእዘን ላይ ተጠግቶ መኖር ይሻላል፡፡ BSB BSB: Better to live on a corner of the roof than to share a house with a quarrelsome wife.
25 ULB ለተጠማ ሰው ቀዝቃዛ ውሃ እንደሚያረካው ሁሉ፣ ከሩቅ አገር የመጣ የምስራችም እንዲሁ ነው፡፡ BSB BSB: Like cold water to a weary soul is good news from a distant land.
26 ULB በክፉ ሰዎች ፊት የሚንበረከክ መልካም ሰው፣ እንደ ተበከለ ፈሳሽና እንደተበላሸ ምንጭ ነው፡፡ BSB BSB: Like a muddied spring or a polluted well is a righteous man who gives way to the wicked.
27 ULB እጅግ በጣም ብዙ ማር መብላት ጥሩ አይደለም፤ በክብር ላይ ክብር እንደመፈለግ ነው፡፡ BSB BSB: It is not good to eat too much honey or to search out one’s own glory.
28 ULB ራሱን መግዛት የማይችል ሰው እንደፈረሰችና ቅጥር እንደሌላት ከተማ ነው፡፡ BSB BSB: Like a city whose walls are broken down is a man who does not control his temper.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.