1 ULB በበጋ ጊዜ እንደሚወርድ በረዶና በመከር ጊዜ እንደሚዘንብ ዝናብ፣ ክብርም ለሞኝ ሰው አይገባውም፡፡ BSB BSB: Like snow in summer and rain at harvest, honor does not befit a fool.
2 ULB ድንቢጥ ከቦታ ቦታ እንደምትበርር፣ ጨረባም እንደምትሸመጥጥ፣ ያልተገባ እርግማን ማንም ላይ አይደርስም፡፡ BSB BSB: Like a fluttering sparrow or darting swallow, an undeserved curse does not come to rest.
3 ULB ጅራፍ ለፈረስ፣ ልጓምም ለአህያ እንደሆነ፣ በትርም ለሞኞች ጀርባ ነው፡፡ BSB BSB: A whip for the horse, a bridle for the donkey, and a rod for the backs of fools!
5 ULB ሞኝን እንደ ሞኝነቱ መልስለት፣ በሞኝነቱም ተባበረው፣ አለዚያ በዓይኖቹ ጥበበኛ የሆነ ይመስለዋል፡፡ BSB BSB: Answer a fool according to his folly, lest he become wise in his own eyes.
6 ULB በሞኝ ሰው እጅ መልዕክትን የሚልክ ሁሉ የራሱን እግር ይቆርጣል ሁከትንም ይጠጣል፡፡ BSB BSB: Like cutting off one’s own feet or drinking violence is the sending of a message by the hand of a fool.
7 ULB የሰለሉ የሽባ እግሮች በሞኝ አፍ እንዳለ ምሳሌ ናቸው፡፡ BSB BSB: Like lame legs hanging limp is a proverb in the mouth of a fool.
8 ULB ለሞኝ ክብር መስጠት ድንጋይን በወንጭፍ እንደ ማሰር ነው፡፡ BSB BSB: Like binding a stone into a sling is the giving of honor to a fool.
9 ULB በሰካራም እጅ ላይ ያለ እሾህ በሞኞች አፍ እንዳለ ምሳሌ ነው፡፡ BSB BSB: Like a thorn that goes into the hand of a drunkard is a proverb in the mouth of a fool.
10 ULB ሁሉንም ሰው የሚያቆስል ቀስተኛ፣ ሞኝን ወይም አላፊ አግዳሚውን እንደሚቀጥር ሰው ነው፡፡ BSB BSB: Like an archer who wounds at random is he who hires a fool or passerby.
11 ULB ውሻ ወደ ትውከቱ እንደሚመለስ፣ ሞኝነቱን የሚደጋግም ሞኝም እንዲሁ ነው፡፡ BSB BSB: As a dog returns to its vomit, so a fool repeats his folly.
12 ULB በራሱ ዓይን ጥበበኛ እንደሆነ የሚያስብን ሰው አይተሃልን? ከእርሱ ይልቅ ለሞኝ የተሻለ ተስፋ አለው፡፡ BSB BSB: Do you see a man who is wise in his own eyes? There is more hope for a fool than for him.
13 ULB ሰነፍ ሰው እንዲህ ይላል፣ “አንበሳ በመንገድ አለ! በውጭ በአውራ ጎዳና አንበሳ አለ፡፡” BSB BSB: The slacker says, “A lion is in the road! A fierce lion roams the public square!”
14 ULB በር በማጠፊያው ላይ እንደሚዞር፣ ሰነፍም በአልጋው ላይ ይዟዟራል፡፡ BSB BSB: As a door turns on its hinges, so the slacker turns on his bed.
15 ULB ሰነፍ ሰው እጁን ወደ ሳህኑ ያስገባል፣ ነገር ግን እጁን ወደ አፉ ለመመለስ ጉልበት የለውም፡፡ BSB BSB: The slacker buries his hand in the dish; it wearies him to bring it back to his mouth.
16 ULB ሰነፍ ሰው ማስተዋል ካላቸው ከሰባት ሰዎች የበለጠ ጥበበኛ እንደሆነ በራሱ ዓይን ያስባል፡፡ BSB BSB: The slacker is wiser in his own eyes than seven men who answer discreetly.
17 ULB የውሻን ጆሮ እንደሚይዝ ሰው፣ የራሱ ባልሆነ ጥል ላይ የሚገባ መንገድ አላፊ ሰውም እንዲሁ ነው፡፡ BSB BSB: Like one who grabs a dog by the ears is a passerby who meddles in a quarrel not his own.
18 ULB ተቀጣጣይ ቀስት እንደሚወራወር እብድ ሰው፣ BSB BSB: Like a madman shooting firebrands and deadly arrows,
19 ULB “የተናገርሁት እኮ ቀልዴን ነበር?” በማለት ጎረቤቱን የሚያታልል ሰው እንዲሁ ነው፡፡ BSB BSB: so is the man who deceives his neighbor and says, “I was only joking!”
20 ULB በእንጨት እጦት እሳት ይጠፋል፣ ሐሜት በሌለበትም ጥል ያቆማል፡፡ BSB BSB: Without wood, a fire goes out; without gossip, a conflict ceases.
21 ULB ከሰል ፍምን እንጨትም እሳትን እንደሚያቀጣጥል፣ ጠበኛ ሰውም ሁከትን ያቀጣጥላል፡፡ BSB BSB: Like charcoal for embers and wood for fire, so is a quarrelsome man for kindling strife.
22 ULB የሐሜት ቃላቶች እንደ ጣፋጭ ጉርሻ ናቸው፤ ወደ ውስጣዊ የሰውነት ክፍሎችም ይወርዳሉ፡፡ BSB BSB: The words of a gossip are like choice morsels that go down into the inmost being.
23 ULB እንሚያቃጥሉ ከንፈሮችና እንደ ክፉ ልብ በብር ፈሳሽ የተለበጠ የሸክላ ድስት እንዲሁ ነው፡፡ BSB BSB: Like glaze covering an earthen vessel are burning lips and a wicked heart.
24 ULB ሌሎችን የሚጠላ ሰው ስሜቱን በከንፈሮቹ ይሸነግላል፣ ተንኮሉን ግን በውስጡ ያኖራል፡፡ BSB BSB: A hateful man disguises himself with his speech, but he lays up deceit in his heart.
25 ULB ማራኪ የሆነ ንግግር ይናገራል፣ ነገር ግን አትመነው፣ በልቡ ውስጥ ሰባት ርኩሰቶች አሉና፡፡ BSB BSB: When he speaks graciously, do not believe him, for seven abominations fill his heart.
26 ULB ምንም እንኳ ጥላቻው በሽንገላ የተሸፈነ ቢሆንም፣ ክፋቱ ግን በጉባኤ ይገለጣል፡፡ BSB BSB: Though his hatred is concealed by deception, his wickedness will be exposed in the assembly.
27 ULB ጉድጓድን የሚቆፍር ሰው እርሱ ይገባበታል፣ ድንጋይንም የሚያንከባልል ተመልሶ በላዩ ላይ ይገለበጥበታል፡፡ BSB BSB: He who digs a pit will fall into it, and he who rolls a stone will have it roll back on him.
28 ULB ውሸታም ምላስ የጎዳቸውን ሰዎች ይጠላል፣ ሸንጋይ አፍም ጥፋትን ያመጣል፡፡ BSB BSB: A lying tongue hates those it crushes, and a flattering mouth causes ruin.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.