1 ULB ነገ በሚሆነው አትመካ፣ ቀኑ የሚያመጣው ምን እንደሆነ አታውቅምና፡፡ BSB BSB: Do not boast about tomorrow, for you do not know what a day may bring.
2 ULB ሌላ ያመስግንህ እንጂ በራስህ አፍ ራስህን አታመስግን፤ የማያውቅህ ሰው እንጂ የራስህ ከንፈሮች አያመስግኑህ፡፡ BSB BSB: Let another praise you, and not your own mouth—a stranger, and not your own lips.
3 ULB የድንጋይን ክብደትና የአሸዋንም ክብደት አስብ፣ የሞኝ ሰው ትንኮሳ ግን ከሁለቱም እጅግ የከበደ ነው፡፡ BSB BSB: A stone is heavy and sand is a burden, but aggravation from a fool outweighs them both.
4 ULB የንዴት ጨካኝነትና የቁጣ ጎርፍ አለ፣ በቅናት ፊት መቆም የሚችል ግን ማን ነው? BSB BSB: Wrath is cruel and anger is like a flood, but who can withstand jealousy?
5 ULB ከተሰወረ ፍቅር ይልቅ የተገለጠ ተግሳጽ ይሻላል፡፡ BSB BSB: Better an open rebuke than love that is concealed.
6 ULB የጓደኛ ማቁሰል የታመኑ ናቸው፣ ጠላት ግን ከመጠን በላይ ይስማል፡፡ BSB BSB: The wounds of a friend are faithful, but the kisses of an enemy are deceitful.
7 ULB በጣም ጠግቦ የበላ ሰው የማር ወለላንም አይቀበልም፣ ለራበው ሰው ግን ማንኛውም መራራ ነገር እንኳ ጣፋጭ ነው፡፡ BSB BSB: The soul that is full loathes honey, but to a hungry soul, any bitter thing is sweet.
8 ULB ከጎጆዋ ወጥታ የምትንከራተት ወፍ ከመኖሪያው አካባቢ ወጥቶ እንደሚባዝን ሰው ናት፡፡ BSB BSB: Like a bird that strays from its nest is a man who wanders from his home.
9 ULB ሽቶና እጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ፣ የጓደኛ ጣፋጭነት ግን ከምክሩ ይበልጣል፡፡ BSB BSB: Oil and incense bring joy to the heart, and the counsel of a friend is sweetness to the soul.
10 ULB በችግርህ ጊዜ ጓደኛህንና የጓደኛህን አባት ትተህ ወደ ወንድምህ ቤት አትሂድ፡፡ በቅርብ ያለ ወዳጅ በሩቅ ካለ ወንድም ይሻላልና፡፡ BSB BSB: Do not forsake your friend or your father’s friend, and do not go to your brother’s house in the day of your calamity; better a neighbor nearby than a brother far away.
11 ULB ልጄ ሆይ፣ ጥበበኛ ሁን፣ ልቤንም ደስ አሰኛት፤ በዚያን ጊዜ ለሚያፌዝብኝ ሰው እኔ መልስ እሰጣለሁ፡፡ BSB BSB: Be wise, my son, and bring joy to my heart, so that I can answer him who taunts me.
12 ULB ጥንቁቅ ሰው ችግር ሲያይ ራሱን ይሸሽጋል፣ አላዋቂዎች ግን ቀድመው ሄደው በችግሩ ምክንያት ይጎዳሉ፡፡ BSB BSB: The prudent see danger and take cover, but the simple keep going and pay the penalty.
13 ULB ለማይታወቅ ሰው ብድር በዋስትና ገንዘብ ያስያዘውን ሰው ልብስ ውሰድበት፤ ዝሙት ለምትፈጽም ሴት ዋስትና አስይዞ ከሆነ ውሰድበት፡፡ BSB BSB: Take the garment of him who posts security for a stranger; get collateral if it is for a foreigner.
14 ULB ጎረቤቱን በማለዳ ድምጹን በጣም ከፍ አድርጎ የሚባርክ ሰው፣ ባርኮቱ እንደ እርግማን ይቆጠራል! BSB BSB: If one blesses his neighbor with a loud voice early in the morning, it will be counted to him as a curse.
15 ULB ጠበኛ ሚስት በዝናብ ቀን እንደማያቋርጥ ነጠብጣብ ናት፤ BSB BSB: A constant dripping on a rainy day and a contentious woman are alike—
16 ULB እሷን ማቆም ንፋስን እንደማቆም ወይም ዘይትን በቀኝ እጅህ ለመጨበጥ እንደ መሞከር ነው፡፡ BSB BSB: restraining her is like holding back the wind or grasping oil with one’s right hand.
17 ULB ብረት ብረትን ይስለዋል፤ በተመሳሳይ መንገድ ሰው ጓደኛውን ይስለዋል፡፡ BSB BSB: As iron sharpens iron, so one man sharpens another.
18 ULB የበለስ ዛፍ የሚጠብቅ ፍሬውን ይበላል፣ ጌታውንም የሚጠብቅ ይከብራል፡፡ BSB BSB: Whoever tends a fig tree will eat its fruit, and he who looks after his master will be honored.
19 ULB ውኃ የሰውን ፊት እንደሚያሳይ፣ የሰው ልብ ሰውየውን ያሳያል፡፡ BSB BSB: As water reflects the face, so the heart reflects the true man.
20 ULB ሲዖልና የሙታን ዓለም መቼም እንደማይጠግቡ፣ የሰውም ዓይኖች መቼም አይጠግቡም፡፡ BSB BSB: Sheol and Abaddon are never satisfied; so the eyes of man are never satisfied.
21 ULB ማቅለጫ ለብር ከውርም ለወርቅ ነው፣ ሰውም በሚመሰገንበት ጊዜ ይፈተናል፡፡ BSB BSB: A crucible for silver and a furnace for gold, but a man is tested by the praise accorded him.
22 ULB ሰነፍን ከእህል ጋር በዘነዘና ብትወቅጠውም፣ ሞኝነቱ ግን እርሱን አይለቀውም፡፡ BSB BSB: Though you grind a fool like grain with mortar and a pestle, yet his folly will not depart from him.
23 ULB የመንጋህን ሁኔታ በእርግጠኝነት እወቅ፣ ስለ ከብቶችህም ግድ ይበልህ፣ BSB BSB: Be sure to know the state of your flocks, and pay close attention to your herds;
24 ULB ሐብት ለዘላለም አይኖርምና፡፡ ዘውድ ለትውልድ ሁሉ ይጸናልን? BSB BSB: for riches are not forever, nor does a crown endure to every generation.
25 ULB የነበረው ሳር ጠፍቶ፣ አዲሱ ቡቃያ አድጎ ሲታይ፣ በተራሮች ደግሞ ለከብቶች የሚሆን መብል ተሰብስቦ ይገባል፡፡ BSB BSB: When hay is removed and new growth appears and the grass from the hills is gathered,
26 ULB ለልብስህ የሚሆን ከበጎች ታገኛለህ፣ ለእርሻህ ዋጋ የሚሆን ደግሞ ከፍየሎችህ ታገኛለህ፡፡ BSB BSB: the lambs will provide you with clothing, and the goats with the price of a field.
27 ULB ለአንተና ለቤተሰብህ መብል፣ ሴት አገልጋዮችህንም ለመመገብ የሚበቃ የፍየሎች ወተት ይኖራል፡፡ BSB BSB: You will have plenty of goats’ milk to feed you—food for your household and nourishment for your maidservants.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.