1 ULB ኃጢአተኛ ማንም ሳያባርረው ይሸሻል፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን እንደ አንበሳ ደፋር ናቸው፡፡ BSB BSB: The wicked flee when no one pursues, but the righteous are as bold as a lion.
2 ULB በአገር አመጽ ምክንያት ብዙ ገዢዎች አሏት፣ ማስተዋልና እውቀት ባለው ሰው ግን፣ አገር ለረዥም ዘመን ትቆያለች፡፡ BSB BSB: A land in rebellion has many rulers, but a man of understanding and knowledge maintains order.
3 ULB ድሃ ሆኖ ሌሎች ድሆችን የሚያስጨንቅ ሰው፣ ሰብልን እንሚያጠፋ ዶፍ ዝናብ ነው፡፡ BSB BSB: A destitute leader who oppresses the poor is like a driving rain that leaves no food.
4 ULB ሕግን የሚተዉ ሰዎች ክፉዎችን ያመሰግናሉ፣ ሕግን የሚጠብቁ ግን ከእነርሱ ጋር ይዋጋሉ፡፡ BSB BSB: Those who forsake the law praise the wicked, but those who keep the law resist them.
5 ULB ክፉ ሰዎች ፍትህን አያውቁም፣ እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ግን ሁሉን ነገር ያውቃሉ፡፡ BSB BSB: Evil men do not understand justice, but those who seek the LORD comprehend fully.
6 ULB በመንገዱ ጠማማ ከሆነ ባለጠጋ ይልቅ፣ በሐቀኝነቱ የሚራመድ ድሃ ሰው ይሻላል፡፡ BSB BSB: Better a poor man who walks with integrity than a rich man whose ways are perverse.
7 ULB ሕግን የሚጠብቅ ማስተዋል ያለው ልጅ ነው፣ የሆዳሞች ጓደኛ ግን አባቱን ያሳፍራል፡፡ BSB BSB: A discerning son keeps the law, but a companion of gluttons disgraces his father.
8 ULB ከፍተኛ ወለድ በመሰብሰብ ሀብቱን የሚያከማች ለድሀዎች ለሚራራ ለሌላ ሰው ሀብቱን ይሰበሰብለታል፡፡ BSB BSB: He who increases his wealth by interest and usury lays it up for one who is kind to the poor.
9 ULB አንድ ሰው ሕግን ከማድመጥ ጆሮውን የሚያዞር ከሆነ፣ ጸሎቱ እንኳ የተጠላ ነው፡፡ BSB BSB: Whoever turns his ear away from hearing the law, even his prayer is detestable.
10 ULB ቅኑን ሰው ወደ ክፋት መንገድ የሚመራ ሁሉ ራሱ በቆፈረው ጉድጓድ ይገባል፣ ንጹሐን ግን መልካምን ነገር ይወርሳሉ፡፡ BSB BSB: He who leads the upright along the path of evil will fall into his own pit, but the blameless will inherit what is good.
11 ULB ባለጠጋ ሰው በራሱ ዓይኖች ጥበበኛ ሊሆን ይችላል፣ አስተዋይ የሆነ ድሃ ሰው ግን እርሱን ይመረምረዋል፡፡ BSB BSB: A rich man is wise in his own eyes, but a poor man with discernment sees through him.
12 ULB ጽድቅን የሚያደርጉ ድል በሚያገኙበት ጊዜ፣ ታላቅ ክብር አለ፣ ክፉዎች በሚነሱበት ጊዜ ግን ሰዎች ራሳቸውን ይሸሽጋሉ፡፡ BSB BSB: When the righteous triumph, there is great glory, but when the wicked rise, men hide themselves.
13 ULB ኃጢአቱን የሚሸሽግ አይሳካለትም፣ የሚናዘዝና የሚተወው ግን ምህረትን ያገኛል፡፡ BSB BSB: He who conceals his sins will not prosper, but whoever confesses and renounces them will find mercy.
14 ULB ዘወትር እግዚአብሔርን እየፈራ የሚኖር ሰው ደስተኛ ነው፣ ልቡን የሚያደነድን ግን ወደ መከራ ይወድቃል፡፡ BSB BSB: Blessed is the man who is always reverent, but he who hardens his heart falls into trouble.
15 ULB እንደሚያገሳ አንበሳ ወይም እንደ ተቆጣ ድብ በድሆች ላይ የሚገዛ ክፉ ገዥም እንዲሁ ነው፡፡ BSB BSB: Like a roaring lion or a charging bear is a wicked ruler over a helpless people.
16 ULB ማስተዋል የሌለው ገዥ በጭካኔ የሚያስጨንቅ ነው፣ ማታለልን የሚጠላ ግን እድሜውን ያረዝማል፡፡ BSB BSB: A leader who lacks judgment is also a great oppressor, but he who hates dishonest profit will prolong his days.
17 ULB አንድ ሰው የሌላውን ደም በማፍሰሱ ምክንያት በደለኛ ከሆነ፣ እስከ ሞቱ ቀን ድረስ ኮብላይ ይሆናል፣ ማንም ሰው አይረዳውም፡፡ BSB BSB: A man burdened by bloodguilt will flee into the Pit; let no one support him.
18 ULB በሐቀኝነት የሚራመድ ሰው በደህና ይጠበቃል፣ መንገዱ በጠማማነት የተሞላ ግን በድንገት ይወድቃል፡፡ BSB BSB: He who walks with integrity will be kept safe, but whoever is perverse in his ways will suddenly fall.
19 ULB መሬቱን የሚያርስ ሰው ብዙ መብል ይኖረዋል፣ የማይጠቅም ሞያ የሚከተል ግን እጅግ በጣም ይደኸያል፡፡ BSB BSB: The one who works his land will have plenty of food, but whoever chases fantasies will have his fill of poverty.
20 ULB ታማኝ ሰው ታላቅ በረከት ያገኛል፣ በጥድፊያ ሃብታም የሆነ ግን ሳይቀጣ አይቀርም፡፡ BSB BSB: A faithful man will abound with blessings, but one eager to be rich will not go unpunished.
21 ULB አድልዎን ማሳየት መልካም አይደለም፣ ነገር ግን ለቁራጭ ዳቦ ሲል ሰው ስህተትን ይሰራል፡፡ BSB BSB: To show partiality is not good, yet a man will do wrong for a piece of bread.
22 ULB ስስታም ሰው ሐብትን ያሳድዳል፣ ድህነት በላዩ ላይ እንደሚመጣ ግን አያውቅም፡፡ BSB BSB: A stingy man hastens after wealth and does not know that poverty awaits him.
23 ULB ሰውን በምላሱ ከሚያሞግስ ይልቅ የሚገስጽ ሰው በኋላ ውሎ አድሮ ከገሰጸው ሰው ብዙ ሞገስ ያገኛል፡፡ BSB BSB: He who rebukes a man will later find more favor than one who flatters with his tongue.
24 ULB አባቱንና እናቱን ሰርቆ “ኃጢአት አይደለም” የሚል ሰው የአጥፊ ተባባሪ ነው፡፡ BSB BSB: He who robs his father or mother, saying, “It is not wrong,” is a companion to the man who destroys.
25 ULB ስግብግብ ሰው ግጭትን ያነሳሳል፣ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን ይባረካል፡፡ BSB BSB: A greedy man stirs up strife, but he who trusts in the LORD will prosper.
26 ULB በራሱ ልብ የሚታመን ሰው ሞኝ ነው፣ በጥበብ የሚራመድ ግን ከአደጋ ይርቃል፡፡ BSB BSB: He who trusts in himself is a fool, but one who walks in wisdom will be safe.
27 ULB ለድሃ የሚሰጥ ምንም ነገር አይጎድልበትም፣ በድሆች ላይ ዓይኖቹን የሚከድን ሰው ግን ብዙ እርግማን ይቀበላል፡፡ BSB BSB: Whoever gives to the poor will not be in need, but he who hides his eyes will receive many curses.
28 ULB ክፉ ሰዎች ሲነሱ፣ ሰዎች ራሳቸውን ይሸሽጋሉ፣ ክፉ ሰዎች ሲጠፉ ግን፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ይበዛሉ፡፡ BSB BSB: When the wicked come to power, people hide themselves; but when they perish, the righteous flourish.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.