1 ULB ብዙ ተግሳጽን ተቀብሎ አንገቱን ያደነደነ ሰው እንደማይድን ሆኖ በቅጽበት ይሰበራል፡፡ BSB BSB: A man who remains stiff-necked after much reproof will suddenly be shattered beyond recovery.
2 ULB ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ሲበዙ፣ ሕዝብ ደስ ይለዋል፣ ክፉ ሰው ገዢ ሲሆን ግን ሕዝብ ያቃስታል፡፡ BSB BSB: When the righteous flourish, the people rejoice, but when the wicked rule, the people groan.
3 ULB ጥበብን የሚወድ ሁሉ አባቱን ደስ ያሰኛል፣ አመንዝራዎች ወዳጅ ግን ሀብቱን ያጠፋል፡፡ BSB BSB: A man who loves wisdom brings joy to his father, but a companion of prostitutes squanders his wealth.
4 ULB ንጉስ አገሩን በፍትህ ያጸናል፣ ጉቦን የሚፈልግ ግን ያፈራርሳታል፡፡ BSB BSB: By justice a king brings stability to the land, but a man who exacts tribute demolishes it.
5 ULB ጎረቤቱን የሚሸነግል ሰው ለገዛ እግሩ መረብ እየዘረጋ ነው፡፡ BSB BSB: A man who flatters his neighbor spreads a net for his feet.
6 ULB ክፉ ሰው በራሱ ኃጢአት በወጥመድ ይያዛል፣ ጽድቅን የሚያደርግ ግን ይዘምራል፣ ይደሰታልም፡፡ BSB BSB: An evil man is caught by his own sin, but a righteous one sings and rejoices.
7 ULB ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ለድሆች ፍትሕ ይጨነቃል፤ ክፉ ሰው ግን እንዲህ ዓይነት እውቀት የለውም፡፡ BSB BSB: The righteous consider the cause of the poor, but the wicked have no regard for such concerns.
8 ULB ፌዘኞች ከተማን ያቃጥላሉ፣ ጥበበኞች ግን ቁጣን ይመልሳሉ፡፡ BSB BSB: Mockers inflame a city, but the wise turn away anger.
9 ULB ጥበበኛ ሰው ከሞኝ ጋር በሚከራከርበት ጊዜ፣ ሞኝ ይቆጣል ይስቃልም፣ እረፍትም አይኖርም፡፡ BSB BSB: If a wise man goes to court with a fool, there will be raving and laughing with no resolution.
10 ULB ደም የተጠማ ሰው ንጹሐንን ይጠላሉ፣ ቅን የሆነውንም ሕይወት ለማጥፋት ይፈልጋሉ፡፡ BSB BSB: Men of bloodshed hate a blameless man, but the upright care for his life.
11 ULB ሞኝ ቁጣውን ሁሉ ይገልጣል፣ ጥበበኛ ሰው ግን ቁጣውን ይቆጣጠራል፣ ራሱንም ያረጋጋል፡፡ BSB BSB: A fool vents all his anger, but a wise man holds it back.
12 ULB ገዢ ለሐሰተኛ ወሬ ትኩረት የሚሰጥ ከሆነ፣ ሹማምንቶቹ ሁሉ ክፉ ይሆናሉ፡፡ BSB BSB: If a ruler listens to lies, all his officials will be wicked.
13 ULB ድሃና ጨቋኝን አንድ የሚያደርጋቸው አለ፣ እግዚአብሔር ለሁለቱም የዓይን ብርሃንን ሰጥቷቸዋልና፡፡ BSB BSB: The poor man and the oppressor have this in common: The LORD gives light to the eyes of both.
14 ULB ንጉስ ለድሃ በእውነት ከፈረደ፣ ዙፋኑ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል፡፡ BSB BSB: A king who judges the poor with fairness—his throne will be established forever.
15 ULB በትርና ተግሳጽ ጥበብን ይሰጣሉ፣ ያልተቀጣ ልጅ ግን እናቱን ያሳፍራል፡፡ BSB BSB: A rod of correction imparts wisdom, but a child left to himself disgraces his mother.
16 ULB ክፉ ሰዎች ስልጣን ሲይዙ፣ አመጸኝነት ይጨምራል፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን የክፉዎችን ውድቀት ያያሉ፡፡ BSB BSB: When the wicked thrive, rebellion increases; but the righteous will see their downfall.
17 ULB ልጅህን ቅጣው እረፍትም ይሰጥሃል፤ ለሕይወትህም ደስታን ያመጣል፡፡ BSB BSB: Discipline your son, and he will give you rest; he will bring delight to your soul.
18 ULB ትንቢታዊ ራዕይ በሌለበት ሕዝብ መረን ይሆናል፣ ሕግን የሚጠብቅ ግን የተባረከ ነው፡፡ BSB BSB: Where there is no vision, the people cast off restraint; but blessed is he who keeps the Law.
19 ULB አገልጋይ በቃል አይታረምም፣ ቢገባውም ምላሽ አይሰጥም፡፡ BSB BSB: A servant cannot be corrected by words alone; though he understands, he will not respond.
20 ULB በቃሎቹ የሚቸኩለውን ሰው ተመልክተሃል? ከእርሱ ይልቅ ለሞኝ የበለጠ ተስፋ አለው፡፡ BSB BSB: Do you see a man who speaks in haste? There is more hope for a fool than for him.
21 ULB አገልጋዩን ከወጣትነቱ ጀምሮ የሚያሞላቅቅ፣ በመጨረሻ ችግር ይገጥመዋል፡፡ BSB BSB: A servant pampered from his youth will bring grief in the end.
22 ULB ቁጡ ሰው ሁከትን ያነሳሳል፣ ቁጣ የሞላበትም ሰው ብዙ ኃጢአቶችን ይሰራል፡፡ BSB BSB: An angry man stirs up dissension, and a hot-tempered man abounds in transgression.
23 ULB የሰው ትዕቢት ያዋርደዋል፣ ትሁት መንፈስ ያለው ግን ይከበራል፡፡ BSB BSB: A man’s pride will bring him low, but a humble spirit will obtain honor.
24 ULB ከሌባ ጋር የሚካፈል ሰው ሕይወቱን ይጠላል፤ እርግማንን ይሰማል መልስ ግን አይሰጥም፡፡ BSB BSB: A partner to a thief hates his own soul; he receives the oath but does not testify.
25 ULB ሰውን መፍራት ወጥመድ ውስጥ ይከትታል፣ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን ይጠበቃል፡፡ BSB BSB: The fear of man is a snare, but whoever trusts in the LORD is set securely on high.
26 ULB ብዙዎች የገዢን ፊት ይሻሉ፣ ፍትህ ለሰው የሚመጣው ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፡፡ BSB BSB: Many seek the ruler’s favor, but a man receives justice from the LORD.
27 ULB ፍትህን የሚያጓድል ሰው ጽድቅን በሚያደርጉ ሰዎች ፊት የተጠላ ነው፣ መንገዱ ቅን የሆነ ሰው ግን በክፉዎች የተጠላ ነው፡፡ BSB BSB: An unjust man is detestable to the righteous, and one whose way is upright is detestable to the wicked.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.