3 ULB ክፉዎች ሲሳካላቸው ዐይቼ ቅናት አድሮብኝ ነበር፡፡ BSB BSB: For I envied the arrogant when I saw the prosperity of the wicked.
4 ULB እስኪሞቱ ድረስ ሕመም አያውቃቸውም ሰውነታቸውም ጤነኛና ጠንካራ ነው፡፡ BSB BSB: They have no struggle in their death; their bodies are well-fed.
5 ULB እንደ ሌሎች ሰዎች አይጨነቁም በሌሎች ላይ የሚደርሰው ስቃይ እነርሱ ላይ አይደርስም፡፡ BSB BSB: They are free of the burdens others carry; they are not afflicted like other men.
6 ULB ትዕቢት የአንገት ጌጣቸው ነው ግፍን እንደ ልብስ ለብሰውታል፡፡ BSB BSB: Therefore pride is their necklace; a garment of violence covers them.
7 ULB የሰባ ዐይናቸውም ይጉረጠርጣል፣ ልባቸው ክፉ ሐሳብ ያፈልቃል፡፡ BSB BSB: From their prosperity proceeds iniquity; the imaginations of their hearts run wild.
8 ULB በፌዝና በክፋት ይናገራሉ በእብሪት ተነሣሥተው ሌሎች ላይ ይዝታሉ፡፡ BSB BSB: They mock and speak with malice; with arrogance they threaten oppression.
9 ULB አፋቸውን በሰማይ ያላቅቃሉ አንደበታቸውም ምድርን ያካልላል፡፡ BSB BSB: They set their mouths against the heavens, and their tongues strut across the earth.
10 ULB ስለዚህ ሕዝቡ ወደ እነርሱ ይመለሳል ውሃቸውንም በገፍ ይጠጣሉ፡፡ BSB BSB: So their people return to this place and drink up waters in abundance.
11 ULB «እግዚአብሔር እንዴት ሊያውቅ ይችላል በልዑልስ ዘንድ ዕውቀት አለ?» ይላሉ፡፡ BSB BSB: The wicked say, “How can God know? Does the Most High have knowledge?”
12 ULB እንግዲህ ክፉዎች እንደዚህ ናቸው ሁልጊዜ እንደ ተዝናኑ ናቸው በሀብት ላይ ሀብት ይጨምራሉ፡፡ BSB BSB: Behold, these are the wicked—always carefree as they increase their wealth.
13 ULB ለካ ልቤን ንጹሕ ያደረግሁት እኔን በየዋህነት የታጠብሁት በከንቱ ኖሮአል! BSB BSB: Surely in vain I have kept my heart pure; in innocence I have washed my hands.
14 ULB ቀኑን ሙሉ ተሰቃየሁ በየማለዳውም ተቀጣሁ፡፡ BSB BSB: For I am afflicted all day long and punished every morning.
15 ULB እኔ እንደዚህ እናገራለሁ ብል ኖሮ የልጆችህን ትውልድ በከዳሁ ነበር፡፡ BSB BSB: If I had said, “I will speak this way,” then I would have betrayed Your children.
17 ULB ወደ መቅደስህ እስክገባ ድረስ ምንም ማወቅ አልቻልሁም በኋላ ግን በክፉዎች ላይ ምን እንደሚደርስባቸው ተረዳሁ፡፡ BSB BSB: until I entered God’s sanctuary; then I discerned their end.
18 ULB በእርግጥ በሚያዳልጥ ስፍራ አኑረሃቸዋል ወድቀው እንዲጠፉም አድርገሃል፡፡ BSB BSB: Surely You set them on slick ground; You cast them down into ruin.
19 ULB እንዴት ፈጥነው በቅጽበት ጠፉ! በከባድ ድንጋጤ ፈጽመው ወደሙ፡፡ BSB BSB: How suddenly they are laid waste, completely swept away by terrors!
20 ULB ሰው ከሕልሙ ሲነቃ እንደሚሆነው፣ ጌታ ሆይ፣ አንተም በምትነሣበት ጊዜ፣ እነርሱ በማለዳ እንደሚረሳ ሕልም ይሆናሉ፡፡ BSB BSB: Like one waking from a dream, so You, O Lord, awaken and despise their form.
21 ULB ልቤ በጣም ተማረረች፣ እኔም እጅግ ቆሰልሁ፡፡ BSB BSB: When my heart was grieved and I was pierced within,
22 ULB ስሜት የሌለው አላዋቂ ሆንሁ በፊትህም እንደ እንስሳ ሆንሁ፡፡ BSB BSB: I was senseless and ignorant; I was a brute beast before You.
23 ULB ይህም ሆኖ ዘወትር ከአንተ ጋር ነኝ አንተም ቀኝ እጄን ይዘኸኛል፡፡ BSB BSB: Yet I am always with You; You hold my right hand.
24 ULB በምክርህ ትመራኛለህ በመጨረሻም በክብር ትቀበለኛለህ፡፡ BSB BSB: You guide me with Your counsel, and later receive me in glory.
25 ULB በሰማይ ከአንተ በቀር ማን አለኝ? በምድርም ከአንተ ሌላ የምፈልገው የለኝም፡፡ BSB BSB: Whom have I in heaven but You? And on earth I desire no one besides You.
26 ULB ሥጋዬና ልቤ ደከሙ እግዚአብሔር ግን ለዘላለም የልቤ ብርታትና አለኝታ ነው፡፡ BSB BSB: My flesh and my heart may fail, but God is the strength of my heart and my portion forever.
27 ULB እነሆ፣ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉ ለአንተ ያልታመኑትንም ታጠፋቸዋለህ፡፡ BSB BSB: Those far from You will surely perish; You destroy all who are unfaithful to You.
28 ULB ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፣ ጌታ ያህዌን መጠጊያዬ አድርጌዋለሁ ሥራህንም ሁሉ እናገራለሁ፡፡ BSB BSB: But as for me, it is good to draw near to God. I have made the Lord GOD my refuge, that I may proclaim all Your works.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.