1 ULB ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ ይሰማኝ ዘንድ ድምፄን ከፍ አድርጌ እግዚአብሔርን እጠራለሁ፡፡ BSB BSB: For the choirmaster. According to Jeduthun. A Psalm of Asaph. I cried out to God; I cried aloud to God to hear me.
2 ULB በመከራዬ ቀን ጌታን ፈለግሁት በሌሊትም ያለ ዕረፍት እጆቼን ዘረጋሁ፤ ነፍሴ አልጽናና አለች፡፡ BSB BSB: In the day of trouble I sought the Lord; through the night my outstretched hands did not grow weary; my soul refused to be comforted.
3 ULB አምላኬ ሆይ፣ አንተን ባሰብሁ ቁጥር ቃተትሁ ባወጣሁ ባወረድሁ መጠን መንፈሴ ዛለች፡፡ BSB BSB: I remembered You, O God, and I groaned; I mused and my spirit grew faint. Selah
4 ULB ዐይኖቼ እንዳይከደኑ አደረግህ መናገር እስኪሳነኝ ድረስ ታወክሁ፡፡ BSB BSB: You have kept my eyes from closing; I am too troubled to speak.
5 ULB የቀድሞውን ዘመን አሰብሁ የድሮውን ዘመን አወጠነጠንሁ፡፡ BSB BSB: I considered the days of old, the years long in the past.
6 ULB በሌሊት ዝማሬዬን አስታወስሁ በጥልቅ በማሰብ እየሆነ ያለውን መረዳት ሞከርሁ፡፡ BSB BSB: At night I remembered my song; in my heart I mused, and my spirit pondered:
7 ULB እግዚአብሔር ለዘላለም ጥሎኛልን? ከእንግዲህስ ቸርነት አያደርግልኝምን? BSB BSB: “Will the Lord spurn us forever and never show His favor again?
8 ULB የኪዳን ታማኝነቱስ እስከ ወዲያኛው ተሻረን? የተስፋ ቃሉንስ ዘነጋ? BSB BSB: Is His loving devotion gone forever? Has His promise failed for all time?
9 ULB እግዚአብሔር ቸርነቱን ረሳ? ወይስ ከቁጣው የተነሣ መራራቱን ትቶአልን? ሴላ BSB BSB: Has God forgotten to be gracious? Has His anger shut off His compassion?” Selah
10 ULB እኔም፣ «የልዑል ቀኝ እጅ እንደ ተለወጠ ማሰቤ ይህ የእኔ ደካማነት ነው» አልሁ፡፡ BSB BSB: So I said, “I am grieved that the right hand of the Most High has changed.”
11 ULB ያህዌ ሆይ፣ ሥራዎችህን ሁሉ አስታውሳለሁ ድሮ ያደረግኸውን ድንቅ ሥራ አስባለሁ፡፡ BSB BSB: I will remember the works of the LORD; yes, I will remember Your wonders of old.
12 ULB ሥራዎችህን ሁሉ አሰላሰላለሁ ድንቅ ሥራህን ሁሉ አውጠነጥናለሁ፡፡ BSB BSB: I will reflect on all You have done and ponder Your mighty deeds.
13 ULB አምላክ ሆይ፣ መንገድህ ቅዱስ ነው እንደ አምላካችን ያለ ታላቅ አምላክ ማን ነው? BSB BSB: Your way, O God, is holy. What god is so great as our God?
14 ULB እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ድንቆችን የምታደርግ አምላክ ነህ በሕዝቦች መካከል ኃይልህን ገለጥህ፡፡ BSB BSB: You are the God who works wonders; You display Your strength among the peoples.
15 ULB በታላቅ ኃይልህ ለሕዝብህ ለያዕቆብና ለዮሴፍ ልጆች ድል ሰጠሃቸው፡፡ ሴላ BSB BSB: With power You redeemed Your people, the sons of Jacob and Joseph. Selah
16 ULB አምላክ ሆይ፣ ውሆች አዩህ ውሆች አንተን አይተው ፈሩ፤ ጥልቆችም ተነዋወጡ፡፡ BSB BSB: The waters saw You, O God; the waters saw You and swirled; even the depths were shaken.
17 ULB ደመኖች ውሃ አንጠባጠቡ፡፡ ሰማያት አንጐዳጐዱ ፍላጾችህም ዙሪያውን አንጸባረቁ፡፡ BSB BSB: The clouds poured down water; the skies resounded with thunder; Your arrows flashed back and forth.
18 ULB የድምፅህ ነጐድጓድ ዐውሎ ነፋስ ውስጥ አስተጋባ የመብረቅ ብልጭታ ዓለምን አበራ ምድር ራደች ተንቀጠቀጠች፡፡ BSB BSB: Your thunder resounded in the whirlwind; the lightning lit up the world; the earth trembled and quaked.
19 ULB መንገድህ በባሕር ውስጥ ነው መሄጃህም በታላቅ ውሃ ውስጥ ነው ዱካህንም ማንም አላየም፡፡ BSB BSB: Your path led through the sea, Your way through the mighty waters, but Your footprints were not to be found.
20 ULB በሙሴና በአሮን እጅ ሕዝብህን እንደ በግ መንጋ መራኸው፡፡ BSB BSB: You led Your people like a flock by the hand of Moses and Aaron.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.