1 ULB ወንድሞች ሆይ፥ሰው በሕይወት እስካለ ድረስ ሕግ እንደሚገዛው አታውቁምን? ይህንን የምለው ስለ ሕግ ለሚያውቁት ነው። BSB BSB: Do you not know, brothers (for I am speaking to those who know the law), that the law has authority over a man only as long as he lives?
2 ULB ያገባች ሴት ባሏ በሕይወት እስካለ ድረስ ለእርሱ በሕግ የታሰረች ነች፥ባሏ ቢሞት ግን ከጋብቻ ሕግ ነጻ ትሆናለች። BSB BSB: For instance, a married woman is bound by law to her husband as long as he lives. But if her husband dies, she is released from the law of marriage.
3 ULB እንግዲህ ባሏ በሕይወት እያለ ከሌላ ወንድ ጋር ብትኖር አመንዝራ ትባላለች። ባሏ ቢሞት ግን ከሕጉ ነጻ ስለሆነች ከሌላ ወንድ ጋር ብትኖርም አመንዝራ አትሆንም። BSB BSB: So then, if she is joined to another man while her husband is still alive, she is called an adulteress; but if her husband dies, she is free from that law and is not an adulteress if she marries another man.
4 ULB ስለዚህ ወንድሞቼ ሆይ፥እናንተም በክርስቶስ ሥጋ ለሕግ ምውት ተደርጋችኋል። ይኸውም ለእግዚአብሔር ፍሬ እናፈራ ዘንድ ከሌላው ማለትም ከሙታን ከተነሣው ጋር እንድትተባበሩ ነው። BSB BSB: Therefore, my brothers, you also died to the law through the body of Christ, that you might belong to another, to Him who was raised from the dead, in order that we might bear fruit to God.
5 ULB በሥጋ በነበርንበት ጊዜ ኃጢአታዊ ምኞት በሕግ በኩል ሞትን ሊያፈራ በሰውነታችን ክፍሎች ይሠራ ነበር። BSB BSB: For when we lived according to the flesh, the sinful passions aroused by the law were at work in our bodies, bearing fruit for death.
6 ULB አሁን ግን ከሕግ ነጻ ተደርገናል። ተይዘን ለነበርንበት ለዚያ ሞተናል።ይኸውም በአሮጌው ፊደል ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ እንድናገለግል ነው። BSB BSB: But now, having died to what bound us, we have been released from the law, so that we serve in the new way of the Spirit, and not in the old way of the written code.
7 ULB እንግዲህ ምን እንላለን? ሕጉ ራሱ ኃጢአት ነውን? አይደለም። ይሁንና በሕግ በኩል ባይሆን ኖሮ ኃጢአትን አላውቅም ነበር። ሕጉ "አትጎምጅ" ባይል ኖሮ መጎምጀትን አላውቅም ነበር። BSB BSB: What then shall we say? Is the law sin? Certainly not! Indeed, I would not have been mindful of sin if not for the law. For I would not have been aware of coveting if the law had not said, “Do not covet.”
8 ULB ነገር ግን ኃጢአት በትዕዛዛት አማካይነት ዕድል አገኘና መጎምጀትን ሁሉ በውስጤ አመጣ። ምክንያቱም ኃጢአት ያለ ሕግ ምውት ስለሆነ ነው። BSB BSB: But sin, seizing its opportunity through the commandment, produced in me every kind of covetous desire. For apart from the law, sin is dead.
9 ULB በአንድ ወቅት ያለ ሕግ ሕያው ነበርኩ፥ትዕዛዝ በመጣ ጊዜ ግን እኔ ሞትኩኝና ኃጢአት ህያው ሆነ። BSB BSB: Once I was alive apart from the law; but when the commandment came, sin sprang to life and I died.
10 ULB ሕይወትን እንዲያመጣ የተሰጠው ትዕዛዝ ለእኔ ሞት ሆነ። BSB BSB: So I discovered that the very commandment that was meant to bring life actually brought death.
11 ULB ምክንያቱም ኃጢአት በሕግ አማካይነት ዕድል አግኝቶ አታሎኛል። በትዕዛዝ አማካይነትም ገደለኝ። BSB BSB: For sin, seizing its opportunity through the commandment, deceived me and through the commandment put me to death.
13 ULB ስለዚህ በጎ የሆነው እርሱ ለእኔ ሞት ሆነብኝን? አይደለም። ነገር ግን ኃጢአት በጎ በሆነው በእርሱ አማካይነት ኃጢአትነቱ ይታወቅ ዘንድ በእኔ ሞትን አመጣብኝ። ይህ የሆነው በሕግ አማካይነት ኃጢአት ያለ ልክ ኃጢአታዊ ይሆን ዘንድ ነው። BSB BSB: Did that which is good, then, become death to me? Certainly not! But in order that sin might be exposed as sin, it produced death in me through what was good, so that through the commandment sin might become utterly sinful.
14 ULB ሕጉ መንፈሳዊ መሆኑን እናውቃለንና እኔ ግን ሥጋዊ ነኝ። ለኃጢአት ባርነት ተሽጫለሁ። BSB BSB: We know that the law is spiritual; but I am unspiritual, sold as a slave to sin.
15 ULB በርግጥ የማደርገውን አላውቅም። ለማድረግ የምፈልገውን አላደርግም፥ለማድረግ የምጠላውን ግን ያንኑ አደርጋለሁ። BSB BSB: I do not understand what I do. For what I want to do, I do not do. But what I hate, I do.
16 ULB ለማድረግ የማልፈልገውን የማደርግ ከሆንሁ ሕጉ መልካም ስለመሆኑ እስማማበታለሁ። BSB BSB: And if I do what I do not want to do, I admit that the law is good.
17 ULB አሁን ግን ያንን የሚያደርገው በእኔ የሚኖረው ኃጢአት ነው እንጂ እኔ አይደለሁም። BSB BSB: In that case, it is no longer I who do it, but it is sin living in me that does it.
18 ULB በእኔ ማለትም በሥጋዬ ውስጥ ምንም መልካም ነገር እንደሌለ አውቃለሁ። መልካም የማድረግ ፍላጎቱ አለኝ፥ነገር ግን ላደርገው አልችልም። BSB BSB: I know that nothing good lives in me, that is, in my flesh; for I have the desire to do what is good, but I cannot carry it out.
19 ULB የምፈልገውን ያንን መልካሙን አላደርግም ክፉውን፥ያንን የማልፈልገውን ግን አደርጋለሁ። BSB BSB: For I do not do the good I want to do. Instead, I keep on doing the evil I do not want to do.
20 ULB ለማድረግ የማልፈልገውን የማደርግ ከሆነ እንግዲህ አሁን ያንን የሚያደርገው በእኔ ውስጥ የሚኖረው ኃጢአት እንጂ እኔ አይደለሁም። BSB BSB: And if I do what I do not want, it is no longer I who do it, but it is sin living in me that does it.
21 ULB እንግዲህ መልካም የሆነውን ለማድረግ የሚፈልግ ሕግ በውስጤ እንዳለ አያለሁ፥ነገር ግን በተግባር በውስጤ ያለው ክፋት ሆኖ አገኘዋለሁ። BSB BSB: So this is the principle I have discovered: When I want to do good, evil is right there with me.
22 ULB በውስጡ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለኛል። BSB BSB: For in my inner being I delight in God’s law.
23 ULB ነገር ግን በሰውነቴ ክፍሎች ውስጥ ሌላ ሕግ አያለሁ። እርሱም በአዕምሮዬ ውስጥ ያለውን አዲሱን ሕግ በመቃወም ይዋጋል። በሰውነት ክፍሎቼ ውስጥ ባለ የኃጢአት ሕግ ይማርከኛል። BSB BSB: But I see another law at work in my body, warring against the law of my mind and holding me captive to the law of sin that dwells within me.
24 ULB እኔ ምስኪን ሰው ነኝ! ለሞት ከሚዳርገኝ ከዚህ ሰውነት ማን ይታደገኛል? BSB BSB: What a wretched man I am! Who will rescue me from this body of death?
25 ULB እንግዲያውስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን! እኔ ራሴ በአእምሮዬ የእግዚአብሔርን ሕግ አገለግላለሁ። ሆኖም በሥጋ የማገለግለው የኃጢአትን ሕግ ነው። BSB BSB: Thanks be to God, through Jesus Christ our Lord! So then, with my mind I serve the law of God, but with my flesh I serve the law of sin.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.