1 ULB እኔ በሜዳ የሚገኝ አበባ፥ በሸለቆም የሚገኝ አበባ ብቻ ነኝ። ሰውየው ሲናገራት፥ BSB BSB: I am a rose of Sharon, a lily of the valley.
2 ULB ውዴ ሆይ፥ አበባ በእሾህ መካከል እንደሆነ አንቺም በሀገሬ ሴቶች ልጆች መካከል ነሽ። ሴቲቱ ለራስዋ ስትናገር፥ BSB BSB: Like a lily among the thorns is my darling among the maidens.
3 ULB በዱር ዛፍ መካከል እንዳለ የእንኮይ ዛፍ የእኔም ውድ በጎልማሶች መካከል ነው። በታላቅ ደስታ ከጥላው ሥር ተቀመጥኩ፥ የፍሬውም ጣዕም ጣፋጭ ነው። BSB BSB: Like an apple tree among the trees of the forest is my beloved among the young men. I delight to sit in his shade, and his fruit is sweet to my taste.
4 ULB ወደ ግብዣው አዳራሽ አመጣኝ፥ በእኔ ላይ ያለው ሰንደቁ ፍቅር ነው። ሴቲቱ ለፍቅረኛዋ ስትናገር፥ BSB BSB: He has brought me to the house of wine, and his banner over me is love.
5 ULB በዘቢብ ጥፍጥፍ ነፍስ ዝሩብኝ፥ በእንኮይ ጭማቂም አበርቱኝ፥ በፍቅር ተይዤ ደክሜአለሁና። ሴቲቱ ለራስዋ ስትናገር፥ BSB BSB: Sustain me with raisins; refresh me with apples, for I am faint with love.
6 ULB ግራ እጁ ከአንገቴ ሥር ነው፥ ቀኝ እጁም ያቅፈኛል። ሴቲቱ ለሌላዋ ሴት ስትናገር፥ BSB BSB: His left hand is under my head, and his right arm embraces me.
7 ULB የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች፥ በፍቅር ግንኙነታችን ወቅት እስክንረካ ድረስ ላታቋርጡን በሜዳ ፍየሎችና በአጋዘኖች ቃል እንድትገቡልኝ እፈልጋለሁ። ሴቲቱ ለራሷ ትናገራለች፥ BSB BSB: O daughters of Jerusalem, I adjure you by the gazelles and does of the field: Do not arouse or awaken love until the time is right.
8 ULB የውዴ ድምጽ ነው! ኦ፥ በተራራዎች ላይ እየዘለለ፥ በኮረብታዎች ላይ እየተስፈነጠረ ሲመጣ ይታወቀኛል። BSB BSB: Listen! My beloved approaches. Look! Here he comes, leaping across the mountains, bounding over the hills.
9 ULB ውዴ የሜዳን ፍየል ወይም ግልገል አጋዘንን ይመስላል፤ እነሆ እርሱ ከቤታችን ግድግዳ በስተኋላ ቆሟል፥ በመስኮቱ በኩል አተኩሮ፥ በፍርግርጉም አጮልቆ ይመለከታል። BSB BSB: My beloved is like a gazelle or a young stag. Look, he stands behind our wall, gazing through the windows, peering through the lattice.
10 ULB ውዴ እንዲህ ሲል ተናገረኝ፥ "ውዴ ሆይ ተነሽ፤ የኔዋ ቆንጆ ከእኔ ጋር ነይ። BSB BSB: My beloved calls to me, “Arise, my darling. Come away with me, my beautiful one.
11 ULB ተመልከች፥ ክረምቱ አልፏል፥ ዝናቡም ቆሟል፥ ሄዷልም። BSB BSB: For now the winter is past; the rain is over and gone.
12 ULB አበቦች በምድር ላይ ታይተዋል፤ ወይን የሚገረዝበትና የወፎች ዝማሬ ጊዜ ደርሶአል፥ የእርግቦችም ድምጽ በምድራችን ተሰምቷል። BSB BSB: The flowers have appeared in the countryside; the season of singing has come, and the cooing of turtledoves is heard in our land.
13 ULB የበለስ ዛፍ አረንጓዴ ፍሬዎቿ በስለዋል፥ ወይኖቹም አብበዋል፥ መዓዛቸውንም ሰጥተዋል። ውዴ ሆይ ተነሽ፥ የኔዋ ቆንጆ ነይ። BSB BSB: The fig tree ripens its figs; the blossoming vines spread their fragrance. Arise, come away, my darling; come away with me, my beautiful one.”
14 ULB በዐለት ሥንጣቂ ውስጥ፥ በድብቁ የተራራማው ቋጢኝ ስንጣቂ ውስጥ ያለሽ እርግቤ ሆይ፥ ፊትሽን ልየው። ድምጽሽን ልስማው፥ ድምጽሽ ጣፋጭ ነውና ፊትሽም ውብ ነው።" ሴቲቱ ለራሷ ስትናገር፥ BSB BSB: O my dove in the clefts of the rock, in the crevices of the cliff, let me see your face, let me hear your voice; for your voice is sweet, and your countenance is lovely.
15 ULB የወይናችን ቦታ አብቦአልና የወይን ቦታዎችን የሚያበላሹትን ትናንሽ ቀበሮዎች ያዙልን። BSB BSB: Catch for us the foxes—the little foxes that ruin the vineyards—for our vineyards are in bloom.
16 ULB ውዴ የእኔ ነው፥ እኔም የእርሱ ነኝ፤ እርሱ መንጋውን በአበቦቹ መካከል በደስታ ያሰማራል። BSB BSB: My beloved is mine and I am his; he pastures his flock among the lilies.
17 ULB ሴቲቱ ለፍቅረኛዋ ስትናገር፥ ውዴ ሆይ፥ ተመለስ፣ የንጋቱ ቀዝቃዛ ንፋስ ሳይነፍስ፥ ጥላውም ሳይሸሽ። ተመለስ፤ በጎርበጥባጣዎቹ ኮረብቶች ላይ የሜዳ ፍየልን ወይም ግልገል አጋዘንን ምሰል። BSB BSB: Before the day breaks and shadows flee, turn, my beloved, and be like a gazelle or a young stag on the mountains of Bether.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.