Song of Songs 3 3 Song of Songs Longing and courtship Amharic Unlocked Literal Bible 1 ULB ሌሊት በመኝታዬ የምወደውን ናፈቅሁት፤ ፈለግሁት፥ ነገር ግን ላገኘው አልቻልኩም። BSB BSB: On my bed at night I sought the one I love; I sought him, but did not find him.
2 ULB እኔም ለራሴ፥ "እነሣለሁ፥ ወደ ከተማው ውስጥ፥ ወደ ጎዳናዎቹና ወደ አደባባዮቹ እሄዳለሁ፤ ውዴንም እፈልገዋለሁ" አልኩ። ፈለግሁት፥ ላገኘው ግን አልቻልኩም። BSB BSB: I will arise now and go about the city, through the streets and squares. I will seek the one I love. So I sought him but did not find him.
3 ULB ጠባቂዎች በከተማው ውስጥ ለጥበቃ ሲዘዋወሩ አገኙኝ። እኔም፥ "ውዴን አይታችሁታል?" ብዬ ጠየቅኋቸው። BSB BSB: I encountered the watchmen on their rounds of the city: “Have you seen the one I love?”
4 ULB ከእነርሱ ጥቂት እልፍ እንዳልኩኝ ነፍሴ የወደደችውን አገኘሁት። ያዝኩት፥ ወደ እናቴ ቤት፥ ወደ ፀነሰችኝም መኝታ ቤት እስካመጣው ድረስ አልለቀውም። ሴቲቱ ለሌላይቱ ሴት ስትናገር፥ BSB BSB: I had just passed them when I found the one I love. I held him and would not let go until I had brought him to my mother’s house, to the chamber of the one who conceived me.
5 ULB እናንተ የኢየሩሳሌም ሰዎች ሴቶች ልጆች፥ በፍቅር ግንኙነታችን እስክንረካ ድረስ ላታቋርጡን በሜዳ ፍየሎችና አጋዘኖች እንድትምሉልኝ እፈልጋለሁ። ወጣቷ ሴት ለራሷ ስትናገር፥ BSB BSB: O daughters of Jerusalem, I adjure you by the gazelles and does of the field: Do not arouse or awaken love until the time is right.
6 ULB ይህቺ በዕጣንና ከርቤ፥ ነጋዴዎችም በሚሸጡት ልዩ ልዩ ቅመም በተቀመመ ሽቶ ተቀብታ እንደ ጢስ ምሶሶ ከምድረ በዳ የምትወጣ ማናት? BSB BSB: Who is this coming up from the wilderness like a column of smoke, scented with myrrh and frankincense from all the spices of the merchant?
7 ULB እነሆ እርሱ የሰለሞን ተንቀሳቃሽ አልጋ ነው፤ ስልሳ የእስራኤል ወታደሮች፥ ስልሳ ጦረኞች ከብበውታል። BSB BSB: Behold, it is Solomon’s carriage, escorted by sixty of the mightiest men of Israel.
8 ULB እነርሱ በሰይፍ የላቁ ናቸው፥ በጦርነትም የታወቁ። እያንዳንዱ በወገቡ ሰይፍ አለው፥ በሌሊት የሚያሸብሩትን ለመከላከል ታጥቀዋል። BSB BSB: All are skilled with the sword, experienced in warfare. Each has his sword at his side prepared for the terror of the night.
9 ULB ንጉሥ ሰለሞን ከሊባኖስ በመጣ እንጨት ሰው ተቀምጦበት የሚሸከሙትን ለአንድ ሰው መቀመጫ የሚሆን ወንበር የሚይዝ ሳጥን ለራሱ ሠራ። BSB BSB: King Solomon has made his carriage out of the timber of Lebanon.
10 ULB ምሶሶዎቹን ከብር፥ ጀርባው ከወርቅ፥ መቀመጫው ከሐምራዊ ጨርቅ ተደርጎ ተሠራ። ውስጡ የተዋበው በኢየሩሳሌም ሰዎች ሴቶች ልጆች ነበር። ወጣቷ ለኢየሩሳሌም ሴቶች ስትናገር፥ BSB BSB: He has made its posts of silver, its base of gold, its seat of purple fabric. Its interior is inlaid with love by the daughters of Jerusalem.
11 ULB የጽዮን ሴቶች ልጆች ሆይ፥ ሂዱ ውጡ፥ ንጉሥ ሰለሞንን ትኩር ብላችሁ እዩት፥ በሕይወቱ በተደሰተባት በዚያች ቀን፥ በሠርጉ ቀን እናቱ የደፋችለትን አክሊል ጭኖ። BSB BSB: Come out, O daughters of Zion, and gaze at King Solomon, wearing the crown with which his mother crowned him on the day of his wedding—the day of his heart’s rejoicing.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.
Chapter complete
You’ve read Song of Songs 3
Make Opened yours A free account keeps your place, highlights and notes on every device. Add Plus to ask Study Help about Song of Songs 3, and keep Opened free for readers who can’t pay.