1 ULB ኦ፥ ወዳጄ ሆይ፥ አንቺ ውብ ነሽ፥ እነሆም ቆንጆ ነሽ። በመሸፈኛሽ ውስጥ ዓይኖችሽ እርግቦች ናቸው። ጸጉርሽ ከገለዓድ ተራራ ቁልቁል የሚወርደውን የፍየል መንጋ ይመስላል። BSB BSB: How beautiful you are, my darling—how very beautiful! Your eyes are like doves behind your veil. Your hair is like a flock of goats streaming down Mount Gilead.
2 ULB ጥርስሽ በቅርቡ ተሸልቶ ከመታጠቢያው ሥፍራ የሚወጣውን የበግ መንጋ ይመስላል። እያንዳንዱ መንታ ወልዷል፥ በመካከላቸውም መካን የለም። BSB BSB: Your teeth are like a flock of newly shorn sheep coming up from the washing; each has its twin, and not one of them is lost.
3 ULB ከንፈሮችሽ ቀይ የሐር ፈትል ይመስላሉ፤ አፍሽ ውብ ነው። ጉንጮችሽ በመሸፈኛሽ ውስጥ ለሁለት የተከፈለ ሮማን ይመስላል። BSB BSB: Your lips are like a scarlet ribbon, and your mouth is lovely. Your brow behind your veil is like a slice of pomegranate.
4 ULB አንገትሽ በረድፍ በተደረደሩ ድንጋዮች ላይ የተገነባውን የዳዊትን የጥበቃ ማማ ይመስላል፥ አንድ ሺህ ጋሻ፥ የወታደሮቹ ሁሉ ጋሻ በእርሱ ላይ ተሰቅሏል። BSB BSB: Your neck is like the tower of David, built with rows of stones; on it hang a thousand shields, all of them shields of warriors.
5 ULB ሁለቱ ጡቶችሽ በአበቦች መካከል የተሰማሩ ሁለት የአጋዘን ግልገሎችን፥ መንታም የተወለዱ የሜዳ ፍየሎችን ይመስላሉ። BSB BSB: Your breasts are like two fawns, twins of a gazelle grazing among the lilies.
6 ULB ጎሕ እስኪቀድና ጥላው እስኪሸሽ ድረስ፥ ወደ ከርቤው ተራራ፥ ወደ ዕጣኑም ኮረብታ እሄዳለሁ። BSB BSB: Before the day breaks and the shadows flee, I will make my way to the mountain of myrrh and to the hill of frankincense.
7 ULB ውዴ ሆይ፥ ሁለመናሽ ውብ ነው፥ እንከንም የለብሽም። BSB BSB: You are altogether beautiful, my darling; in you there is no flaw.
8 ULB ሙሽራዬ ሆይ፥ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ። አዎን፥ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ፥ ከአማና ጫፍ፥ ከሳኔርና ከኤርሞን ጫፍ፥ ከአንበሶች ዋሻ፥ የነብሮች ዋሻ ከሆነውም ተራራ ነይ። BSB BSB: Come with me from Lebanon, my bride, come with me from Lebanon! Descend from the peak of Amana, from the summits of Senir and Hermon, from the dens of the lions, from the mountains of the leopards.
9 ULB እህቴ ሙሽራዬ ሆይ፥ ልቤን ሰርቀሽዋል፤ በአንድ አፍታ ዕይታሽ ብቻ፥ በአንድ ሐብልሽ ብቻ ልቤን ሰርቀሽዋል። BSB BSB: You have captured my heart, my sister, my bride; you have stolen my heart with one glance of your eyes, with one jewel of your neck.
10 ULB እህቴ ሙሽራዬ ሆይ፥ ፍቅርሽ እንዴት ያማረ ነው! ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ ምንኛ ይሻላል፥ የሽቶሽ መዓዛም ከቅመሞች ሁሉ። BSB BSB: How delightful is your love, my sister, my bride! Your love is much better than wine, and the fragrance of your perfume than all spices.
11 ULB ሙሽራዬ ሆይ፥ ከንፈሮችሽ ማር ያንጠባጥባሉ፥ ማርና ወተት ምላስሽ ሥር ናቸው። የልብሶችሽ መዓዛ የሊባኖስን መዓዛ ይመስላል። BSB BSB: Your lips, my bride, drip sweetness like the honeycomb; honey and milk are under your tongue, and the fragrance of your garments is like the aroma of Lebanon.
12 ULB እህቴ ሙሽራዬ የተቆለፈበት የመናፈሻ ቦታ ናት፥ የተቆለፈበት የመናፈሻ ቦታ፥ የታተመበትም ምንጭ። BSB BSB: My sister, my bride, you are a garden locked up, a spring enclosed, a fountain sealed.
13 ULB ቅርንጫፎችሽ የሮማን ዛፍ ከተመረጠ ፍሬ ጋር፥ ሂናና የናርዶስ ተክል፥ BSB BSB: Your branches are an orchard of pomegranates with the choicest of fruits, with henna and nard,
14 ULB ናርዶስና ቀጋ፥ ጠጅ ሣርና ቀረፋ ከልዩ ልዩ ቅመሞች ጋር፥ ከርቤና እሬት ምርጥ ከሆኑት ቅመሞች ሁሉ ጋር አሉባቸው። BSB BSB: with nard and saffron, with calamus and cinnamon, with every kind of frankincense tree, with myrrh and aloes, with all the finest spices.
15 ULB አንቺ የአትክልት ሥፍራ ምንጭ፥ የንጹህ ውሃ ጉድጓድ፥ ከሊባኖስ ወደ ታች የሚወርድ ምንጭ ነሽ። ወጣቷ ለፍቅረኛዋ ስትናገር፥ BSB BSB: You are a garden spring, a well of fresh water flowing down from Lebanon.
16 ULB የሰሜን ንፋስ ሆይ ንቃ፤ የደቡቡም ንፋስ ና፤ ቅመሞቹ መዓዛቸውን እንዲሰጡ በአትክልት ሥፍራዬ ላይ ንፈስ። ውዴ ወደ አትክልቱ ሥፍራ ይምጣ፥ ከምርጡም ፍሬ ጥቂት ይብላ። BSB BSB: Awake, O north wind, and come, O south wind. Breathe on my garden and spread the fragrance of its spices. Let my beloved come into his garden and taste its choicest fruits.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.