1 ULB እህቴ፥ ሙሽራዬ፥ ወደ አትክልቴ ቦታ መጣሁ፤ ከርቤዬን ከቅመሜ ጋር ሰብስቤአለሁ። የማር እንጀራዬን ከወለላው ጋር በልቻለሁ፤ ወይኔን ከወተቴ ጋር ጠጥቻለሁ። ጓደኞች ለአፍቃሪዎች ሲናገሩ፥ ጓደኞቻችን ሆይ ብሉ፤ ጠጡ፥ በፍቅርም ስከሩ። ወጣቷ ለራሷ ስትናገር፥ BSB BSB: I have come to my garden, my sister, my bride; I have gathered my myrrh with my spice. I have eaten my honeycomb with my honey; I have drunk my wine with my milk. Eat, O friends, and drink; drink freely, O beloved.
2 ULB እኔ ተኝቻለሁ፥ ልቤ ግን በሕልም ነቅቷል። የውዴ ድምጽ ነው፥ በሩን ያንኳኳል፥ "እህቴ፥ ውዴ፥ እርግቤ፥ እንከን የሌለብሽ ሆይ፥ ራሴ በጤዛ ርሷል ፀጉሬም በሌሊቱ እርጥበት፥ ስለዚህ ክፈችልኝ" እያለ። BSB BSB: I sleep, but my heart is awake. A sound! My beloved is knocking: “Open to me, my sister, my darling, my dove, my flawless one. My head is drenched with dew, my hair with the dampness of the night.”
3 ULB "ልብሴን አውልቄአለሁ፤ እንደገና መልበስ አለብኝ? እግሬን ታጥቤአለሁ፤ ማቆሸሽ አለብኝ?" BSB BSB: I have taken off my robe—must I put it back on? I have washed my feet—must I soil them again?
4 ULB ውዴ በበሩ መካፈቻ ቀዳዳ በኩል እጁን አስገባ፥ ልቤም ስለ እርሱ ታወከ። BSB BSB: My beloved put his hand to the latch; my heart pounded for him.
5 ULB ለውዴ በሩን ልከፍትለት ተነሣሁ፥ እጆቼ ከርቤን አንጠባጠቡ፥ ጣቶቼ በበሩ እጀታ ላይ በከርቤ ረጠቡ። BSB BSB: I rose up to open for my beloved. My hands dripped with myrrh, my fingers with flowing myrrh on the handles of the bolt.
6 ULB ለውዴ በሩን ከፈትኩለት፥ ውዴ ግን ተመልሶ ሄዶ ነበር። ልቤ ደነገጠ፤ እኔም ተከፋሁ። ፈለግሁት፥ ነገር ግን አላገኘሁትም፤ ጠራሁት፥ ነገር ግን አልመለሰልኝም። BSB BSB: I opened for my beloved, but he had turned and gone. My heart sank at his departure. I sought him but did not find him. I called, but he did not answer.
7 ULB ጠባቂዎቹ በከተማ ሲዘዋወሩ አገኙኝ፤ መቱኝ፥ አቆሰሉኝም፤ በቅጥሩ ላይ ያሉት ጠባቂዎችም ካባዬን ወሰዱብኝ። ወጣቷ ለከተማው ሴቶች ስትናገር፥ BSB BSB: I encountered the watchmen on their rounds of the city. They beat me and bruised me; they took away my cloak, those guardians of the walls.
8 ULB እናንተ የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች፥ ውዴን ካገኛችሁት ለእርሱ ካለኝ ፍቅር የተነሣ መታመሜን ልትነግሩት ቃል እንድትገቡልኝ እፈልጋለሁ። የከተማው ሴቶች ለወጣቷ ሲናገሩ፥ BSB BSB: O daughters of Jerusalem, I adjure you, if you find my beloved, tell him I am sick with love.
9 ULB አንቺ በሴቶች መካከል የተዋብሽዋ ሆይ፥ ውድሽ ከሌላው አፍቃሪ ወንድ የተሻለው እንዴት ነው? እንዲህ ያለውን መሐላ እንድናደርግ የጠየቅሽን ውድሽ ከሌላው አፍቃሪ የተሻለው ለምንድነው? ወጣቷ ለከተማው ሴቶች ስትናገር፥ BSB BSB: How is your beloved better than others, O most beautiful among women? How is your beloved better than another, that you charge us so?
10 ULB ውዴ ደስተኛና ቀይ ነው፥ ከአሥር ሺዎችም የላቀ ነው። BSB BSB: My beloved is dazzling and ruddy, outstanding among ten thousand.
11 ULB ራሱ ንጹህ ወርቅ ነው፤ ፀጉሩም ዞማና እንደ ቁራ የጠቆረ ነው። BSB BSB: His head is purest gold; his hair is wavy and black as a raven.
12 ULB ዓይኖቹ በጅረት አጠገብ እንዳሉ እርግቦች፥ በወተት እንደ ታጠቡ፥ በማስቀመጫቸው ያሉ ዕንቁዎችን ይመስላሉ። BSB BSB: His eyes are like doves beside the streams of water, bathed in milk and mounted like jewels.
13 ULB ጉንጮቹ የሽቶ መዓዛ የሚሰጡ የልዩ ልዩ ቅመማ ቅመም መደብ ይመስላሉ። ከንፈሮቹ ከርቤን የሚያንጠባጥቡ አበቦች ናቸው። BSB BSB: His cheeks are like beds of spice, towers of perfume. His lips are like lilies, dripping with flowing myrrh.
14 ULB ክንዶቹ የዕንቁ ፈርጥ ባለበት ወርቅ ተሸፍኗል፤ ሆዱ በሰንፔር ያጌጠ የዝሆን ጥርስ ነው። BSB BSB: His arms are rods of gold set with beryl. His body is polished ivory bedecked with sapphires.
15 ULB እግሮቹ በንጹህ የወርቅ መሠረት ላይ የቆሙ፥ የእምነ በረድ ምሶሶዎች ናቸው፤ መልኩ እንደ ሊባኖስ፥ እንደ ተመረጠም ዝግባ ነው። BSB BSB: His legs are pillars of marble set on bases of pure gold. His appearance is like Lebanon, as majestic as the cedars.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.