1 ULB አንድ ቀን እንዲህ ሆነ፣ ኢየሱስ ሕዝቡን በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያስተምርና ወንጌልን ይሰብክ በነበረ ጊዜ፣ የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ከሽማግሌዎች ጋር ወደ እርሱ መጡ። BSB BSB: One day as Jesus was teaching the people in the temple courts and proclaiming the gospel, the chief priests and scribes, together with the elders, came up to Him.
2 ULB "እነዚህን ነገሮች የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? ወይም ይህን ሥልጣን የሰጠህ እርሱ ማን ነው?" አሉት። BSB BSB: “Tell us,” they said, “by what authority are You doing these things, and who gave You this authority?”
3 ULB እርሱም እንዲህ በማለት መለሰላቸው፤ "እኔም አንድ ጥያቄ እጠይቃችኋለሁ፣ እስቲ መልሱልኝ። BSB BSB: “I will also ask you a question,” Jesus replied. “Tell Me:
4 ULB የዮሐንስ ጥምቀት ከሰማይ ነበር ወይስ ከሰዎች?" BSB BSB: John’s baptism—was it from heaven, or from men?”
5 ULB እርስ በርሳቸው ተመካከሩና፣ "'ከሰማይ ነው ብንል፣ 'ታዲያ ለምን አላመናችሁትም ይለናል። BSB BSB: They deliberated among themselves and said, “If we say, ‘From heaven,’ He will ask, ‘Why did you not believe him?’
6 ULB ነገር ግን 'ከሰው ነው ብንል' ሕዝቡ ዮሐንስን ነቢይ አድርገው ስለሚቆጥሩ ይወግሩናል" አሉ። BSB BSB: But if we say, ‘From men,’ all the people will stone us, for they are convinced that John was a prophet.”
7 ULB ስለዚህ ከየት እንደ ሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት። BSB BSB: So they answered that they did not know where it was from.
8 ULB ኢየሱስ፣ "እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ አልነግራችሁም" አላቸው። BSB BSB: And Jesus replied, “Neither will I tell you by what authority I am doing these things.”
9 ULB ለሕዝቡ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፣ "አንድ ሰው ያዘጋጀውን የወይን ዕርሻ ለወይን ገበሬዎች አከራይቶ ረጅም ጊዜ ሊቆይ ወደ ሌላ አገር ሄደ። BSB BSB: Then He proceeded to tell the people this parable: “A man planted a vineyard, rented it out to some tenants, and went away for a long time.
10 ULB ምርቱ የሚሰበሰብበት ጊዜ ሲደርስ ከወይኑ የሚገባውን ፍሬ ለማግኘት ወደ ገበሬዎቹ አንድ አገልጋይ ላከ። ነገር ግን የወይኑ ገበሬዎች አገልጋዩን ደብድበው ባዶ እጁን መልሰው ላኩት። BSB BSB: At harvest time, he sent a servant to the tenants to collect his share of the fruit of the vineyard. But the tenants beat the servant and sent him away empty-handed.
11 ULB እርሱም አሁንም ሌላ አገልጋይ ላከባቸው፣ ይህንም ደብድበውና አዋርደው ባዶ እጁን መልሰው ላኩት። BSB BSB: So he sent another servant, but they beat him and treated him shamefully, sending him away empty-handed.
12 ULB እንደ ገና ሦስተኛ አገልጋይ ቢልክባቸው፣ እርሱንም አቈሳስለው አውጥተው ጣሉት። BSB BSB: Then he sent a third, but they wounded him and threw him out.
13 ULB ስለዚህ የወይኑ ዕርሻ ባለቤት፣ 'ምን ላድርግ? የምወደውን ልጄን እልከዋለሁ። ምናልባት እርሱን ያከብሩት ይሆናል' አለ። BSB BSB: ‘What shall I do?’ asked the owner of the vineyard. ‘I will send my beloved son. Perhaps they will respect him.’
14 ULB ነገር ግን የወይኑ ገበሬዎች ባዩት ጊዜ፣ 'ወራሹ ይህ ነው። ዕርሻው የእኛ እንዲሆን እንግድለው' ብለው እርስ በርስ ተመካከሩ። BSB BSB: But when the tenants saw the son, they discussed it among themselves and said, ‘This is the heir. Let us kill him, and the inheritance will be ours.’
15 ULB ከዕርሻው ቦታ አወጡትና ገደሉት። እንግዲህ የዕርሻው ባለቤት ምን ያደርግባቸዋል? መጥቶ እነዚህን የወይን ገበሬዎች ይደመስሳቸዋል፣ BSB BSB: So they threw him out of the vineyard and killed him. What then will the owner of the vineyard do to them?
16 ULB ዕርሻውንም ለሌሎች ይሰጣል" አላቸው። እነርሱም ይህን በሰሙ ጊዜ፣ "እግዚአብሔር እንዲህ ያለውን ነገር ያርቀው!" አሉ። BSB BSB: He will come and kill those tenants and give the vineyard to others.” And when the people heard this, they said, “May such a thing never happen!”
17 ULB ኢየሱስ ግን ተመለከታቸውና፣ 'ግንበኞች የናቁት ድንጋይ የማዕዘን ራስ ሆነ' "የሚለው ይህ የመጽሐፍ ቃል ምን ማለት ነው? BSB BSB: But Jesus looked directly at them and said, “Then what is the meaning of that which is written: ‘The stone the builders rejected has become the cornerstone’?
18 ULB በዚህ ድንጋይ የሚደናቀፍ ሁሉ ይሰባበራል። ነገር ግን ድንጋዩ የሚወድቅበት ሁሉ ይደቃል" አለ። BSB BSB: Everyone who falls on this stone will be broken to pieces, but he on whom it falls will be crushed.”
19 ULB ስለዚህ፣ የሕግ መምህራንና የካህናት አለቆች በዚያን ሰዓት ሊይዙት ፈለጉ፣ ምክንያቱም ይህን ምሳሌ የተናገረው በእነርሱ ላይ እንደ ሆነ አውቀዋልና። BSB BSB: When the scribes and chief priests realized that Jesus had spoken this parable against them, they sought to arrest Him that very hour. But they were afraid of the people.
20 ULB ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ። በዐይነ ቁራኛ እየተከታተሉት፣ ለፍርድና ለገዢው ሥልጣን የሚዳርገውን ስሕተት ከንግግሩ ሊያገኙበት ራሳቸውን ጻድቃን አስመስለው የሚቀርቡ ሰላዮችን ላኩበት። BSB BSB: So they watched Him closely and sent spies who pretended to be sincere. They were hoping to catch Him in His words in order to hand Him over to the rule and authority of the governor.
21 ULB እነርሱ እንዲህ በማለት ጠየቁት፤ "መምህር ሆይ፣ አንተ በትክክል እንደምትናገርና እንደምታስተምር፣ ደግሞም በማንም እንደማትመራ፣ነገር ግን ስለ እግዚአብሔር መንገድ እውነቱን እንደምታስተምር እናውቃለን። BSB BSB: “Teacher,” they inquired, “we know that You speak and teach correctly. You show no partiality but teach the way of God in accordance with the truth.
22 ULB ለቄሣር ግብር መክፈል ተፈቅዷል ወይስ አልተፈቀደም?" BSB BSB: Is it lawful for us to pay taxes to Caesar or not?”
23 ULB ኢየሱስ ግን ተንኰላቸውን ተረዳ፣ እንዲህም አላቸው፣ BSB BSB: But Jesus saw through their duplicity and said to them,
24 ULB "አንድ ዲናር አሳዩኝ። በላዩ ያለው የማን ጽሑፍና ምስል ነው?" እነርሱም፣ "የቄሣር ነው" አሉት። BSB BSB: “Show Me a denarius. Whose image and inscription are on it?” “Caesar’s,” they answered.
25 ULB "እንግዲያውስ የቄሣር የሆኑትን ነገሮች ለቄሣር፣ የእግዚአብሔርን ነገሮች ለእግዚአብሔር ስጡ" አላቸው። BSB BSB: So Jesus told them, “Give to Caesar what is Caesar’s, and to God what is God’s.”
26 ULB የሕግ መምህራንና የካህናት አለቆች በሕዝቡ ፊት በንግግሩ ሊያጠምዱት አልቻሉም። ምንም እስከማይናገሩ ድረስ በመልሱ ተደነቁ። BSB BSB: And they were unable to trap Him in His words before the people. And amazed at His answer, they fell silent.
27 ULB የሙታን ትንሣኤ የለም የሚሉ አንዳንድ ሰዱቃውያን ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ፣ BSB BSB: Then some of the Sadducees, who say there is no resurrection, came to question Him.
28 ULB እንዲህ ብለው ጠየቁት፤ "መምህር ሆይ፣ ሙሴ አንድ ሰው ሚስት አግብቶ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት ወንድሙ የዚያን ሰው ሚስት አግብቶ ልጅ ለእርሱ እንዲወልድለት ጽፎልናል። BSB BSB: “Teacher,” they said, “Moses wrote for us that if a man’s brother dies and leaves a wife but no children, the man is to marry his brother’s widow and raise up offspring for him.
29 ULB ሰባት ወንድማማች ነበሩ፤ የመጀመሪያው ሚስት አገባና ልጅ ሳይወልድ ሞተ፤ BSB BSB: Now there were seven brothers. The first one married a wife but died childless.
30 ULB ሁለተኛውም እንደዚሁ አግብቷት ልጅ ሳይወልድ ሞተ። BSB BSB: Then the second
31 ULB ሦስተኛውም አገባት፤ በዚህ ዓይነት ሰባቱም ሴቲቱን አግብተው ልጅ ሳይወልዱ ሞቱ። BSB BSB: and the third married the widow, and in the same way all seven died, leaving no children.
32 ULB በመጨረሻ ሴቲቱም ሞተች። BSB BSB: And last of all, the woman died.
33 ULB ታዲያ በትንሣኤ ቀን ይህች ሴት የማንኛቸው ሚስት ትሆናለች? ምክንያቱም ሰባቱም አግብተዋታልና።" BSB BSB: So then, in the resurrection, whose wife will she be? For all seven were married to her.”
34 ULB ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ "የዚህ ዓለም ሰዎች ያገባሉ፣ ይጋባሉም። BSB BSB: Jesus answered, “The sons of this age marry and are given in marriage.
35 ULB ነገር ግን የሙታን ትንሣኤንና የዘላለም ሕይወትን ለመቀበል የተገባቸው አያገቡም፣ አይጋቡምም። BSB BSB: But those who are considered worthy to share in the age to come and in the resurrection from the dead will neither marry nor be given in marriage.
36 ULB እንደ መላእክት ስለ ሆኑ፣ ከእንግዲህ ወዲያ ሊሞቱ አይችሉም። የትንሣኤ ልጆች እንደ መሆናቸው መጠን የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው።" BSB BSB: In fact, they can no longer die, because they are like the angels. And since they are sons of the resurrection, they are sons of God.
37 ULB ነገር ግን ሙታን ስለ መነሣታቸው ሙሴ እንኳ በቊጥቋጦው ስፍራ፣ጌታን የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክና የያዕቆብ አምላክ ብሎ በመጥራቱ አሳይቷል። BSB BSB: Even Moses demonstrates that the dead are raised, in the passage about the burning bush. For he calls the Lord ‘the God of Abraham, the God of Isaac, and the God of Jacob.’
38 ULB አሁን እርሱ የሕያዋን እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም፣ ምክንያቱም ለእርሱ ሁሉም ሕያዋን ናቸው።" BSB BSB: He is not the God of the dead, but of the living, for to Him all are alive.”
39 ULB ከሕግ መምህራን አንዳንዶች፣ "መምህር ሆይ፣ ጥሩ አድርገህ መልሰሃል" አሉት። BSB BSB: Some of the scribes answered, “Teacher, You have spoken well!”
40 ULB ደግሞም ተጨማሪ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ ማንም አልደፈሩም። BSB BSB: And they did not dare to question Him any further.
41 ULB ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ "እንግዲህ ሰዎች ክርስቶስን የዳዊት ልጅ ነው የሚሉት እንዴት ነው? BSB BSB: Then Jesus declared, “How can it be said that the Christ is the Son of David?
42 ULB ዳዊት ራሱ በመዝሙር መጽሐፍ፣ "ጌታ ለጌታዬ ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ BSB BSB: For David himself says in the book of Psalms: ‘The Lord said to my Lord, “Sit at My right hand
43 ULB እስከማደርግልህ ድረስ 'በቀኜ ተቀመጥ' ይላልና። BSB BSB: until I make Your enemies a footstool for Your feet.”’
44 ULB ስለዚህ ዳዊት ክርስቶስን ጌታ ይለዋል፣ታዲያ የዳዊት ልጅ እንዴት ይሆናል?" BSB BSB: Thus David calls Him ‘Lord.’ So how can He be David’s son?”
45 ULB ሕዝቡ ሁሉ እየሰሙ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፣ BSB BSB: In the hearing of all the people, Jesus said to His disciples,
46 ULB "ረጅም ቀሚስ ለብሰው መመላለስ ከሚፈልጉ፣ በገበያ ቦታዎችም ልዩ ሰላምታ፣ በምኲራቦች ከፍተኛ ስፍራ፣ በግብዣ ቦታዎችም የከበሬታ መቀመጫ እንዲሰጣቸው ከሚወዱ የሕግ መምህራን ተጠንቀቁ። BSB BSB: “Beware of the scribes. They like to walk around in long robes, and they love the greetings in the marketplaces, the chief seats in the synagogues, and the places of honor at banquets.
47 ULB ደግሞም እነርሱ ረጅም የሆኑ የማስመሰል ጸሎቶችን እየጸለዩ የመበለቶችን ቤት አለአግባብ ይበዘብዛሉ። እነዚህ የባሰ ቅጣት ይቀበላሉ።" BSB BSB: They defraud widows of their houses, and for a show make lengthy prayers. These men will receive greater condemnation.”