1 ULB ኢየሱስ ቀና ብሎ ሲመለከት ሀብታም ሰዎች በመባ መሰብሰቢያ ሣጥን ውስጥ ገንዘብ ሲጨምሩ አየ። BSB BSB: Then Jesus looked up and saw the rich putting their gifts into the treasury,
2 ULB አንዲት ድኻ መበለት ደግሞ ሁለት ሳንቲሞችን ስትጨምር አየ። BSB BSB: and He saw a poor widow put in two small copper coins.
3 ULB ስለዚህ እንዲህ አለ፣ "እውነት እላችኋለሁ፣ ይህች ድኻ መበለት ከሁሉም የበለጠ ሰጠች። BSB BSB: “Truly I tell you,” He said, “this poor widow has put in more than all the others.
4 ULB እነዚህ ሁሉ የሰጡት ስጦታ ከተትረፈረፈ ሀብታቸው ነው። ይህች መበለት ግን በድኽነቷ መተዳደሪያዋን ሁሉ ሰጠች።" BSB BSB: For they all contributed out of their surplus, but she out of her poverty has put in all she had to live on.”
5 ULB አንዳንዶች ቤተ መቅደሱ በተዋቡ ድንጋዮች እንዴት እንዳማረና እንዳጌጠ ሲናገሩ ሰምቶ እንዲህ አለ፣ BSB BSB: As some of the disciples were remarking how the temple was adorned with beautiful stones and consecrated gifts, Jesus said,
7 ULB ስለዚህ፣ "መምህር ሆይ፣ እነዚህ ነገሮች የሚሆኑት መቼ ነው? እነዚህ ነገሮች እንደሚፈጸሙ ምልክቱስ ምንድን ነው?" በማለት ጠየቁት። BSB BSB: “Teacher,” they asked, “when will these things happen? And what will be the sign that they are about to take place?”
8 ULB ኢየሱስ፣ "እንዳትስቱ ተጠንቀቁ። ምክንያቱም ብዙዎች 'እኔ ኢየሱስ ነኝ፣ ደግሞም 'ጊዜው አሁን ነው' እያሉ በስሜ ይመጣሉ። አትከተሏቸው። BSB BSB: Jesus answered, “See to it that you are not deceived. For many will come in My name, claiming, ‘I am He,’ and, ‘The time is near.’ Do not follow them.
9 ULB ስለ ጦርነቶችና ሁከቶች ስትሰሙ አትሸበሩ፣ እነዚህ ነገሮች አስቀድመው መፈጸም ይኖርባቸዋል፣ ነገር ግን መጨረሻው ወዲያው አይሆንም" ብሎ መለሰ። BSB BSB: When you hear of wars and rebellions, do not be alarmed. These things must happen first, but the end is not imminent.”
10 ULB ከዚያም እንዲህ አላቸው፣ "ሕዝብ በሕዝብ ላይ ይነሣል፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣል። BSB BSB: Then He told them, “Nation will rise against nation, and kingdom against kingdom.
11 ULB ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ይሆናል፣ ደግሞም በተለያዩ ቦታዎች ራብና ቸነፈር ይከሠታል። አስፈሪ ሁነቶችና ታላላቅ ምልክቶች ከሰማይ ይገለጣሉ። BSB BSB: There will be great earthquakes, famines, and pestilences in various places, along with fearful sights and great signs from heaven.
12 ULB ነገር ግን ከእነዚህ ሁሉ ነገሮች አስቀድሞ እናንተን ይይዟችኋል፣ ያሳድዷችኋል፣ ለምኩራቦችና ለወህኒ ቤቶች አሳልፈው በመስጠት ስለ ስሜ በገዦችና በነገሥታት ፊት ያቆሟችኋል። BSB BSB: But before all this, they will seize you and persecute you. On account of My name they will deliver you to the synagogues and prisons, and they will bring you before kings and governors.
13 ULB ይህም ለእናንተ ለመመስከር ዕድልን ይሰጣችኋል። BSB BSB: This will be your opportunity to serve as witnesses.
14 ULB ስለዚህ፣ አስቀድማችሁ ምን መከላከያ እናቀርባለን በማለት አትናወጡ፣ BSB BSB: So make up your mind not to worry beforehand how to defend yourselves.
15 ULB ምክንያቱም በዚያን ጊዜ ጠላቶቻችሁ ሊቋቋሙትና ሊቃወሙት የማይችሉትን ቃልና ጥበብ እሰጣችኋለሁ። BSB BSB: For I will give you speech and wisdom that none of your adversaries will be able to resist or contradict.
16 ULB ነገር ግን በወላጆች፣ በወንደሞች፣ በዘመዶችና በጓደኞች ተላልፋችሁ ትሰጣላችሁ፣ ከእናንተም አንዳንዶቹን ይገድላሉ። BSB BSB: You will be betrayed even by parents and brothers and relatives and friends, and some of you will be put to death.
17 ULB በስሜ ምክንያት በሰው ሁሉ ትጠላላችሁ። BSB BSB: And you will be hated by everyone because of My name.
18 ULB ነገር ግን ከራሳችሁ ጠጒር አንዲቱ እንኳ አትጠፋም። BSB BSB: Yet not even a hair of your head will perish.
19 ULB በትዕግሥታችሁም ነፍሳችሁን ታተርፋላችሁ። BSB BSB: By your patient endurance you will gain your souls.
21 ULB በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፣ በከተማይቱ መካከል ያሉትም ለቀው ይሂዱ፣ በገጠር ያሉት ደግሞ ወደ ከተማይቱ አይግቡ። BSB BSB: Then let those who are in Judea flee to the mountains, let those in the city get out, and let those in the country stay out of the city.
22 ULB የተጻፈው እንዲፈጸም እነዚህ ጊዜያት የበቀል ጊዜያት ናቸውና። BSB BSB: For these are the days of vengeance, to fulfill all that is written.
23 ULB በእነዚያ ቀኖች ለእርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው! በምድሪቱ ላይ ታላቅ መከራ፣ በዚህ ሕዝብም ላይ ቊጣ ይወርዳል። BSB BSB: How miserable those days will be for pregnant and nursing mothers! For there will be great distress upon the land and wrath against this people.
25 ULB በፀሐይ፣ በጨረቃና በከዋክብት ምልክቶች ይታያሉ። በምድር ላይ ያሉ ሕዝቦች ከባሕርና ከማዕበል ድምፅ የተነሣ ተስፋ በመቊረጥ ይጨነቃሉ። BSB BSB: There will be signs in the sun and moon and stars, and on the earth dismay among the nations, bewildered by the roaring of the sea and the surging of the waves.
26 ULB ከፍርሃትና በዓለም ላይ ሊከሰቱ ያሉትን ነገሮች ከመሥጋት የተነሣ የሚዝሉ ሰዎችም ይኖራሉ። ምክንያቱም የሰማያት ኅይላት ይናወጣሉና። BSB BSB: Men will faint from fear and anxiety over what is coming upon the earth, for the powers of the heavens will be shaken.
27 ULB ከዚያም የሰው ልጅ በኅይልና በታላቅ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል። BSB BSB: At that time they will see the Son of Man coming in a cloud with power and great glory.
28 ULB ነገር ግን እነዚህ ነገሮች መፈጸም ሲጀምሩ፣ መዳናችሁ ስለ ቀረበ ንቁ፣ ቀና ብላችሁ ተመልከቱ። BSB BSB: When these things begin to happen, stand up and lift up your heads, because your redemption is drawing near.”
29 ULB ኢየሱስ አንድ ምሳሌ ነገራቸው፤ “የበለስ ዛፍና ሌሎች ዛፎችን ተመልከቱ። BSB BSB: Then Jesus told them a parable: “Look at the fig tree and all the trees.
30 ULB ቀንበጥ ሲያወጡ፣ በጋ እንደተቃረበ ታውቃላችሁ። BSB BSB: When they sprout leaves, you can see for yourselves and know that summer is near.
31 ULB ልክ እንደዚሁም እነዚህ ነገሮች መፈጸማቸውን ስታዩ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ። BSB BSB: So also, when you see these things happening, know that the kingdom of God is near.
32 ULB እውነቱን እነግራችኋለሁ፣ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ከመፈጸማቸው በፊት ይህ ትውልድ አያልፍም። BSB BSB: Truly I tell you, this generation will not pass away until all these things have happened.
33 ULB ሰማይና ምድር ያልፋሉ፣ ቃሌ ግን አያልፍም። BSB BSB: Heaven and earth will pass away, but My words will never pass away.
34 ULB ልቅ በሆነ አኗኗር፣ በስካርና በጭንቀት ልባችሁ እንዳይከብድ ተጠንቀቁ። ምክንያቱም ያ ቀን እንደ ወጥመድ በድንገት ይመጣባችኋል። BSB BSB: But watch yourselves, or your hearts will be weighed down by dissipation, drunkenness, and the worries of life—and that day will spring upon you suddenly like a snare.
35 ULB በምድር በሚኖሩት ሁሉ ላይም ይመጣባቸዋል። BSB BSB: For it will come upon all who dwell on the face of all the earth.
36 ULB ነገር ግን ከሚከሠቱት ከአነዚህ ነገሮች ሁሉ እንድታመልጡና በሰው ልጅም ፊት ለመቆም እንድትበረቱ ሁልጊዜ ነቅታችሁ ጸልዩ። BSB BSB: So keep watch at all times, and pray that you may have the strength to escape all that is about to happen and to stand before the Son of Man.”
37 ULB ስለዚህ ኢየሱስ በየቀኑ በቤተ መቅደስ ያስተምር፣ ሌሊቱን ደግሞ ወደ ደብረ ዘይት ተራራ እየወጣ ያሳልፍ ነበር። BSB BSB: Every day Jesus taught at the temple, but every evening He went out to spend the night on the Mount of Olives.
38 ULB በቤተ መቅደስም ሲያስተምር ሰዎች ሁሉ ሊሰሙት በማለዳ ይመጡ ነበር። BSB BSB: And early in the morning all the people would come to hear Him at the temple.