1 ULB ሕዝቡ በጠቅላላ ተነሥተው ቆሙ፣ ኢየሱስንም በጲላጦስ ፊት አቀረቡት። BSB BSB: Then the whole council rose and led Jesus away to Pilate.
2 ULB “ይህ ሰው ራሱን ክርስቶስ፣ ንጉሥ ነኝ ሲልና ለቄሣር ግብር እንዳይከፈል በመከልከል አገር ሲበጠብጥ አግኝተነዋል” በማለት ይከሱት ጀመር። BSB BSB: And they began to accuse Him, saying, “We found this man subverting our nation, forbidding payment of taxes to Caesar, and proclaiming Himself to be Christ, a King.”
3 ULB ጲላጦስ፣ “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” በማለት ጠየቀው። ኢየሱስም፣ “አንተ አልህ” ብሎ መለሰለት። BSB BSB: So Pilate asked Him, “Are You the King of the Jews?” “You have said so,” Jesus replied.
4 ULB ጲላጦስ የካህናት አለቆችንና የተሰበሰቡትን ሕዝብ፣ “በዚህ ሰው ምንም ስሕተት አላገኘሁበትም” አላቸው። BSB BSB: Then Pilate said to the chief priests and the crowds, “I find no basis for a charge against this man.”
5 ULB እነርሱ ግን፣ “ከገሊላ ጀምሮ በመላው ይሁዳ፣ እስከዚህ ስፍራም እንኳ እያስተማረ ሕዝቡን ያነሣሣል” በማለት አጥብቀው ተናገሩ። BSB BSB: But they kept insisting, “He stirs up the people all over Judea with His teaching. He began in Galilee and has come all the way here.”
6 ULB ስለዚህ ጲላጦስ ይህን በሰማ ጊዜ ሰውየው ገሊላዊ እንደ ሆነ አጠያየቀ። BSB BSB: When Pilate heard this, he asked if the man was a Galilean.
7 ULB ከሄሮድስ ሥልጣን በታች እንደ ሆነ ተረድቶ በዚያው ሰሞን ኢየሱስን በኢየሩሳሌም ወደ ነበረው ሄሮድስ ላከው። BSB BSB: And learning that Jesus was under Herod’s jurisdiction, he sent Him to Herod, who himself was in Jerusalem at that time.
8 ULB ሄሮድስ ኢየሱስን ባየው ጊዜ በጣም ደስ አለው፣ ምክንያቱም ለረጅም ጊዜ ሊያየው ሲፈልግ ነበር። ስለ እርሱ ሰምቶ የነበረ ሲሆን፣ አንዳንድ ተአምራት ሲያደርግ ለማየትም ተስፋ ነበረው። BSB BSB: When Herod saw Jesus, he was greatly pleased. He had wanted to see Him for a long time, because he had heard about Him and was hoping to see Him perform a miracle.
9 ULB ሄሮድስ ኢየሱስን በብዙ ቃሎች ቢጠይቅም፣ ኢየሱስ ግን ምንም መልስ አልሰጠውም። BSB BSB: Herod questioned Jesus at great length, but He gave no answer.
10 ULB በዚህ ጊዜ የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ተነሥተው ቆሙና በኅይለ ቃል ከሰሱት። BSB BSB: Meanwhile, the chief priests and scribes stood there, vehemently accusing Him.
11 ULB ሄሮድስ ከወታደሮቹ ጋር በመሆን ኢየሱስን ሰደበው፣ አላገጠበትም፤ ጥሩ ልብስ ካለበሰው በኋላ መልሶ ወደ ሄሮድስ ላከው። BSB BSB: And even Herod and his soldiers ridiculed and mocked Him. Dressing Him in a fine robe, they sent Him back to Pilate.
12 ULB ከዚያን ቀን ጀምሮ ሄሮድስና ጲላጦስ ወዳጆች ሆኑ (ከዚያ በፊት አንዱ የአንዱ ጠበኞች ነበሩ)። BSB BSB: That day Herod and Pilate became friends; before this time they had been enemies.
13 ULB ከዚያም ጲላጦስ የካህናት አለቆችን፣ ገዢዎችንና ሕዝቡን አንድ ላይ ጠራ፤ BSB BSB: Then Pilate called together the chief priests, the rulers, and the people,
14 ULB እንዲህም አላቸው፤“ይህን ሰው ሰዎችን ለክፉ ድርጊት የሚያነሣሣ አድርጋችሁ ወደ እኔ አመጣችሁት፣ እኔም በፊታችሁ ከጠየቅሁት በኋላ፣ እነሆ፣ እርሱን በምትከሱባቸው ነገሮች ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም። BSB BSB: and said to them, “You brought me this man as one who was inciting the people to rebellion. I have examined Him here in your presence and found Him not guilty of your charges against Him.
15 ULB ሄሮድስም ቢሆን ምንም ነገር አላገኘበትም፤ ምክንያቱም መልሶ ወደ እኛ ልኮታልና፤ እነሆ፣ እርሱን ለሞት የሚያደርስ በዚህ ሰው የተፈጸመ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም። BSB BSB: Neither has Herod, for he sent Him back to us. As you can see, He has done nothing deserving of death.
16 ULB ስለዚህ ቀጥቼው እለቀዋለሁ።" ጲላጦስም በበዓሉ ለአይሁድ አንድ እስረኛ የመፍታት ግዴታ ነበረበት። BSB BSB: Therefore I will punish Him and release Him.”
18 ULB ነገር ግን እነርሱ በአንድነት፣ “ይህን ሰው አስወግደው፣ በርናባስን ለእኛ ፍታልን!" በማለት ጮኹ። BSB BSB: But they all cried out in unison: “Away with this man! Release Barabbas to us!”
19 ULB በርናባስ በከተማይቱ ውስጥ አንድ ዐይነት ዐመፅና ግድያ በመፈጸም የታሰረ ሰው ነበር። BSB BSB: (Barabbas had been imprisoned for an insurrection in the city, and for murder.)
20 ULB ጲላጦስ ኢየሱስን ሊፈታ ፈልጎ እንደ ገና ሕዝቡን አነጋገራቸው። BSB BSB: Wanting to release Jesus, Pilate addressed them again,
21 ULB ነገር ግን ሕዝቡ፣ “ስቀለው፣ ስቀለው” እያሉ ጮኹ። BSB BSB: but they kept shouting, “Crucify Him! Crucify Him!”
22 ULB ለሦስተኛ ጊዜም እንዲህ አላቸው፤ “ለምን? ይህ ሰው የሠራው ክፋት ምንድን ነው? ለሞት ቅጣት የሚያበቃ ነገር አላገኘሁበትም። ስለዚህ ቀጥቼው እለቀዋለሁ።” BSB BSB: A third time he said to them, “What evil has this man done? I have found in Him no offense worthy of death. So after I punish Him, I will release Him.”
23 ULB እነርሱ ግን ኢየሱስ እንዲሰቀል በመጠየቅ ሳያቋርጡ አብዝተው ጮኹ። ጩኸታቸውም ጲላጦስን አሳመነው። BSB BSB: But they were insistent, demanding with loud voices for Jesus to be crucified. And their clamor prevailed.
24 ULB ስለዚህ ጲላጦስ ፍላጎታቸውን ለማሟለት ወሰነ። BSB BSB: So Pilate sentenced that their demand be met.
25 ULB እንዲፈታላቸው የጠየቁትን፣ በዐመፅና በግድያ ምክንያት የታሰረውን ሰው ለቀቀላቸው። ኢየሱስን ግን ለፈቃዳቸው አሳልፎ ሰጠው። BSB BSB: As they had requested, he released the one imprisoned for insurrection and murder, and he handed Jesus over to their will.
26 ULB እየወሰዱት ሳሉ፣ ከገጠር ይመጣ የነበረ ስምዖን የተባለ የቀሬናን ሰው ያዙና ኢየሱስ ይሸከመው የነበረውን መስቀል አሸከሙት። BSB BSB: As the soldiers led Him away, they seized Simon of Cyrene on his way in from the country, and they put the cross on him to carry behind Jesus.
27 ULB እጅግ ብዙ ሕዝብና ለእርሱ የሚያዝኑና የሚያለቅሱ ሴቶች ይከተሉት ነበር። BSB BSB: A great number of people followed Him, including women who kept mourning and wailing for Him.
28 ULB ኢየሱስም ወደ እነርሱ ዞር ብሎ፣ “የኢየሩሳሌም ሴቶች ሆይ፣ ለእኔ ሳይሆን ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ” አለ። BSB BSB: But Jesus turned to them and said, “Daughters of Jerusalem, do not weep for Me, but weep for yourselves and for your children.
29 ULB እነሆ፣ 'መካን የሆኑና ያልወለዱ ማኅፀኖች እንዲሁም ያላጠቡ ጡቶች የተባረኩ ናቸው' የሚሉባቸው ቀኖች ይመጣሉና። BSB BSB: Look, the days are coming when people will say, ‘Blessed are the barren women, the wombs that never bore, and breasts that never nursed!’
30 ULB ከዚያም ተራሮችን፣ 'በላያችን ውደቁ፣ ኮረብቶችንም ክደኑን ማለትይጀምራሉ።' BSB BSB: At that time ‘they will say to the mountains, “Fall on us!” and to the hills, “Cover us!”’
31 ULB ዛፉ እርጥብ እያለ ይህን ነገር ካደረጉ፣ በሚደርቅበት ጊዜ ምን ይሆናል?" BSB BSB: For if men do these things while the tree is green, what will happen when it is dry?”
32 ULB ሌሎች ሁለት ወንጀለኞችም ከእርሱ ጋር ሊገደሉ ተወሰዱ። BSB BSB: Two others, who were criminals, were also led away to be executed with Jesus.
35 ULB “ሌሎችን አዳነ፣ እርሱ በእግዚአብሔር የተመረጠ ክርስቶስ ከሆነ አስኪ ራሱን ያድን” በማለት ገዢዎቹ እየዘበቱበት ሳለ ሕዝቡ ቆመው ያዩ ነበር። BSB BSB: The people stood watching, and the rulers sneered at Him, saying, “He saved others; let Him save Himself if He is the Christ of God, the Chosen One.”
36 ULB ወታደሮቹም ወደ እርሱ ቀርበው፣ BSB BSB: The soldiers also mocked Him and came up to offer Him sour wine.
37 ULB “አንተ ንጉሥ ከሆንህ ራስህን አድን” በማለት እያሾፉበት ኮምጣጤ ሰጡት። BSB BSB: “If You are the King of the Jews,” they said, “save Yourself!”
38 ULB “የአይሁድ ንጉሥ” የሚል ምልክትም ከበላዩ ተደርጎ ነበር። BSB BSB: Above Him was posted an inscription: THIS IS THE KING OF THE JEWS.
39 ULB ከተሰቀሉት ወንጀለኞች አንዱ፣ "አንተ ክርስቶስ ነህን? ራስህንም እኛንም አድን” በማለት ሰደበው። BSB BSB: One of the criminals who hung there heaped abuse on Him. “Are You not the Christ?” he said. “Save Yourself and us!”
40 ULB ሌላኛው ግን እየገሠጸው፣ “ከፍርድ በታች ሆነህ እግዚአብሔርን አትፈራምን? እኛ በዚህ ያለነው እንደ ሥራችን ስለ ሆነ፣ ትክክል ነው፣ BSB BSB: But the other one rebuked him, saying, “Do you not even fear God, since you are under the same judgment?
41 ULB ነገር ግን ይህ ሰው ምንም ጥፋት አላደረገም” ብሎ መለሰለት። BSB BSB: We are punished justly, for we are receiving what our actions deserve. But this man has done nothing wrong.”
44 ULB ጊዜው ስድስት ሰዓት ገደማ ነበር፣ የፀሐይ ብርሃን በመቋረጡ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ላይ ጨለማ ሆነ። BSB BSB: It was now about the sixth hour, and darkness came over all the land until the ninth hour.
45 ULB ከዚያም የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከመሐል ተቀደደ። BSB BSB: The sun was darkened, and the veil of the temple was torn down the middle.
46 ULB ኢየሱስ፣ “አባት ሆይ፣ ነፍሴን በእጅህ አኖራለሁ” በማለት በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህን ከተናገረ በኋላ ሞተ። BSB BSB: Then Jesus called out in a loud voice, “Father, into Your hands I commit My Spirit.” And when He had said this, He breathed His last.
47 ULB መቶ አለቃው የተደረገውን ነገር ባየ ጊዜ፣ “ይህ ሰው በእውነት ጻድቅ ነበር” በማለት እግዚአብሔርን አከበረ። BSB BSB: When the centurion saw what had happened, he gave glory to God, saying, “Surely this was a righteous man.”
48 ULB ሁኔታውን ለማየት እጅግ ብዙ ሰዎች በመጡ ጊዜ፣ የተደረጉትን ነገሮች አይተው ደረታቸውን እየደቁ ተመለሱ። BSB BSB: And when all the people who had gathered for this spectacle saw what had happened, they returned home beating their breasts.
49 ULB ነገር ግን ከገሊላ ጀምሮ የተከተሉት አንዳንድ ወንዶችና ሴቶች ከርቀት ቆመው ይህን ድርጊት ይከታተሉ ነበር። BSB BSB: But all those who knew Jesus, including the women who had followed Him from Galilee, stood at a distance watching these things.
50 ULB እነሆ፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት መምጣት የሚጠባበቅ፣ ከአይሁድ ከተማ፣ ከአርማቲያ የሆነ ዮሴፍ የሚባል BSB BSB: Now there was a Council member named Joseph, a good and righteous man,
51 ULB (በውሳኔያቸውና በድርጊታቸው ያልተስማማ) አንድ መልካምና ጻድቅ ሰው ነበረ። BSB BSB: who had not consented to their decision or action. He was from the Judean town of Arimathea and was waiting for the kingdom of God.
52 ULB ይህ ሰው ወደ ጲላጦስ በመቅረብ የኢየሱስን አስከሬን እንዲሰጠው ጠየቀው። BSB BSB: He went to Pilate to ask for the body of Jesus.
53 ULB አስክሬኑን አውርዶ በጥሩ የተልባ እግር ጨርቅ ከፈነውና ማንም ባልተቀበረበት ከድንጋይ በተወቀረ መቃብር ውስጥ አኖረው። BSB BSB: Then he took it down, wrapped it in a linen cloth, and placed it in a tomb cut into the rock, where no one had yet been laid.
54 ULB ጊዜው የዝግጅት ቀን የነበረ ሲሆን፣ ሰንበትም እየገባ ነበር። BSB BSB: It was Preparation Day, and the Sabbath was beginning.
55 ULB ከእርሱ ጋር ከገሊላ የመጡ ሴቶች ተከትለውት በመሄድ መቃብሩንና አስከሬኑ እንዴት እንዳረፈ አዩ። BSB BSB: The women who had come with Jesus from Galilee followed, and they saw the tomb and how His body was placed.
56 ULB ከዚያም ተመልሰው ቅመማ ቅመምና ቅባቶችን አዘጋጁ። ሰንበት ስለ ነበር በሕጉ መሠረት ዐረፉ። BSB BSB: Then they returned to prepare spices and perfumes. And they rested on the Sabbath, according to the commandment.