2 ULB ‹‹የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ የት ነው? የእርሱን ኮከብ በምሥራቅ አየን፣ ልንሰግድለትም መጥተናል፡፡›› BSB BSB: asking, “Where is the One who has been born King of the Jews? We saw His star in the east and have come to worship Him.”
3 ULB ንጉሡ ሄሮድስ ይህን ሲሰማ ተረበሸ፤ መላው ኢየሩሳሌምም ከእርሱ ጋር ታወከ፡፡ BSB BSB: When King Herod heard this, he was disturbed, and all Jerusalem with him.
4 ULB ሄሮድስ የካህናቱን አለቆችና የሕዝቡን የሕግ መምህራን ሰብስቦ፣ ‹‹ክርስቶስ የሚወለደው የት ነው?›› በማለት ጠየቀ፡፡ BSB BSB: And when he had assembled all the chief priests and scribes of the people, he asked them where the Christ was to be born.
5 ULB ‹‹በቤተ ልሔም ይሁዳ›› አሉት፤ በነቢዩ የተጻፈው ይህ ነውና፡ BSB BSB: “In Bethlehem in Judea,” they replied, “for this is what the prophet has written:
6 ULB በይሁዳ ምድር የምትገኚ አንቺ ቤተ ልሔም፣ ከይሁዳ ገዦች በምንም አታንሺም፣ ሕዝቡን እስራኤልን የሚጠብቅ ገዥ፣ ከአንቺ ይወጣልና፡፡ BSB BSB: ‘But you, Bethlehem, in the land of Judah, are by no means least among the rulers of Judah, for out of you will come a ruler who will be the shepherd of My people Israel.’”
7 ULB ከዚያም በኋላ ሄሮድስ ኮከቡ በትክክል በምን ሰዓት ታይቶ እንደ ነበር ሊጠይቃቸው ጠቢባኑን በምስጢር ጠራቸው፡፡ BSB BSB: Then Herod called the Magi secretly and learned from them the exact time the star had appeared.
8 ULB ወደ ቤተ ልሔምም ላካቸው፤ ‹‹ሂዱና ሕፃኑን በጥንቃቄ ፈልጉ፡፡ ስታገኙት እኔም ደግሞ እንድመጣና እንድሰግድለት ንገሩኝ›› አላቸው፡፡ BSB BSB: And sending them to Bethlehem, he said: “Go and search carefully for the Child, and when you find Him, report to me, so that I too may go and worship Him.”
9 ULB ንጉሡ የተናገረውን ከሰሙ በኋላ ሄዱ፤ በምሥራቅ አይተውት የነበረውም ኮከብ ሕፃኑ በነበረበት ላይ እስኪደርስና እስኪቆም ድረስ በፊታቸው ይሄድ ነበር፡፡ BSB BSB: After they had heard the king, they went on their way, and the star they had seen in the east went ahead of them until it stood over the place where the Child was.
10 ULB ጠቢባኑ ኮከቡን ባዩት ጊዜ፣ እጅግ በጣም ተደሰቱ፡፡ BSB BSB: When they saw the star, they rejoiced with great delight.
11 ULB ወደ ቤት ገብተው ሕፃኑንም ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፤ ተንበርክከውም ሰገዱለት፡፡ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው የወርቅ፣ የዕጣንና የከርቤ ስጦታ አቀረቡለት፡፡ BSB BSB: On coming to the house, they saw the Child with His mother Mary, and they fell down and worshiped Him. Then they opened their treasures and presented Him with gifts of gold and frankincense and myrrh.
12 ULB እግዚአብሔር ጠቢባኑን ወደ ሄሮድስ ተመልሰው እንዳይሄዱ በሕልም አስጠነቀቃቸው፤ ስለዚህም በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው ሄዱ፡፡ BSB BSB: And having been warned in a dream not to return to Herod, they withdrew to their country by another route.
13 ULB ጠበባኑ ከሄዱ በኋላ፣ የጌታ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገለጠለትና፣ "ተነሥ፣ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፡፡ እኔ እስክነግርም ድረስ እዚያ ቈይ፤ ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልጋልና" አለው፡፡ BSB BSB: When the Magi had gone, an angel of the Lord appeared to Joseph in a dream. “Get up!” he said. “Take the Child and His mother and flee to Egypt. Stay there until I tell you, for Herod is going to search for the Child to kill Him.”
14 ULB በዚያ ሌሊት ዮሴፍ ተነሣ፣ ሕፃኑንና እናቱንም ይዞ ወደ ግብፅ ሄደ፡፡ BSB BSB: So he got up, took the Child and His mother by night, and withdrew to Egypt,
16 ULB ከዚያም ሄሮድስ ጠቢባኑ እንደ ተሣለቁበት ሲገነዘብ በጣም ተናደደ፡፡ በቤተ ልሔምና በዚያ አውራጃ የነበሩ ወንድ ሕፃናትን፣ እንደዚሁም ሁለት ዓመትና ከዚያም በታች የሆኑትን ሁሉ ከጠቢባኑ በትክክል በተረዳው ጊዜ መሠረት ልኮ አስፈጀ፡፡ BSB BSB: When Herod saw that he had been outwitted by the Magi, he was filled with rage. Sending orders, he put to death all the boys in Bethlehem and its vicinity who were two years old and under, according to the time he had learned from the Magi.
17 ULB በዚያም በነቢዩ ኤርምያስ ተነግሮ የነበረው፡- BSB BSB: Then what was spoken through the prophet Jeremiah was fulfilled:
18 ULB ‹‹ድምፅ በራማ ተሰማ፣ ልቅሶና መሪር ዋይታ፣ ራሔል ስለ ልጆቿ በማልቀስ፣ ለመጽናናትም እምቢ አለች፣ በሕይወት የተረፈ የለምና›› የሚለው ተፈጸመ፡፡ BSB BSB: “A voice is heard in Ramah, weeping and great mourning, Rachel weeping for her children and refusing to be comforted, because they are no more.”
20 ULB ‹‹ሕፃኑን ሊገድሉት የፈለጉት ስለ ሞቱ፣ ተነሣ፤ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ›› አለው፡፡ BSB BSB: “Get up!” he said. “Take the Child and His mother and go to the land of Israel, for those seeking the Child’s life are now dead.”
21 ULB ዮሴፍ ተነሣ፣ ሕፃኑንና እናቱን ይዞ ወደ እስራኤል አገር ሄደ፡፡ BSB BSB: So Joseph got up, took the Child and His mother, and went to the land of Israel.
22 ULB አርኬላዎስ በአባቱ በሄሮድስ ስፍራ ተተክቶ ይሁዳን ይገዛ እንደ ነበረ ሲሰማ ግን ወደዚያ ለመሄድ ፈራ፡፡ እግዚአብሔር በሕልም ካስጠነቀቀው በኋላ፣ ወደ ገሊላ አውራጃ ሄደ፤ BSB BSB: But when he learned that Archelaus was reigning in Judea in place of his father Herod, he was afraid to go there. And having been warned in a dream, he withdrew to the district of Galilee,