1 ULB በእነዚያ ቀኖች መጥምቁ ዮሐንስ በይሁዳ ምድረ በዳ፤ BSB BSB: In those days John the Baptist came, preaching in the wilderness of Judea
2 ULB "መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ" እያለ እየሰበከ መጣ። BSB BSB: and saying, “Repent, for the kingdom of heaven is near.”
3 ULB በነቢዩ ኢሳይያስ፦ "ምድረ በዳ ውስጥ የሚጮኽ ሰው ድምፅ፣ የጌታን መንገድ አዘጋጁ፣ ጎዳናዎቹንም አስተካክሉ" ተብሎ የተነገረለት ይህ ነውና። BSB BSB: This is he who was spoken of through the prophet Isaiah: “A voice of one calling in the wilderness, ‘Prepare the way for the Lord, make straight paths for Him.’”
4 ULB ዮሐንስ ይለብስ የነበረው የግመል ጠጕር፣ በወገቡ የሚታጠቀውም የቆዳ ጠፍር ነው፤ ምግቡም አንበጣና የዱር ማር ነበረ። BSB BSB: John wore a garment of camel’s hair, with a leather belt around his waist. His food was locusts and wild honey.
5 ULB በዚያ ጊዜ ኢየሩሳሌም፣ መላው ይሁዳና በዮርዳኖስ ወንዝ ዙሪያ ያለ አገር ሁሉ ወደ እርሱ ይመጡ ነበር። BSB BSB: People went out to him from Jerusalem and all Judea and the whole region around the Jordan.
6 ULB ሕዝቡ ኀጢአታቸውን እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ በእርሱ እጅ ተጠመቁ። BSB BSB: Confessing their sins, they were baptized by him in the Jordan River.
7 ULB ነገር ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ለመጠመቅ ወደ እርሱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፣ "እናንተ የመርዛማ እባቦች ልጆች ከሚመጣው ቊጣ ለማምለጥ ማን አስጠነቀቃችሁ? BSB BSB: But when John saw many of the Pharisees and Sadducees coming to his place of baptism, he said to them, “You brood of vipers, who warned you to flee from the coming wrath?
8 ULB ለንስሐ የሚጠቅም ፍሬ ይኑራችሁ። BSB BSB: Produce fruit, then, in keeping with repentance.
9 ULB ለራሳችሁም አብርሃም አባታችን አለን" ብላችሁ አታስቡ። እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች እንኳ ለአብርሃም ልጆችን ማስነሣት እንደሚችል እነግራችኋለሁና። BSB BSB: And do not presume to say to yourselves, ‘We have Abraham as our father.’ For I tell you that out of these stones God can raise up children for Abraham.
10 ULB አሁን መጥረቢያው በዛፎቹ ሥር ተቀምጦአል። ስለዚህ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል በእሳት ውስጥም ይጣላል። BSB BSB: The axe lies ready at the root of the trees, and every tree that does not produce good fruit will be cut down and thrown into the fire.
11 ULB እኔ ለንስሐ የማጠምቃችሁ በውሃ ነው፤ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቃል፤ ጫማውን መሸከምም እንኳ አይገባኝም። እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል። BSB BSB: I baptize you with water for repentance, but after me will come One more powerful than I, whose sandals I am not worthy to carry. He will baptize you with the Holy Spirit and with fire.
12 ULB ዐውድማውን ፈጽሞ ለማጥራትና ስንዴውን በጎተራ ውስጥ ለመክተት መንሹ በእጁ ነው። ገለባውን ግን ፈጽሞ በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል። BSB BSB: His winnowing fork is in His hand to clear His threshing floor and to gather His wheat into the barn; but He will burn up the chaff with unquenchable fire.”
13 ULB ከዚያም ኢየሱስ በዮሐንስ እጅ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መጣ። BSB BSB: At that time Jesus came from Galilee to the Jordan to be baptized by John.
14 ULB ነገር ግን "እኔ አንተ እንድታጠምቀኝ ሲገባ፣ አንተ እንዴት ወደ እኔ ትመጣለህ?" በማለት ሊያስቆመው ሞከረ። BSB BSB: But John tried to prevent Him, saying, “I need to be baptized by You, and do You come to me?”
15 ULB ኢየሱስም መልሶ፣ "አሁን ይህን ፍቀድ፤ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ለእኛ ተገቢ ነውና" አለው። ከዚያም በኋላ ዮሐንስ ፈቀደለት። BSB BSB: “Let it be so now,” Jesus replied. “It is fitting for us to fulfill all righteousness in this way.” Then John permitted Him.
17 ULB እነሆ፣ የምወደው ልጄ ይህ ነው። "በእርሱ እጅግ ደስ ይለኛል" የሚል ድምፅ ከሰማያት መጣ። BSB BSB: And a voice from heaven said, “This is My beloved Son, in whom I am well pleased!”