1 ULB አንቺ የልዑል ልጅ! እግሮችሽ በነጠላ ጫማ ውስጥ ሲታዩ እንዴት ያምራሉ? የዳሌዎችሽ ቅርጽ በእውቅ አንጥረኛ እጅ የተሠሩ ዕንቁዎችን ይመስላሉ። BSB BSB: How beautiful are your sandaled feet, O daughter of the prince! The curves of your thighs are like jewels, the handiwork of a master.
2 ULB እንብርትሽ ክብ ጽዋ ይመስላል፤ ድብልቅ ወይን በፍጹም አይጉደለው። ሆድሽ በአበቦች የተከበበ የስንዴ ክምር ይመስላል። BSB BSB: Your navel is a rounded goblet; it never lacks blended wine. Your waist is a mound of wheat encircled by the lilies.
3 ULB ሁለቱ ጡቶችሽ መንታ የሜዳ ፍየሎችን፥ ሁለት የአጋዘን ግልገሎችን ይመስላሉ። BSB BSB: Your breasts are like two fawns, twins of a gazelle.
4 ULB አንገትሽ በዝሆን ጥርስ የተሠራ የጥበቃ ማማ ይመስላል፤ ዓይኖችሽ በባትረቢ በር አጠገብ በሐሴቦን ያሉትን ኩሬዎች ይመስላሉ። አፍንጫሽ ወደ ደማስቆ አቅጣጫ የሚመለከተውን በሊባኖስ ያለውን የመጠበቂያ ማማ ይመስላል። BSB BSB: Your neck is like a tower made of ivory; your eyes are like the pools of Heshbon by the gate of Bath-rabbim; your nose is like the tower of Lebanon, facing toward Damascus.
5 ULB ራስሽ በአንቺ ላይ የቀርሜሎስን ተራራ ይመስላል፤ በራስሽ ላይ ያለው ጸጉር ጥቁር ሐምራዊ ነው። ንጉሡ በረጅሙ ጸጉርሽ ተይዞ ታስሮአል። BSB BSB: Your head crowns you like Mount Carmel, the hair of your head like purple threads; the king is captured in your tresses.
6 ULB ተወዳጇ ሆይ፥ እንዴት የምታስደስቺ፥ ውብና ያማርሽ ነሽ! BSB BSB: How fair and pleasant you are, O love, with your delights!
7 ULB ቁመትሽ የቴምር ዘንባባ ዛፍ ይመስላል፥ ጡቶችሽም እንደ ተከማቹ ፍሬዎች ናቸው። BSB BSB: Your stature is like a palm tree; your breasts are clusters of fruit.
8 ULB እኔም፥ "በዚያ የዘንባባ ዛፍ ላይ እወጣለሁ፤ ቅርንጫፎቹንም እይዛለሁ" ብዬ አሰብኩ። ጡቶችሽ የወይን ክምችቶች ይሁኑ፥ የአፍንጫሽ እስትንፋስ መዓዛውም እንደ እንኮይ ይሁኑ። BSB BSB: I said, “I will climb the palm tree; I will take hold of its fruit.” May your breasts be like clusters of the vine, the fragrance of your breath like apples,
9 ULB አፍሽ እንደ ምርጥ የወይን ጠጅ ይሁን፥ በዝግታም በውዴ ከንፈርና ጥርስ እየፈሰሱ ይንቆርቆሩ። ወጣቷ ፍቅረኛዋን እንዲህ ትለዋለች፥ BSB BSB: and your mouth like the finest wine. May it flow smoothly to my beloved, gliding gently over lips and teeth.
10 ULB እኔ የውዴ ነኝ፥ እርሱም ይመኘኛል። BSB BSB: I belong to my beloved, and his desire is for me.
11 ULB ውዴ ሆይ ና፥ ወደ ገጠር እንሂድ፥ በመንደሮቹም እንደር። BSB BSB: Come, my beloved, let us go to the countryside; let us spend the night among the wildflowers.
12 ULB ወደ ወይኑ ቦታ ለመሄድ ማልደን እንነሣ፤ ወይናቸው አፍርቶ፥ አበባቸውም ፈክቶ፥ ሮማኑም አብቦ እንደሆነ እንይ። በዚያም ፍቅሬን እሰጥሃለሁ። BSB BSB: Let us go early to the vineyards to see if the vine has budded, if the blossom has opened, if the pomegranates are in bloom—there I will give you my love.
13 ULB ትርንጉዎች መዓዛቸውን ሰጡ፤ በምንቆይበት ቤት ደጃፍ ሁሉም ዓይነት የተመረጡ ፍሬዎች አሉ፥ አዲስና የቆዩ፥ ውዴ ሆይ፥ ለአንተ አስቀምጫቸዋለሁ። BSB BSB: The mandrakes send forth a fragrance, and at our door is every delicacy, new as well as old, that I have treasured up for you, my beloved.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.